TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ አንድም ሰላማዊ ሰው እንዲሞት አልፈልግም" ብ/ጄ #ብርሃኑ_ጁላ
.
.
.
ሰሞኑን ሰባተኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን ተከብሯል። በበዓሉ የማጠቃለያ ዝግጅት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ "የመከላከያ ሠራዊቱ ለጠላቶች የፍርሃት፤ ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ የኩራት ምንጭ ነው" ሲሉ ለሠራዊቱ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ነገር ግን በተለያዩ ጊዜያት ሠራዊቱ በተሰማራባቸው አካባቢዎች ከሚከሰቱ የሰላማዊ ሰዎች ጉዳቶች ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል። የቅርቡን ለመጥቀስ በአማራ ክልል፣ በምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት ቀበሌ፣ ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ተተኮሰ በተባለ ጥይት በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና ግድያውን በመቃወም የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞ ማሰማቱ የሚታወስ ነው።

ከቀናት በፊት (ማክሰኞ የካቲት 5/2011) በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ፣ ሂዲሎላ በምትባል ከተማ አምስት ግለሰቦች ተገድለው፤ ሌሎች ሁለት ዜጎች ደግሞ ቆስለዋል። ከሟቾቹ ሁለቱ ከሠርጋቸው እየተመለሱ የነበሩ #ሙሽሮች ናቸው። የተቀሩት ሦስቱ ደግሞ አጃቢዎቻቸው። የአካባቢው ነዋሪዎችም ግድያው #በመከላከያ_ሠራዊት እንደተፈጸመ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ #በዳኔ_ሊበን፣ መከላከያ በቅርቡ ወደ ከተማዋ መግባቱን ገልጸው ስለክስተቱ በስፍራው የሚገኘውን የመከላከያ ኃይል ጠይቀው "ተኩስ #ተከፍቶብን ምላሽ ስንሰጥ ነው አደጋው የደረሰው" የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

በዚህና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የመከላከያ ሠራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም የሆኑትን ብርጋዴየር ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ቢቢሲ ረቡዕ እለት አነጋግሯቸው ነበር።

ቢቢሲ፡ በቦረና ዞን ሰሞኑን ስለተከሰተው ነገር የሚያውቁት ነገር አለ?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ የትናንትናና የዛሬ መረጃ የለኝም ከቢሮ ውጭ ስለሆንኩ። ነገር ግን መከላከያ በፊት በአንዳንድ ቦታዎች ስህተት ይሰራ ነበር። ያ አስተሳሰብ አሁንም አለ። በተጨባጭ ግን ያን ችግር ቀርፈን ነው እየሰራን ያለነው። ሆኖም ሰላምን የሚያደፈርሱ፣ የሕግን የበላይነት የሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ ሕጋዊ ስለሆነ ለእሱ መልስ የለኝም። ነገር ግን ሕዝቡ ላይ መከላከያ ችግር እያደረሰ ነው የሚባል ነገር ካለ መከላከያ ተጠያቂ ይሆናል።

ቢቢሲ፡ የሕዝቡ ቅሬታ ተጨባጭ አይደለም እያሉኝ ነው?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ ችግሩ መከላከያ ሰው ገደለ ከተባለ ሚዲያ ያንን ወስዶ ይዘግባል። ቦታ ላይ ሄዶ አጣርቶ፣ እውነት የቱ ጋ ነው ያለው ብሎ አይፈትሽም። አንተ እንደሚባለው መከላከያ ወጥቶ ሌላ ተልእኮ የሌለው ሰላማዊ ሰው ላይ እርምጃ ይወስዳል ብዬ በፍጹም አላምንም። ምናልባት እርምጃ ወስዶም ከሆነ እዚያ አካባቢ አንድ የሆነ ችግር አለ ማለት ነው።

ቢቢሲ፡ መከላከያ ምንም ስህትት አይሰራም ነው የሚሉኝ?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ ለምሳሌ አንዳንድ ኃይሎች አንዳንዴ ደፈጣ ያደርጉና መከላከያ ላይ እርምጃ ይወስዳሉ። በዚህ ጊዜ መከላከያ ራሱን ለመከላከል ምላሽ ሲሰጥ በተኩስ ልውውጥ አንድም ሰው አይጎዳም ልልህ አልችልም።

ቢቢሲ፡ እርስዎ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በመከላከያ በተፈጸመ ስህተት ተጠያቂ የሆነ የሠራዊቱ አባል አለ?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ ምንም ስህተት አልተሰራም። የተሰራ ስህተትም አላየንም። እኛ የምናውቀው መንግሥትም ሆነ ክልሎች እንዲሁም በእኛም ደረጃ የተገደለ ሰላማዊ ሰው የምናውቀው የለም። እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ አንድም ሰላማዊ ሰው እንዲሞት አልፈልግም። እኔ የማዘው ወታደርም ይሄንኑ ነው ተግባራዊ የሚያደርገው። እንዲህ የሚያደርግ ወታደር ካለም በሕግ ነው የምጠይቀው። በመከላከያ ላይ የሚደረግ ስም ማጥፋት ነው እንጂ መከላከያ ሕዝቡን እየጠበቀ ከሕዝብ ጋር እጅ ለእጅ ሆኖ ነው ሥራውን እየሰራ ያለው።

ቢቢሲ፡ ሪፎርም ተደርጓል በመከላከያ ይባላል። ምንድነው በተጨባጭ የተቀየረው?

•ብ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፡ በተጨባጭ የተቀየረው የመከላከያ አደረጃጀት ነው። በመከላከያ ውስጥ ከላይኛው አመራር ጀምሮ እስከ ታችኛው ድረስ የኢትዮጵን ብሔር ብሔረሰቦች በሚመስል መልኩ ተደራጅቷል። ከዚህ ውጭ አመለካከት ነው የተቀየረው። ወታደሩ የአንድ ብሔር ወይም የአንድ ክልል ወታደር ሳይሆን የአገር ሠራዊት እንደሆነ እንዲረዱ በማድረግ የአመለካከት ለውጥ መጥቷል።

ከዚህ በፊት የነበሩ አንዳንድ ችግሮች እንዲስተካከሉ፣ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሰረት ብቻ እንዲንቀሳቀስ፣ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጎ እንዲሰራ፣ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን የመሳሰሉ ዓይነት ሥራዎችን ሠርተናል። የቀረን ነገር የለም ማለት ግን አይቻልም።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮማንድ ፖስት...

በደቡብ ክልል ለአንድ ወር የሚቆይ #በመከላከያ_ሠራዊት የሚመራ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia