TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" እርምጃ ተወስዶባቸዋል " በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመተማ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አስታወቀ። የወረዳው ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ፥ " የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሲያውኩ የነበሩ ሶስት ጸረ-ሰላም ኃይሎች በጥምር የጸጥታ ኃይል (ልዩ ኃይል ፣ ፀረሽምቅ እና ፖሊስ) ርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብሏል። በጣምራ…
#Metema

የመተማ ወረዳ ፖሊስ #ሰው_በማገት_ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ግለሠቦች በተካሄደ ኦፕሬሽን መመታታቸውን እንዲሁም ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳወቀ።

ትላንት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ " ጎርድም " በተባለው ተራራ በተደረገ ኦፕሬሽን ሰው በማገት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ 4 ግለሰቦች መመታታቸው እና ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ ባዜ ብርሀኑ እና ላቀው የኔሁን የተባሉ ግለሰቦች የተመቱ ሲሆን አያናው አማረ እና ወርቁ ድረስ የተባሉ ግለሰቦች ደግሞ ቆስለው በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ተገልጿል።

ከቀናት በፊት በዚሁ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገትሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ በወረዳው አኩርፈው ሆነ ሸፍተው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በተደረገው የምህረት አዋጅ እድል ተጠቅመው በሰላም ገብተው ከህብረተሰቡ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ፖሊስ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia