TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የቦይንግ ካምፓኒ / #BOEING / ኢትዮጵያን የአፍሪካ አቪየሽን ማዕከል የሚያደርገውን ስትራተጂካዊ የጋራ ስምምነት ሰነድ /MoU/ ተፈራረሙ።

ስምምነቱ ሁለቱ ካምፓኒዎች ለ70 ዓመታት በአቪየሽን መስክ የገነቡት የዳበረ ግንኙነት /partnership/ ታሪክ አካል ሲሆን ኢትዮጵያን የአፍሪካ አቪየሽን መናኸሪያ በማድረግ ሀገሪቱ በአፍሪካ አህጉር የምትጫወተውን ሁላቀፍ ሚና ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ታምኖበታል።

ተጨማሪ : https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-and-boeing-have-signed-strategic-mou-to-position-ethiopia-as-africa-s-aviation-hub

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#Boeing 

በኢትዮጵያ የተከሰከሰው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአደጋው በፊት የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት የሚያሳየውን መረጃ መደበቁን የቀድሞ የቦይንግ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

ፋውንዴሽን ፎር አቪየሽን ሴፍቲ የተባለ ቡድን የሚመሩት የቦይንግ የቀድሞ ሥራ አስኪያጅ ለ157 ሰዎች እልቂት የሆነው እና ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተከሰከሰው 737 ማክስ 9 አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት በኩባንያው ይታወቅ ነበር ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደሚችል እና በርካታ እክሎች እንደነበሩበት ይፋ አድርገዋል።

ፋውንዴሽኑ በአሁኑ ወቅት እየበረሩ ያሉ ከ1000 በላይ የቦይንግ አውሮፕላኖች በሚመረቱበት ወቅት በነበሩ ችግሮች ምክንያት የኤሌክትሪክ ብልሽት ስጋት እንደተጋረጠባቸው ገልጿል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ጉዞውን በጀመረ በስድስት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰው አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ብልሽቶች ነበሩበት ብለዋል።

አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ወቅት አዲስ ሞዴል 737 ማክስ 9 ነበር።

ከዚያ ቀደም ብሎ ተመሳሳይ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ አደጋ ተከስክሶ የ189 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-08-24-2

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia