TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኮች ይፋ ከሚያደርጉት የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ ዋጋ ውጭ የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን እና ሌላ ክፍያ እንዲያቆሙ ወስኗል።

እንዲህ ያሉ ክፍያዎችን ካስከፈሉ እንኳን ከመግዣና መሸጫ ዋጋው ጋር አካተው አንድ ላይ ለደንበኞቻቸው ይፋ እንዲያደርጉት ተብሏል።

ይህም የውጭ ምንዛሬ ግዥና ሽያጭ ላይ ግልፅነትን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ግን ይህ አሰራር ደንበኞች ከውጭ ሀገር ግዢ ለመፈፀም LC ለመክፈት ሲጠይቁ የሚኖረውን ግብይት አይመለከትም ተብሏል፡፡

ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ በስራ ላይ መዋል መጀመሩንም ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

#ShegerFMRADIO #NBE

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" የዋጋ ንረቱ ሰራተኛውን አልፎት ሄዷል! ለዚህም የደመወዝ ማሻሽያው መዘግየት የለበትም " - ኢሠማኮ

የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ስለ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ምን አለ ?

ምክትል ፕሬዝዳንት አያሌው አህመድ ፦

" መንግስት የደመወዝ ጭማሪ አደርጋለው ቢልም ገበያው በዚሁ ከቀጠለ ከሠራተኛው ከአቅሙ በላይ ሊሆንበት ይችላል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያው በታወጀ በማግስቱ ስለሆነ ለመንግስት ሰራተኞች ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ማሻሽያ ሊዘገይ አይገባም።

የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሽያ ተከትሎ በገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ  እየታየ ነው።

ይህ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ለመንግስት ሰራተኛው ይደረጋል የተባለው የደመወዝ ማሻሽያ ዋጋ የለውም።

የገበያው ዋጋ ቁጥጥር በሌለበት እና በተለመደው አይነት መልኩ ከተገቢው በላይ ጭማሪ የሚያሳይ ከሆነ ይጨመራል በተባለው ደሞዝ መቋቋም የማይችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።

የነጋዴው ማህበረሰብም መንግስት የሚያወጣውን መመርያ ተክትሎ የማይጎዱበትን ጭማሪ ካልሆነ በስተቀር በዘፈቀድ ምርቶች እየተደበቁ ሰራተኛው ለአላስፈላጊ ወጪ የሚደረግ ከሆነ አሁንም መልሶ ከችግር የሚወጣበት ሁኔታ አይኖርም።

መንግስትም በቂ የደመወዝ ማሻሽያ ፤ ነጋዴውም ምክንያታዊ ጭማሪ ካላደረገ በገበያው ይበልጥ ቀውስ ሊፈጠር ይችላል።

ለዚህ ደግሞ ቁጥጥር ማድረግ ያለበት መንግስት እና ህብረተሰቡ ነው።

በገበያው ላይ ምን እንዳለ መንግስት ያውቀዋል ፤ ምክንያቱም የዋጋ ንረቱ ሰራተኛውን አልፎት ሄዷል ለዚህም የደመወዝ ማሻሽያው መዘግየት የለበትም። "

#Ethiopia #ShegerFMRadio

@tikvahethiopia
#Ethiopia

" በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ያሉ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በመንግስትም ሆነ በታጣቂዎች በኩል እውነተኛ ከልብ የመነጨ ፍላጎት የለም።

በሁለቱ ክልሎች ባለው ግጭት ምክንያት ንጹሃን እየሞቱ፣ እየተፈናቀሉ፣  እየታገቱ እና ንብረታቸው እየወደመ ነው።

መንግስትም ሆነ በጫካ ያሉ አካላት ይህንን እያወቁ ችግሮቻቸውን በንግግር ለመፍታት ግን ፍላጎት የላቸውም።

ይህም መንግስት እየመራሁት ነው፣ ጫካ ያሉ አካላት ደግሞ እየታገልኩለት ነው ለሚሉት ህዝብ ያላቸውን ምልከታ ያሳያል።

በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ማድረግ ብቻውን መፍትሄ አያመጣም።

ሰላም የሚመጣው እውነተኛ ሰላም በመሻት እና በፖለቲካ ውሳኔም ጭምር ነው።

አሁን በመንግስት እና በታጣቂዎች መካከል እየታየ ያለው ግን መናናቅ እና አንዱ አንዱን ለማሸነፍ የሚደረግ ትግል ነው።

ይህ ደግሞ ንጹሀን ዜጎች ባሉበት ስቃይ እንዲቀጥሉ አድርጓቸዋል። "
- ደስታ ዲንቃ (የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ)

#ShegerFMRadio

@tikvahethiopia