TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" እርምጃ ተወስዶባቸዋል " በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመተማ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አስታወቀ። የወረዳው ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ፥ " የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሲያውኩ የነበሩ ሶስት ጸረ-ሰላም ኃይሎች በጥምር የጸጥታ ኃይል (ልዩ ኃይል ፣ ፀረሽምቅ እና ፖሊስ) ርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብሏል። በጣምራ…
#Metema

የመተማ ወረዳ ፖሊስ #ሰው_በማገት_ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ግለሠቦች በተካሄደ ኦፕሬሽን መመታታቸውን እንዲሁም ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳወቀ።

ትላንት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ " ጎርድም " በተባለው ተራራ በተደረገ ኦፕሬሽን ሰው በማገት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ 4 ግለሰቦች መመታታቸው እና ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ ባዜ ብርሀኑ እና ላቀው የኔሁን የተባሉ ግለሰቦች የተመቱ ሲሆን አያናው አማረ እና ወርቁ ድረስ የተባሉ ግለሰቦች ደግሞ ቆስለው በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ተገልጿል።

ከቀናት በፊት በዚሁ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ በወረዳው አኩርፈው ሆነ ሸፍተው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በተደረገው የምህረት አዋጅ እድል ተጠቅመው በሰላም ገብተው ከህብረተሰቡ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ፖሊስ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Metema

የምዕራብ ጎንደር ዞን ፥ ከ6 ሺህ በላይ የሱዳን ተፈናቃዮች በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስታውቋል።

ዞኑ ፥ በሱዳን በተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት የ42 ሀገራት ዜጎች  በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ነው ያመለከተው።

ወደ አካባቢው ሊገባ የሚችለውን ተፈናቃይ ለመቀበል በሚቻልበት ጉዳይ ቅድመ ዝግጅት  ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀው ዞኑ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብቻ  ከ6 ሺህ በላይ የ42 ሀገራት  ዜጎች መግባታቸውን አመልክቷል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ 941  #ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ገልጿል።

ተፈናቃዮቹ የጤና ችግር እንዳይገጥማቸው የጤና ባለሙያ በመመደብ  አገልግሎት እየተሰጠ ነው ያለው ዞኑ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በኩል መካከለኛና ከፍተኛ ተሽከርካሪዎች ተመድቦ ተፈናቃዮች ወደ የሚፈልጉት አካባቢ የመሸኘት ሥራ ተሠርቷል ብሏል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርም ውኃና ብስኩት በማቅረብ እያገዘ እንደሆነ ዞኑ ገልጿል።

በቀጣይ ችግሩ እየሰፋ የሚሄድ ከኾነ ወደ ቀጣናው ሊገባ የሚችለውን ስደተኛ ሊያስተናግድ የሚችል ቦታ የመለየት ሥራ መሰራቱን ዞኑን ማስታወቁን አሚኮ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
" ህዝቡ በጣም ተቸግሮ ነው ያለ ዛሬ ፣ ሰው ውሎ የማይገባበት ፤ ያሰበበት ደርሶ የማይመለስበት ነው " - ወንድማቸው የተገደለባቸው ነዋሪ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳና አካባቢው ተባብሷል በተባለ የታጣቂ ኃይሎች እገታና ግድያ ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል አመልክተዋል።

አቶ አወቀ ሰጠኝ የተቡ የህዝብ ማመላለሽ ሚኒባስ አሽከርካሪ የሆነው ወንድማቸው ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ሰኔ 26 በስራ ላይ እያለ በታጣቂዎች ጥቃት መገደሉን አመልክተዋል።

በዕለቱ 18 ሰዎች አሳፍሮ ከጎንደር ተነስቶ መተማ እየተጓዘ ነበር።

' መቃ ' በተባለው ቦታ ላይ ነው ታጣቂዎች ጥይት ተኩሰው እሱን ጨምሮ 3 ሰዎች ሲገደሉ 14 ሰዎች ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል።

ረዳቱ ሩጦ ማምለጡን አቶ አወቀ አስረድተዋል።

ሌላ ከኋላ የመጣ አንድ መኪናም ሰው ባይገደልም አስወርደው እንደሄዱ ጠቁመዋል።

" ሁል ጊዜ ግድያ፣ ሁል ጊዜ እገታ፣ ሞት በቃ በጣም የሚያሳዝን ነው ፤ ገላጋይ የሌለበት ሀገር ሆነናል " ሲሉ በሀዘም ስሜት ሆነው ተናግረዋል።

" ህዝቡ ተቸግሮ ነው ያለ ዛሬ ሰው ውሎ የማይገባበት ፤ ያሰበበት ደርሶ የማይመለስበት ፣ የሰው ህይወት የሚጨፈጨፍበት ሰዓትና ጊዜ ላይ ነው ያለን። ምንም የሚያድነን አላገኘንም፣ መንግስትም ሊያድነን አልቻለም " ብለዋል።

መተማ አጠቃላይ ሆስፒታል አስክሬን ክፍል ውስጥ ሰራተኛ የሆኑት  አቅልለው ገነቱ፥ ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች ተወስደው ከነበሩት መካከል እንደሆነ የተጠቆመ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ ቤተሰቡ ባለመቅረቡ ቀብሩ በማዘጋጃ ቤት መፈጸሙን ተናግረዋል።

አንድ ስሜ አይገለጽብኝ ያሉ የመተማ ወረዳ ነዋሪ ፥ በአካባቢው ግድያ እና እገታ ተባብሶ በመቀጠሉ ስራ ውሎ ወደ ቤት መግባት ፈታኝ እንደሆነ ገልጿል።

" እገታ ብቻ መበራከቱ ሳይሆን ሰዎችም ይገደላሉ " ያለው ይኸው ነዋሪ " የታገተ ሰው ብር የጠየቃል መክፈል የማይል አይመለስም " ሲል ተናግረዋል።

ከሰሞኑም ከመተማ ሆስፒታል አንድ አምፑላንስ ከነሹፌሩ መታገቱን ገልጿል። ለማስለቀቂያ 300 ሺህ መጠየቁን ተከትሎ በየመስሪያ ቤቱ እየተለመነ ነው ብሏል።

እገታ በመስፋፋቱ ነዋሪው፣ ሰራተኛው መንቀሳቀስ እንደቸገረው ጠቁሟል።

" በቃ ከቤት መስሪያ ቤት ከዛ ቤት እንጂ ከቤት መውጣት ከባድ ነው " ብሏል።

አንድ ከጎንደር መተማ የሚሰራ ሹፌር ደግሞ ፤ " ማንኛውም ሰው ወጥቶ ለመግባት ፣ ተንቀሳቅሶ ለመስራት ለመነገድም ሌላም የቀን ተቀን ስራ ለማከናወን በጣም ተቸግሯል። አስፈሪ ሁኔታ ነው ያለው። መንገዱ በጣም አስጊ ነው " ሲል ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል።

#AmharaRegion
#VOAAmh.
#Metema

@tikvahethiopia