TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በየጊዜው እየተፈፀሙ ያሉት #ጎራን_የሚለዩ ግድያዎች ፣ ጥቃቶች አሁን ካለው የከፋ ነገር ይዘው እንደይመጡ ፦
➡️ ሳይረፍድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው
➡️ ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ
➡️ ለተበዳይ ወገኖችም ፍትህ መስጠት እንደሚገባ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪዎች አሳስበዋል።

አንድ ቃላቸውን የሰጡ የክልሉ ነዋሪ ፥ " በየጊዜው እየተፈፀሙ ያሉት ግድያዎች የከፋ መዘዝ ይዘው ሊመጡ የሚችሉ ናቸው ስለዚህ ጠንካራ መፍትሄ ይፈልጋል " ብለዋል።

ከግድያ ባለፈም የሚፈፀሙ የወንጀል ተግባራት ደህንነትን የሚነሱ ናቸው ሲሉ አክለዋል።

ነገ እርስ በእርስ ሰዎች እንዳይጠፋፉ አሁን ያለው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይደረስ መድረግ አለበት ብለዋል።

ሌላኛው ቃላቸው የሰጡ ነዋሪ ፥ በዚህ ወር ብቻ ሰዎች በተለያዩ ስፍራዎች ተገድለዋል ብለዋል።

በጋምቤላ አንድ የትራፊክ አባል " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ሰዎች በጥይት ከተመታ በኃላ ችግሮች እየተባባሱ ሄደው በፍራቻ ምክንያት በከተማው እንቅስቃሴ እስከመስተጓጎል ደርሶ እንደነበር ገልጸዋል።

በአቦቦ ወረዳ ደግሞ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ቢያስን 3 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀድምም እዚሁ ወረዳ ግድያ ተፈፅሞ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከቀናት በፊት ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ባለው መስመር ህዝብ ጭኖ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተፈፀመ ጥቃት 5 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳም ግጭቶች እንደነበሩ ጠቁመዋል።

" እየተፈፀሙት ላሉ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች  ተጠያቂነት ሲረጋገጥ እያየን አይደለም " ብለው ችግሩ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።

ሌላው መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የክልሉ ነዋሪ ፥ " በቀን 18/7/2016 ከተርፋም ወደ ጋምቤላ መስመእ የህዝብ ማመላለሻ መኪናን ታጣቂዎች መትተውት እስካሁን የሰው ህይወት አልፏል ፣ የተጎዱም ሆስፒታል ገብተዋል " ብለዋል።

እኚሁ ነዋሪ ጥቃቱ የተፈፀመ ከተርፋም ወደ አቦል ሲቃረብ ቢያንስ 7 ኪ/ሜ እንደሆነ አስረድተዋል።

አቦል የምትባለው ወረዳ ላይ ዝርፊያና ግድያ በተደጋጋሚ እንደሚፈፀም ጠቁመዋል።

ነዋሪው ፥ ባለፈው ሳምንት አንድ  የትራፊክ ፖሊስ መሀል አደባባይ ላይ በባጃጅ በመጡ ሰዎች በጥይት ከተመታ በኃላ ነገሮች መባባሳቸውን ጠቁመዋል።

ሌላው በክልሉ ያለው ችግር የሚያጠፉ ሰዎች በህግ አለመጠየቃቸው ነው ያሉት ነዋሪው " የህግ የበላይነት የሚባለው ነገር ጠፍቶል " ሲሉ ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ አስረድተዋል።

ነዋሪዎቹ ጋምቤላ ክልል ያለው ሁኔታ ቸል የሚባል ስላልሆነ የፌዴራሉም መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥበት አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፥ ጋምቤላ ክልል እየተከሰተ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ የፌደራል እና የክልሉ የፀጥታ አካላት ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር  ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት ነው የፌዴራል እና የክልል ፀጥታ አመራሮች ውይይት የተካሄደው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሸነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ፥ አንዳንድ ግለሰቦች ጎራ እየለዩ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ ማፈናቀልና የተለያዩ ጉዳቶችን እያደረሱ እንዳሉ መገምገሙን ተናግረዋል።

ችግር ፈጣሪዎችም በአስቸኳይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።

የፌደራል ፖሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ የፀጥታ አካላት የፀጥታ ችግሩን ለመቅረፍ ወደ #ኦፕሬሽን_ገብተው ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በቁጥጥር ሥር እያዋሉ ይገኛሉ ብለዋል።

@tikvahethiopia