TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጎንደር🔝

#የጥምቀት_በዓል ከመድረሱ በፊት የማዕከላዊ #ጎንደር ዞን የባሕል ሳምንት ያካሂዳል፡፡ የባሕል ሳምንቱም የአካባቢውን ትውፊታዊ ማንነት እና አጋጊያጥን ጨምሮ ለጎብኝዎች በጎዳና ላይ ትርኢት ያሳያል፡፡ የጎዳና ላይ ትርኢቱም የጥምቀት በዓል ከመከበሩ በፊት የሚካሄድ በመሆኑ የአካባቢውን ባሕል በአምባሳደሮቹ አማካኝነት ፍንትው አድርጎ በማሳየት ትልቅ ሚና እንደተወጣም ተነግሯል፡፡ ስምንተኛው የባህል ሳምንት ፌስቲባል በጎንደር ከጥር 7 እስከ 9/2011 ሲከበር ቆይቶ ከማዕከላዊ ጎንደር የተወጣጡ የባሕል አምባሳደሮች ዛሬ ትርኢታቸውን በጎዳና ላይ በማቅረብ አጠናቅቀዋል፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሃይማኖት ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ ምን ይዟል ? በኢትዮጵያ አዲስ የተዘጋጀ " #የሃይማኖት_ጉዳዮች " ረቂቅ አዋጅ አለ። ይህ ረቂቅ አዋጅ በርካታ ጉዳዮችን ይዟል። አንዱ የአምልኮና የመቃብር ቦታን የተመለከተ ሲሆን ፥ ረቂቅ አዋጁ ለሃይማኖት ተቋማት የመሬት አቅርቦት በመሬት አጠቃቀምና የሊዝ ሕጎች መሠረት ይወሰናል ይላል። ለአምልኮ ወይም ለመቃብር ቦታ በተጠየቀበት አካባቢ ለሃይማኖት ተቋሙ ለተመሳሳይ…
#Update

" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩም የሃይማኖት ተቋማት ቅሬታ ማቅረባቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ተቋማቱ ረቂቅ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት የሁሉንም የሃይማኖት ተቋማት መብትና ክብር የሚጠብቅ መሆኑ ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በአብዛኛው ተከብሮ የቆየው የሃይማኖቶች ነፃነት ላይ ገደቦችን እንዳይጥል ሥጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የቀረቡ ቅሬታዎች ምንድናቸው ?

1ኛ. ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች የተነሳው ቅሬት፦

በረቂቁ አዋጁ ላይ የአደባባይ በዓላትን በሚመለከት " የአደባባይ ኩነት " ተብሎ መቀመጡን በማንሳት ይህ ትክክለኛ ትርጉም አይደለም ብለዋል፡፡

ለዚህ በማሳያ " የአደባባይ ኩነት በተፈቀደው ቦታ ብቻ መደረግ አለበት " በሚል በረቂቁ ላይ የተቀመጠውን ነው።

ለአብነት #የጥምቀት_በዓል የአደባባይ ሃይማኖታዊ በዓል ቢሆንም ፤" ከተፈቀደለት አደባባይ ውጪ መንገዶች ላይ መካሄድ አይፈቀድም " የሚል ትርጓሜ እንዳይሰጠው #ያሠጋል ብለዋል፡፡ 

ሌላው " የሃይማኖት ተቋም የሚይዘው ስያሜ፣ ዓርማ ወይም ምልክት ቀድሞ ከተቋቋመ ተቋም ስም፣ ዓርማ ወይም ምልክት ጋር ተመሳሳይ መሆን የለበትም " በሚል ረቂቁ ላይ የተቀመጠው ነው።

ይህ ፤ " #በከፊልም ሆነ #ሙሉ_በሙሉ ተመሳሳይ መሆን የለበትም " በሚል ሊስተካከል እንደሚገባው ገልጸዋል።

ለዚህ ምክንያቱ " የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ስያሜ የኢትዮጵያ የሚለውን ብቻ በማውጣትና የራሳቸውን በመተካት አገልግሎት ላይ ሲያውሉ የሚታዩ አካላትን ስለተመለከትን ነው " በማለት አስረድተዋል፡፡

2ኛ. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤትን በመወከል የተገኙ ተሳታፊዎች ያቀረቡት ቅሬት ፦

ሃይማኖታዊ ተግባራትን በሚከለክለው የረቂቅ አዋጁ ክፍል " በአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናሎች መፈጸም የተከለከለ ነው " በሚል የቀረበው ሊስተካከል ይገባል ብለዋል።

#ሶላት_የደረሰበት_ሙስሊም በአውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናሎች እንዳይሰግድ መከልከል እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

" በከተሞች ውስጥ ለአምልኮና መቃብር የሚሰጥ ቦታ የከተማውን የዕድገትና የልማት ዕቅድ ወይም ማስተር ፕላን የማይቃረን መሆን አለበት " በሚለው ረቂቁ ላይ ይህ ወደ ተግባራዊነቱ ሲገባ አስቸጋሪ እንደሚሆን ገልጸዋል።

መጀመሪያ የተገነባ ቤተ እምነት " ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር የሚቃረን ነው " በሚል እንዳይፈርስ ዋስትና የማይሰጥ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመንግሥት ተቋማት የሚሠሩ ሠራተኞች ሁሉ እምነት እንዳላቸው፣ ለአብነትም አንድ ሙስሊም በመንግሥት ተቋም ተቀጥሮ ሲሠራ ሶላቱን በሚሰግድበት ወቅት፣ በተቋሙ ውስጥ ሃይማኖታዊ ክንውን አድርጓል ሊባል መሆኑንና ረቂቁ ይህን እንዴት ማስታረቅ እንደሚችል ጥያቄ አስነስቷል፡፡

3ኛ. የወንጌል አማኞች ካውንስል ተወካዮች ቅሬታ ፦

ረቂቅ አዋጁ በወንጌላውያን ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

" በተለይ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ የሚከለክሉ የረቂቁ ክፍሎች፣ ወንጌል መስበክ መሠረታዊ አስተምሯችን ለሆነው ለወንጌላውያን ተቀባይነት ሊኖረው የማይችል ነው " በማለት ተናግረዋል፡፡

ይህ ' መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ' በሚል የተቀመጠውን መርህ የጣሰ እንዳይሆን ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ 

Credit ➡️ Reporter Newspaper

@tikvahethiopia