TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በጋምቤላ_ክልል_የተለያዩ_አካባቢዎች_ከግንቦት_ወር_2015_ለያዩ_ያ_የደረሱ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰቶችን.pdf
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ብቻ እንዲህ ሆኖ ነበር ....

ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦

ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ገደማ በጋምቤላ ከተማ፣ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው እና ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ትክክለኛ ቀኑ ባልታወቀበት ነገር ግን ሰዓቱ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ዶምቦስኮ ትምህርት ቤት አካባቢ አንድ ሰው ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች ተገድለዋል።

ግንቦት 14/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ 01 ቀበሌ ጀጀቤ ወንዝ አካባቢ 2 ሰዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በጥይት ተመትተው ሞተዋል።

01 ቀበሌ ጀጀቤ ተራራ አካባቢ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ገደማ 7 ሰዎች በጥይት ተገድለዋል።

ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ አንድ በአካባቢው ማኅበረሰብ #የአእምሮ_ሕመም እንዳለበት የተገለጸ ሰው 04 ቀበሌ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አካባቢ #በቡድን በተሰባሰቡ ወጣቶች ጥቃት #በስለት_ተወግቶ ተገድሏል።

ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ገደማ 04 ቀበሌ ብሔር ብሔረሰብ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ ፦
* የቀድሞውን የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል፤
* የጋምቤላ ክልል መደበኛ ፖሊስ
* የጋምቤላ ክልል ሚሊሻ መለዮ ልብሶችን የለበሱ እና ሌሎች የታጠቁ ሰዎች በ3 የተለያየ አቅጣጫ በመግባት በቦታው የነበሩ 9 ሰዎችን በጥይት ገድለዋል፤ ሌሎች 4 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት አካባቢ 04 ቀበሌ፣ ቄራ ሰፈር አጉኛ አካባቢ የታጠቁ ሰዎች ወደ አንድ መኖሪያ ቤት በመግባት ተኩስ ከፍተው፤ አንድ ሰው ሲገድሉ በሌላ አንድ ሰው ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰዋል፡፡

የኢሰመኮ ባለ15 ገፅ ሪፖርት ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/85541

@tikvahethiopia