TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'MINDSET'🔝

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ስርጸት ተግባራዊ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት እና በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ዙሪያ ተወዳዳሪ ብሎም ተመራጭ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ አስተሳሰብ ላይ የተመረኮዘ ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው ማህብሰብ መሰጠቱን ገለፀ፡፡

ስልጠናውን ከሀገረ ደቡብ ኮሪያ ተጋብዘው የመጡ አለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ደቡብ ኮሪያውያን ፕሮፌሰሮች መስጠታቸው ነው የተገለፀው፡፡

ስልጠናው #አስተሳሳብ ላይ የተመሰረተ ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት በሚቻልበት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ በስልጠናው የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳዳር እና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር #ጌታሁን_ጋረደው፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአካዳሚክ እና አስተዳደር ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

ደቡብ ኮሪያ እጅግ ደሀ ከሚባሉ ሀገራት ተርታ የምትገኝ የነበረች እና ዜጎቿም ዝቅተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው ነበሩ፣ ነገር ግን ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ዛሬ ላይ ለውጥ ማምጣት መቻላቸውን ስልጠናውን እየሰጡት ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ላይ ደቡብ ኮሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንደስትሪ ግንባታ በመጀመሪያው ተርታ ተሰልፋ ትገኛለች፤ይህ የሆነው ታዲያደቡብ ኮሪያውን ለቀጣዩ ትውልድ እንስራ፣ሳንበገር ተሃምር መፍጠር እንችላለን ብለው እጅ ለእጅ ተያይዘው በቁርጠኝነት በመስራታቸው የመጣ ለውጥ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር ቾ- ሱንግ-ሓዋ ጠቁመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከድህነት ተላቀን ለቀጣዩ ትውልድ #የተሸለች ሀገር ለማውረስ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት ለመሆን በጋራ እንረባረብ ሲል #መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SPHMMC

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በጭንቅላት ውስጥ አላስፈላጊ ውሃ መጨመር (Hydrocephalus ) እና የጀርባ የአፈጣጠር ችግር (spina bifida)ችግር ያለባቸውን ሕጻናት ከየካቲት 9 ቀን ጀምሮ ነጻ ህክምና እንደሚሰጥ ገልጿል።

ለህክምናው ወላጆች ልጆቻቸውን በ976 በመደወል አንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

#መልዕክቱን_ለሌሎች_ያድረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

በጢስ አባይ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሚካሄደው ጥገና ምክንያት የጢስ አባይ ፏፏቴ ውሃ ከነገ የካቲት 27/2013 ዓ/ም ጀምሮ መጠኑ ጨምሮ ስለሚለቀቅ ከፏፏቴው ግርጌ በሚገኙ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተብሏል።

#መልዕክቱን_ለሌሎች_ያድረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia