TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia #ፍትሕ

በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ የተገደለችው የ7 ዓመቷ ህጻን ሔቨን ታሪክ የበርካቶችን ልብ የሰበረ ጉዳይ ሆኗል።

ይህ ድርጊት የተፈጸመው ከዛሬ #አንድ_ዓመት በፊት በባህርዳር ከተማ እንደሆነ ዛሬም ድረስ መሪር ሀዘን ውስጥ የምትገኘው እናት " ኢዮሃ " በተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቀርባ ተናግራለች።

ህጻን ሔቨን የተደፈረችው ተከራይተው ይኖሩበት በነበረ ግቢ አከራይ ነው።

የተደፈረችበት መንገድም ወደ ሽንት ቤት በምትሔድበት ጊዜ ጠብቆ ወደ ቤት በማስገባት ነው። እጅግ በጣም አሰቃቂም ነበር።

ህጻን ሔቨንን የደፈረው ወንጀለኛ በምትደፈርበት ወቅት አንገቷን አንቆ ፤ አፏን አፍኖ ድርጊቱን የፈጸመ ሲሆን ወድቃ የሞተች ለማስመሰል ደሟን አንጠባጥቦ በር ላይ ጥሏት መሄዱን እናት ታስረዳለች።

እናት ልጇን ብቻ አይደለም ያጣችው ፤ ፍትህ ስትጠይቅ ይህንን ግፍ ሰምተው እንዳልሰማ የሆኑ ጎረቤት እና ቤተሰቦች ፤ በጥቅም ወንጀለኛውን ነጻ ለማስወጣት የሰሩ ፤ እናትን ጭምር ተባብረው ለማጥፋት ረጅም ርቀት የተጓዙ ፤ ማስፈራሪያ ደርሷቸው ቃላቸውን ከመስጠት የጠፉ ሁሉ ለእናት ፈተና ሆነውባታል።

ይህም ሆኖ ጥቂት የሚባሉ (የሴቶች እና ህጻናት ወንጀል መሪማሪ ፖሊሷ፤ የሴቶችና ህጻናት ቢሮ) አንዳንዶቹ ማስፈራሪያ ጭምር እየደረሳቸው አግዘዋት ከብዙ መከራ በኋላ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ይፈረድበታል።

እናት ግን ዛሬም ትኩስ ሀዘን ላይ ነች።

ሥራ እየሰራች መኖር አልቻለችም።

ነገ ከእስር ሲለቀቅ እሷንም ጭምር ለመግደል እንደሚፈልግ ፤ ለዚህም ደግሞ ዳግም ሥራ ከጀመረችበት ቦታ ቤተሰቦቹ ተከታትለዋት ጥላ መውጣቷን እናት አስረድታለች።

ዛሬም እውነተኛ ፍትሕ አጥታ ትንከራተታለች።

ግፍ ላይ ግፍ !

በመሰረቱ በዚህች ምስኪን አንድ ፍሬ ፤ ክፉ ደግ በማታውቅ ህጻን ላይ አሰቃቂ የመድፈር እና ኃሏም ህይወቷን ያሳጣ የወንጀል ድርጊት የፈጸመ ሰው እንዴት 25 ዓመት ይፈረድበታል ? እውነት ይህ ማስተማሪያ ነው ? ወይስ ሌላ ነው ዓላማው ?

የሔቨን ታሪክ የብዙ ህጻናት ታሪክ ጭምር ነው።

ከዚህ በፊት ሴቶች፣ ህጻናት ጭምር ሲደፈሩ የሚተላለፉ የፍርድ ውሳኔዎች ህዝቡን እያስቆጣ መሆኑን አሳውቀን ነበር።

ዛሬም ፍትሕ ተጓድሏል። ፍትሕ ይስፈን።

ዛሬ አጋጣሚ ይህ ጉዳይ አደባባይ ወጣ እንጂ ስንቷ እናት ቤቷ ዘግያ እያለቀሰች ይሆን ? ስንት ሴቶች በግፍ ሰለባ ሆነው እያነቡ ይሆን ?

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፍትሕ

በሀገራችን በተደጋጋሚ ጊዜ ሴቶች ፣ ትንንሽ ህጻናት ሳይቀሩ ይደፈራሉ ፤ ይገደላሉ የሚሰጠው ፍርድ ግን " እውነት ፍርዱ ለማስተማር ነው ? ፍትሕ ለማስፈን ነው ? " የሚል ጥያቄ የሚያስነሳና እጅግ በጣም አስደንጋጭ ጭምር ነው።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ፥ መቼም ስለ ሚደፈሩ ሴቶች ፤ ደጉን ከክፉ ያለዩ ምንም የማያውቁ ህጻናት ሳይቀሩ ስለሚፈጸምባቸው አሰቃቂ ግፍና ወንጀለኞች ላይ ስለሚተላለፉት ፍርዶች ብዙ ጊዜ መረጃ ስንለዋወጥ መቆየታችን ይታወሳል።

ለአብነት በቅርብ ወራት እንኳን ፦

- " የ11 ዓመቷን ልጅ የደፈረው አባት 16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ። "

- " አንገቷን አንቆና አፏ ውስጥ ጨርቅ ጠቅጥቆ የ14 ዓመቷን ልጅ የደፈረው እና ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በ19 ዓመት ተቀጣ። "

- " የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት በ6 ወር እስር ተቀጣ። "

- " የ10 አመቷን ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። "

- " የ4 አመቷን ህጻን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ። "

- " የ8 አመት ህፃናትን አስገድዶ የደፈረው የ41 አመት ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። "

- " እጅግ አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ ሁለት የ16 እና የ17 ዓመት ልጆቹን በአልኮል አደንዝዞ አስገድዶ የደፈረው አባት በ21 አመት ተቀጣ። "


የሚሉ እነዚህን መረጃዎች በቲክቫህ ገጻችሁ ላይ አንብባችኋል።

ይኸው ዛሬ ደግሞ ጆሮን ጭው ፤ ልብን ቀጥ የሚያደርግ የባህር ዳሯን የ7 ዓመት ህጻን ሔቨንን ጉዳይ ሰማን።

ህጻን ሔቨን ላይ እጅግ አሰቃቂ የመድፈር እና የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ 25 ዓመት እንደተፈረደበት ተሰማ።

ጭራሽ ይህም እንዳይሆነ የግለሰቡ ቤተሰቦች፣ ጎረቤቶች ፣ አንዳንድ የፖሊስ አባላት ፣ ከፍትህ አካላት ጭምር ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

በሔቨን ጉዳይ በርካቶች ልባቸው ተሰብሯል ፤ ተቆጥተዋል። የመንግስት አካላትም ስለ ጉዳዩ ፊት ለፊት ወጥተው ተናግረዋል።

እናት የፍትሕ እያለች ነው። ለፍትሕ እያነባች ነው።

የግለሰቡ ቤተሰቦችም #እህቱን ጨምሮ ስራ የምትሰራበት ቦታ ድረስ ተከታትለዋት መቀመጫ መቆሚያ አሳጥተዋት ስራ እንድትልቀ አድርገዋል።

ከፍርዱ በፊትም ብዙ ማስፈራሪያ ሲደረግባት ነበር። ኃላም እንደዛው።

ማስፈራሪያ እና ክትትሉ ብዙ ጊዜ ቤት እንድትለቅ አድርጓታል።

ዛሬም ለቅሶ ላይ ናት። እናት ዛሬም የፍትሕ ያላህ ትላለች።

" የት እንሂድ እንግዲህ ? ወይ ሌላ ሀገር የለን ? ለማን እንናገር ? ማንስ ይሰማናል ? የእውነት አምላክ እሱ ይፍረድ ነው " ቃሏ።

የሔቨን ጉዳይ የብዙዎች ነው።

የእናቷ አንባ የብዙዎች ነው።

ስንት እናቶች ናቸው ይሁኑ እውነተኛ ፍርድና ፍትሕ አጥተው ቤታቸውን ዘግተው እያለቀሱ ያሉት ?

መሰል ጉዳዮች ሰሞነኛ ጉዳይ እየሆኑ እያለፉ ነው።

አንድ ሰሞን ይወራል ከዛ ይተዋል። በቃ ሊባልና መፍትሄ ሊፈለግ ይገባል።

የወንጀለኞቹ መታሰር የልጆቻችንን  ህይወት እንኳ ባያስመልስም ትክክለኛ ፍርድ ግን ቢያንስ እንባ ያብሳል። ሌላውን ያስተምራል። አሁን እየሆነ ያለው ያ አይደለም።

ፍትሕ ይስፈን !
አስተማሪና ሀቀኛ ፍርድ ይፈረድ !
ፍትሕ ! እውነተኛ ፍትሕ ለተነፈጉ በርካታ ሴቶች፣ እናቶች ፣ ህጻናት !

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Infinix_Note40_Pro_Plus

ኢንፊኒክስ ኖት 40 ፕሮ ፕላስ 5G የ100 ዋት ፈጣን የገመድ ቻርጅ ያለው ሲሆን የገመድ ቻርጀር ባይኖሮትም አያሳስብም! ምክንያቱስ ካሉ ባለ 20 ዋት ገመድ አልባ የቻርጂንግ ቴክኖሎጂን ይዞ ብቅ ብሏል!!

#Note40Et #Note40Pro #Note40 #Note40ProPlus #InfinixEt
#DStvEthiopia

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጀመረ💥

⚽️ማን ሲቲ ከኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ በኋላ የዓመቱን የመጀመሪያ 3 ነጥብ ለማሸነፍ ይጫወታል!

🏆 በስታንፎርድ ብሪጅ ስታዲዮም ቼልሲ ከማንሲቲ ጋር የሚያደርጉትን ፍልሚያ ዛሬ ከምሽቱ 6፡30 ሰዓት በSS Premier League እና SS Liyu ቻናል በሜዳ ፓኬጅ በቀጥታ ይከታተሉ!

አሁኑኑ ደንበኝነትዎን  ወደ ሜዳ ያሳድጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት በቀጥታ ይከታተሉ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ሁሉምያለውእኛጋርነው 
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray🚨 " የጊዚያዊ አስተዳደሩን ስልጣን ለመንጠቅ የመሞከር እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንትና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዛሬ ነሀሴ 11/2016 ዓ.ም መገለጫ ሰጥተዋል። በጋዜጣዊ መግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ምንድናቸው ? - የህወሓትና ሌሎች ህገ-ደንቦች ያላሟለና ተጨባጭ የትግራይ…
#Tigray

" ጊዚያዊ አስተዳደር ተቆጥረው የተሰጡት ስራዎች አሉት ፤ ስራዎቹን ፍፅሞ ስልጣኑ ያስረክባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ትናት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ ከነሀሴ 9 አስከ 11/2016 ዓ.ም  " ትግራይ ከአስከፊውና ደም አፋሳሽ  ጦርነት ወደ ከፍታ ወይስ ወደ ብዥታ ጉዞ !! " በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ የመዝግያ ስነ-ስርዓት ተገኝተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ " በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት ማበብ አለበት ፤ የተለየ ሃሳብ ያቀረበ እንደ ጠላትና አፍራሽ አድርጎ ማሰብና መፈረጅ መቆም አለበት " ብለዋል።

" አሁን ላይ ትግራይ ውስጥ በመታየት ላይ ያለውን ተስፋ አስቆራጭ የሚመስል ሁኔታ ከትግራይና ከትግራዋይ የመፈፀም አቅም በታች ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ችግሮቹ ይፈታሉ " በማለት ተናግረዋል። 

" ፈረንሳዮች ' ልዩነት ለዘልአለም ይኑር ! ' የሚል የሃሳብ ብዙህነት እንደ ዳበረ ባህልና ልምምድ የሚቆጥር አባባል አላቸው ይህንን አባባል እንደ ጥሩ ልምድ በመቅሰምና በመተግበር በሃሳብ ልዩነት የሚያምን የሰለጠነ ፓለቲካዊ ባህል ማጎልበት አንዱ የመልካም አስተሳብና የእድገት መለኪያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው " ብለዋል።

" ጊዚያዊ አስተዳደሩ ሃላፊነት ላይ ሲቀመጥ ፦ 
- ሰላም ፍትህና ፀጥታ እንዲያረጋግጥ
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው መልሶ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲያስከብር 
- የትግራይ መልሶ ግንባታ አስመልክተው የሚካሂዱት እንቅስቃሴዎች እንዲመራ
- ለቀጣዩ ምርጫ ምቹ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታ እንዲፈጥር የሚሉ ተግባራት ለመስራትና ለመፈፀም ነው " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " እነዚህ ተቆጥረው የተሰጡት ሰራዎች ፈፅሞ ስልጣኑ ያስረክባል " በማለት አክለዋል።

በመካሄድ ያለው የህወሓት 14 ኛው ጉባኤ ትናነት ነሀሴ 11/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፥ " በህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ስም ማንኛውም ፓለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም " ብሏል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ጉባኤው በማካሄድ ላይ የሚገኘው " የህወሓትን ደንብና አሰራር በጣሰ ቡድን " ብለው " የጊዚያው አስተዳደሩ ስልጣን ለመንጠቅ የመሞከር እንቅስቃሴ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን " ማለታቸው ይታወሳል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ  " የድርጅቱ ህገ-ደንብና አሰራር በጣሰ ጉባኤ አልሳተፍም ያለው "  በእነ አቶ ጌታቸው የሚመራው የህወሓት ሃይል ዛሬ ነሀሴ 12/2016 ዓ.ም በመቐለ የውይይት መድረክ ጠርቶ ውይይት እያካሄደ ነው።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray " ጊዚያዊ አስተዳደር ተቆጥረው የተሰጡት ስራዎች አሉት ፤ ስራዎቹን ፍፅሞ ስልጣኑ ያስረክባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ ትናት የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፤ ከነሀሴ 9 አስከ 11/2016 ዓ.ም  " ትግራይ ከአስከፊውና ደም አፋሳሽ  ጦርነት ወደ ከፍታ ወይስ ወደ ብዥታ ጉዞ !! " በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የትግራይ ሙሁራን ማህበር ያዘጋጀው የውይይት መድረክ…
#አሁን : በመቐለ ከተማ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ በወቅታዊ የህወሓት የፓለቲካ ሁኔት ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ መድረኩ ላይ " 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ህጋዊ አይደለም " ብለው የተቃወሙ ፦
➡️ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ፣
➡️ የድርጅቱ የማእከላዊ ቁጥጥር ኮሚሽን ፣
➡️ የክልል ፣ የዞን ፣ የወረዳና ሌሎች አመራሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።

የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበር ጌታቸው ረዳ፥ " የውይይት መድረኩ ህወሓትን ለማዳንና ትግራይን ወደ ነባራዊ ሁኔታዋ ለመመለስ ወሳኝ ነው " ማለታቸውን ከድምጺ ወያነ ቴሌቪዥን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ተጨማሪ ይኖረናል።

የፎቶ ባለቤት ፦ ድምጺ ወያነ

@tikvahethiopia
#ዮናታን_ቢቲ_ፈርኒቸር
Yonatan BT Furniture

ከ15% እስከ 20% ቅናሽ የተደረገባቸውን የተለያዩ የቤት ዕቃዎች እድሉ ሳያመልጥዎ አሁኑኑ ይግዙ!
የውበት እና የጥራት ዳር ድንበር!

አድራሻችን፦
1.ዊንጌት አደባባዩን ተሻግሮ: +251995272727
2.ፒያሳ እሪ በከንቱ : +251957868686
3.ሲ ኤም ሲ አደባባዩን አለፍ ብሎ: +251993828282

👉 Telegram:  https://t.iss.one/yonatanbt_furniture
👉 Facebook:  https://www.facebook.com/profile.php?id=100087238034736
👉 Instagram: https://www.instagram.com/yonatanbtfurniture/
👉 TikTok: https://www.tiktok.com/@yonatanbtfurniture
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ሞጆ ቅርንጫፍ እየተጉላላን ነው። ትላንት የተላከውን ደብዳቤ ስራ አስኪያጅ ‘አልመራበትም’ ተብሎ ” - አስመጪዎች “ ደብዳቤው ትላንትና ከመሸ ነው እኛ ጋ የደረሰው ከዋና መስሪያ ቤት፡፡ ተመርቶ ለሚመለከተው ክፍል ሰጥጠናል ” - ሥራ አስኪያጅ ክፍሉ አስመጪዎች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በጉምሩክ እያጋጠማቸው ስላለው ሁኔታ ፤ ክፈሉ ስለተባሉትም ከፍተኛ ቀረጥ በተመለከተ ለቲክቫህ…
#ጉምሩክ

" ሰርኩለሩ በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " - አስመጪዎች

በርካታ የመኪና አስመጪዎች ከጉምሩክ አሰራር ጋር በተያያዘ ቅሬታ እንዳላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አስመጪዎቹ በጋራ ፈርመው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባላኩት ደብዳቤ ፤ " መንግስት በሀምሌ 22/2016 ዓ.ም በስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ ያስተላለፈው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከዚህ በፊት የነበሩ ውስብስብ የንግድ መዛባቶችን እና ብሮክራሲዎችን እንደሚያስቀር እንተማመናል " ብለዋል።

ነገር ግን የኢፌዲሪ ጉምሩክ ኮሚሽን ነሐሴ 03/2016 እና ነሐሴ 10/2016 ያወጣቸው ሰርኩላሮች ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

" ይህም ሰርኩላር ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ከግምት ውስጥ ያላስገባ እና ከጉምሩክ ትራንዚት እና መጋዘን አስተዳደር የሚጣረስ በመሆኑ ነው " ብለዋል።

አስመጪዎቹ " የኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር FXD/01/2024 ተከትሎ የጉምሩክ ኮሚሽን ከ22/11/2016 በፊት የተመዘገቡ እና ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች ላይ በደብዳቤ ቁጥር 4/0/04/17 ነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ/ም ስርኩለት የተላከ ሲሆን ነገር ግን ሰርኩለር በዩኒ ሞዳል ተጓጉዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገባ እቃዎች ግምት ውስጥ ያላስገባ " ነው ብለዋል።

ጉዳዩን ሲያብራሩም ፦

" በጉምሩክ ደንቡ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው የቀረጥ ማስከፈያ የሚወሰነው ዲ/ዬን. በተመዘገበበት እለት ያለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ተመን በመጠቀም ነው።

ይህ ማለት በዮኒሞዳል አሰራር ሕጋዊ ዶክሜንት አሟልተን ዲ/ዬን ሞልተን ክፍያ ፈፅመን ሰነዱን የተሟላ መሆኑን ለጉምሩክ ኦፊሰር ተረጋግጦ ትራንዚት ተፈቅዶልናል፡፡

ትራንዚት ካስፈቀድን በኋላ ደግሞ ሕጉ በሚፈቅደው በአንድ ወር የትራንዚት ጊዜ ገደብ ውስጥ ኘሮሰስ ጨርሰን እቃዎቹን ወደ አገር ውስጥ አስገብተናል የጉምሩክ ሪስክ የሚጣለው ደግሞ እቃዎቹ አገር ውስጥ / መድረሻው ጣቢያ / ሲደርሱ መሆኑን ከግምት ያላስገባ ውሳኔ ነው።

እቃዎቹ ተጓጉዘው በድሬዳዋ መስመር /ደወሌ/ ለሚገቡ በድሬዳዋ ድልድይ ተሰብሮ ከ3 ሳምንት በላይ መቆማቸው ግምት ውስጥ ያላስገባ ውሳኔ ነው " ብለዋል።


" የጉምሩክ ኮሚሽን ከላይ የተገለጸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአስቸኳይ የውሳኔ ማሻሻያ እንዲደረግልን እና በአዋጁ መሰረት እንድንስተናገድ " ሲሉ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ፤ " ጉምሩክ  ኮሚሽን አዋጅን በሴኩላር በማሻር የማይሆን ስራ እየሰራ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀረቡ አስመጪዎች አሁንም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሴኩርላር ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም።

አሁንም ማሻሻያ እንደሚያስፈልግ አስገንዘበዋል።

ጉዳዩ  በገበያና ስራው ላይ ሚያመጣውን ከፍተኛ ተፅእኖ በመረዳት እውቀትን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ በውይይት መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#Customs #Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ  በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት…
የእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ጉዳይ የት ደረሰ ?

የባህር ዳር ከነማው የመሀል ሜዳ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከወራት በፊት አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ " የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ያለው የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ " ጉዳዩን በፍጥነት በማጣራት በቅርብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የደረስኩበትን አደርሳለሁ " በማለት ቃል ገብቶ ነበር።

ይሁንና በጉዳዩ ላይ ሀምሌ ወር ውስጥ መግለጫ ይሰጣል መባሉ በተጨማሪ ለእስር የተዳረጉት የተጫዋቹ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውን ተከትሎ ጉዳዩ የት ደረሰ ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ያቀረበለት የጋሞ ዞን ፍ/ቤት ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት አለመመራቱንና ክስ ባልተከፈተበት በጉዳዩ ላይ መረጃ መስጠት እንደማይችል ገልጾልናል።

ይህንንም ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ጉዳዩን እንደያዙትና ከምርመራ በኋላ የተደረሠበትን ጉዳይ ለህዝብ እንደሚያደርሱ ቃል የገቡልን በወቅቱ የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩትን ኢንስፔክተር አብርሀምን አነጋግረናቸው ነበር።

አዛዡ በወቅቱ የሟችን ቤተሰቦች በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያካሄዱ እንደነበር አስታውሰው አሁንም ጉዳዩ ምርመራ ላይ እንደሆነ በመግለጽ ከቦታው በመነሳታቸው እንዲሁም የፖሊስ አሰራር በዚህ ሰአት መረጃ መስጠትን ስለሚከለክል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አሁንም ይከታተላል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia