TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PASSPORT

- የመደበኛ ፓስፖርት እድሳት እና አዲስ ጥያቄ ከጥቅምት 2/2013 ጀምሮ በሁሉም የኤጀንሲው (INVEA) የክልል ቅርንጫፍ ቢሮዎች አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፤

- በአዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ፤

- በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት በጥቅምት 10/ 2013 ይጀምራል፤

- ለውጭ አገር ዜጎች በOnline ቪዛ የማራዘም እና ግዜያዊ መኖሪያ ፍቃድ የማደስ እና አዲስ የመጠየቅ አገልግሎት ጥቅምት 2/2013 ይጀምራል፤

- የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እድሳትና ጥያቄ መደበኛ አገልግሎት ከጥቅምት 2/2013 እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- የኢማግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

ከነገ ጥቅምት 10/2013 ጀምሮ በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ይጀምራል።

*አዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ። (INVEA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PASSPORT ከነገ ጥቅምት 10/2013 ጀምሮ በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ይጀምራል። *አዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ። (INVEA) @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባጋጠመው የኔትወርክ ችግር ምክንያት የኦንላይን (online) አገልግሎቱን ዛሬ ጠዋት መጀመር እንዳልተቻለ ለ 'ኢትዮጵያ ቼክ' ገልጿል።

አገልግሎቱ ከሰአት አካባቢ ይሰራል ተብሎ እንደሚጠበቅና ፣ ስራው ሲጠናቀቅ አገልግሎቱ ማግኘት የሚቻልበት ሊንክ ይፋ እንደሚደረግ ኤጀንሲው አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት አመልካቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

1. ይህን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሰነዶች ማዘጋጀት ፦

• ህጋዊ የቀበሌ መታወቂያ ካርድ
• የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት/ማስረጃ

2. የሚያመለክቱት ለአስቸኳይ አገልግሎቶች ከሆነ ከሚከተሉት መካከል ቢያንስ አንዱ ሊኖርዎት ይገባል ፦

• የሕክምና ደብዳቤ
• የትምህርት እድል እና ዲቪ
• ከተፈቀደለት ድርጅት የተጻፈ ደብዳቤ
• የውጭ ሀገር የነዋሪነት ፍቃድ
• የግብዣ ደብዳቤ
• አስቸኳይ የስራ ጉዞ
• በሀዘን/ጋብቻ ምክንያት የሚደረግ ጉዞ

3. ለአዲስ ፓስፖርት የሚከፈለውን ክፍያ ያረጋግጡ ፦

• ለ32 ገጽ ፓስፖርት - 600
• ለ64 ገጽ ፓስፖርት - 2186 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍላችሁ online አድራሻ ላይ አባሪ ያደርጉታል።

አድራሻ እስኪገለፅላችሁ በትዕግሥት ጠብቁ።

የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
ጥቅምት 10/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PASSPORT

በOnline ላይ ፖስፖርት ለማደስና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ጥቅምት 11 ይጀምራል ቢባልም ዛሬም ድረስ አልተጀመረም።

ውድ የቲክቫህ አባላት የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የኦንላይን (online) አገልግሎቱ የሚሰጥበት 'ሊንክ' ይፋ ሲያደርግ ተከታትለን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

www.ethiopianpassportservices.gov.et

ኦንላይ (online) ላይ ፖስፖርት ለማደስና ለአዲስ ፖስፖርት አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ አገልግሎትን ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጠቁሙ👇

www.ethiopianpassportservices.gov.et

ደንበኞች በፕላትፎርሙ ላይ የሚገጥማቸው ጉዳይ ዘውትር በ [email protected] ላይ እና በስራ ሰዓት በ8133 ነጻ የስልክ መስማር ላይ INVEA ማሳወቅ ይችላሉ።

ተጨማሪ ፦

- ፓስፖርት ለማሳደስ ማሟላት ስላለባችሁ መስፈርት ይህ ተጭናችሁ ተመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/53852

- ፓስፖርት ለማግኘት ማሟላት ስላለባችሁ መስፈርት ይህን ተጭናችሁ ተመልከቱ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/53851

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

በአዲስ አበባ ከዛሬ ህዳር 1 ቀን/2013 ዓ/ም የፓስፖርት አገልግሎት የሚጀምር መሆኑ ይታወቃል።

ሆኖም ለአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት ካልሆነ በስተቀር online www.ethiopianpassportservices.gov.et በሚል ሊንክ ገብታችሁ ቀጠሮ ሳትይዙ ወደኤጀንሲው ዋናው መ/ቤት በአካል እንዳትመጡ ተብሏል።

ከ08/2013 ዓ/ም በሗላ ቀጠሮ ሳትዙ በአካል መምጣት እንደሌለባችሁ የተገለፀ ሲሆን ቀጠሮ በ online ላይ ይዞ ለማይመጣ ተገልጋይ አገልግሎት እንደማያገኝ ተገልጿል።

በክልል ቅርንጫፍ የምትገለገሉ ተገልጋዮች በ online እና በአካል መገልገል ትችላላችሁ ተብሏል።

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
ህዳር 1 ቀን 2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በዋናው ዳታ ቤዝ ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት ለጊዜው ማቆሙን ገልጿል።

ደንበኞች የተቋረጠው አገልግሎት #በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈቶ ወደ ቀደመ አገልግሎቱ እንስኪመለስ በትእግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ኤጀንሲው ካጋጠመው የሰርቨር ችግር ውጪ በድረ-ገጽ አማካኝነት የሚሰጠው የፓስፖርት አገልግሎት አልተቋረጠም ብሏል።

በኤጀንሲው ዋና ሰርቨር ላይ ያጋጠመው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በኤጀንሲው ድረገጽ ላይ በመግባት ቀጠሮ ማያዝ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ያጋጠመውን ችግር ዛሬ ወይንም ነገ አልያም በመጪዎቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለመፍታት እተየሰራ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የፓስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኤጀንሲው ደንበኞች አገልግሎቱን ከዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ማግኘት እንደሚችሉ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Passport

ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ አስቸኳይ ፓስፖርት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው።

የኢሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በማንሳት፣ ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲያገኙ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቅድመ ሁኔታዎች ሲነሱ አሁኑ ላይ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት ተገልጋዮች ማቅረብ ሚጠበቅባቸውን የሕክምና ደብዳቤ ፣ ነፃ የትምህርት ዕድል ማስረጃ... የመሳሰሉትን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፡፡

በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት በፀደቀው የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ፓስፖርት በአንድና በአምስት ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት የተቀመጠውን ክፍያ " መክፈል የቻለ ሁሉ " ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ግንበቶ መናገራቸውን ሪፖርተር ገልጿል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

- #በአስቸኳይ_ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ለማንሳት ዝግጅት እየተደረገ ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጡ ከሙስናና ከብልሹ አሠራር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡

- " አስቸኳይ ፓስፖርት ከውስጥ ሠራተኞች ተነጋግረን እናስጨርሳለን " የሚሉ ደላሎች አሉ ከብልሹ አሠራሮች ጋር በተያያዘ ፣ በዓመት ግፋ ቢል ከ50 ሰዎች በላይ እያባረርን ነው። ከአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ያስችላል ተብሎ የታሰበው መፍትሔ አገልግሎቱን ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማንሳት ነው።

- አሁን ባለው አሠራር ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት ከሚያስችሉ ማስረጃዎች መካከል ፦

• ወደ ውጭ ሄደው መታከም እንዳለባቸው የሚገልጽ የሕክምና ደብዳቤ ፣
• ለሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆነ የትምህርት ዕድል ማግኘትን የሚገልጽ ደብዳቤ
• የዲቪ ሎተሪ ዕድል ማግኘትን የሚያሳይ ማስረጃ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተነስተው ሥራ ሲያስጀምር ደንበኞች የሚስተናገዱት በአዲሱ የክፍያ ተመን ይሆናል።

- ቅድመ ሁኔታዎችን አንስቶ አገልግሎቱን ለመጀመር ጥናት ተጠንቷል፤ ይህንን አገልግሎት ለማስጀመር የፓስፖርት ወረቀት ፣ ላምኔት ፣ የማተሚያ ቀለም እና የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ መለዋወጫዎችን ... የመሳሰሉ ግብዓቶች መሟላት እንዳለባቸው በጥናቱ ታይቷል።

የሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት የኦንላይን ፓስፖርት ቡድን መሪ አቶ ዳንኤል የሻነው ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

• በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሰጥባቸው መስኮቶች ሁለት ናቸው የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎትን ያለገደብ ለማስጀመር እንዲቻል ቢያንስ ስድስት መስኮቶች መኖር አለባቸው።

• አገልገሎቱን ለማስጀመር ሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጀምሯል ፤ ምን ያህል ብር እንደሚጠይቅም አዘጋጅተን ለሚመለከተው ክፍል አቅርበናል።

• አገልግሎቱ እንዲጀመር ተጨማሪ በጀት ይጠይቃል ፤ በጀቱ የሚፈቀድልን ከሆነ #በቅርብ_ወራት ውስጥ ይኼንን አስጀምረን አገልግሎት አሰጣጡን እናሻሽላለን።

አሁን ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት ክፍያና የሚሻሻለው ክፍያ ምን ይመስላል ?

አሁን በሥራ ላይ ባለው አሠራር መሠረት ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት 2,186 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ ይኼንኑ ፓስፖርት በሁለት ቀናት ውስጥ ለማግኘት 3,279 ብር ክፍያ ይፈጸማል፡፡

በቅርቡ በሥራ ላይ መዋል ይጀምራል የተባለው አዲስ የአገልግሎት ክፍያ ተመን በ5 ቀናት ውስጥ ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠየቀውን ገንዘብ ወደ 5,000 ብር አሳድጎታል፡፡

ፓስፖርቱን በአንድ ቀን ለማግኘት ደግሞ 6,500 ብር ክፍያ መፈጸም እንዳለበት ደንቡ ያስረዳል፡፡

የባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ ለማግኘት 6,500 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ በአንድ ቀን ለማግኘት የሚከለፈለው ክፍያ 8,000 ብር ይደርሳል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ (ethiopianreportr.com)

@tikvahethiopia
#Passport

የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ተገልጿል።

የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ገልጿል።

ፖስፖርት ለማደስ 5 ዓመት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ከአንድ ወር በኃላ ወደ ሥራ በሚገባው አሰራር መሰረት ግን ከ25 ዓመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች በየ10 ዓመቱ እንደሚታደስ አገልግሎቱ ገልጿል።

#ICS #AHADU

@tikvahethiopia