TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቁልቢ

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ አሳውቋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ እና የበዓሉ የጸጥታ ኮማንድ በመጪው ረቡዕ በሚከበረው ዓመታዊ የቁልቢ ንግስ በዓል ላይ ከተለያየ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ብዛት ያላቸው ምዕመናን፣ ቱሪስቶችና ሌሎችም እንግዶች ወደ ስፍራው እንደሚመጡ ይጠበቃል ብለዋል።

የምዕመናኑን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅም ከምዕራብ ሐረርጌ ዞን ፣ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ ከሐረሪ ክልል እና ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከመከላከያ ሠራዊት፣ ብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ጋር በመቀናጀት ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

የበዓሉ ታዳሚዎች የግል ንብረቶቻቸውን እንዳይሰረቅ በጥንቃቄ በመያዝና የወንጀል ድርጊት ሲመለከቱ በማጋለጥ የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው ተብሏል።

በንግስ በዓሉ ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያና ተጠርጣሪ ወንጀለኞችም ሲያዙ ውሳኔ ለመሰጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።

ወደ ስፍራው በሚያመራው መንገድ አልፎ አልፎ ያለው አካባቢ የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ በማክበር አደጋን ለመከላከል የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

ከዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ #ከባድ_መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑንም ተገልጿል።

ምዕመናን ወደ ንግስ ስፍራው በሚመጡበት ወቅት ተገቢነት የሌላቸው አርማና ምልክቶችን ይዘው መገኘት እንደሌለባቸውም ፖሊስ አሳስቧል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia