TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Alert🚨

የዝንጀሮ ፈንጣጣ (MPox) የዓለም አቀፍ አሳሳቢ የህዝብ ጤና ደኅንነት ስጋት (PHEIC) እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወሰኑ።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) እና በአፍሪካ የሥርጭት መጠኑ እየጨመረ መምጣቱን አሳውቀዋል።

ከዚህ ባለፈ፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣን የአፍሪካ ሲዲሲ የህብረተሰብ ጤና አህጉራዊ ደህንነት ስጋት እንደሆነ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የተያዘ ሰው #አለመኖሩን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ አመልክቷል።

በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እና ሞያሌን ጨምሮ በሌሎች የመግቢያ ቦታ ላይ የቁጥጥርና ማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

በሽታው እስካሁን በ13 የአፍሪካ ሀገራት መከሰቱን እንዲሁም፣ 2,863 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው እና 517 ለህልፈት መዳረጋቸዉ መረጋገጡን የአፍሪካ ሲዲሲ መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia