#Afar ⛈
ከትላንትና በስቲያ ፤ በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ ከምሽት 1 ሰዓት አንስቶ ለሊቱን ሙሉ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተለያዩ የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።
የክልሉ አደጋ መከላከልና ስጋት አመራርና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ ሀሙስ ከምሽቱ 1 ሰአት ጀምሮ ሌሊቱን ሙሉ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት ፦
👉 13 ሺህ 834 ፍየል እና በግ፣
👉 180 የቀንድ ከብት፣
👉 20 ግመሎች እና 3 አህዮች ሞተዋል።
በክልሉ ባለዉ ድርቅ የቤት እንስሳዎቹ በመኖ እጥረት የተጎዱ በመሆናቸዉ ዝናቡን መቋቋም አለመቻላቸው አደጋውን የከፋ አድርጎታል ተብሏል።
በወረዳው ደርጌራ ፣ አፉማና ወአማ ቀበሌዎች በዝናቡ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
የቤት እንስሳቶቻቸው ለሞቱባቸው ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።
የጭፍራ ወረዳ አርብቶ አደር ጽ/ ቤት በበኩሉ ፤ ከወረዳዉ ስፋት ጋር በተያያዘ ገና መረጃ እየተሰበሰበ የሚገኝ በመሆኑ የሞቱ የቤት እንሰሳዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ለኢዜአ ገልጿል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከግንቦት 15 እስከ 20/2014 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሰመራ እና አጋቲና ካምፖች በመባል በሚታወቁ ቦታዎች ውስጥ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ " ለደኅንነታቸው ጥበቃ እና በወንጀል ጥርጣሬ የሚፈለጉ ሰዎችን ለመለየት " በሚል ምክንያት ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ከሆኑ 3 የአፋር ክልል ወረዳዎች ፦ - ከአባላ - ከኮነባ - ከበረሃሌ…
#Afar
በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ በሚገኝ የማቆያ ካምፕ ውስጥ #ያለፈቃዳቸው ተይዘው ከነበሩት የትግራይ ተወላጆች መካከል የተወሰኑት በአውቶብሶች እና የደረቅ ጭነት መኪኖች ተሳፍረው ወደ ቀደመ መኖሪያቸው እየተወሰዱ እንደሆነ መግለፃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።
በሺዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ተወላጆች ከአፋሯ አብኣላ ተይዘው ወደ ሰመራ ተዘዋውረው የነበረ ሲሆን ከ8 ወራት እስር በኋላ ወደ አብኣላ እየተመሰሉ መሆኑን ተናግረዋል።
በሰመራ ተይዘው የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን "በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል ብሎ ነበር።
https://t.iss.one/tikvahethiopia/71528?single
የትግራይ ተወላጆቹ ቀደሞ ወደሚኖሩበት የመኖሪያ ስፍራቸው እንዲመለሱ እያመቻች የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት (OCHA Ethiopia) መሆኑ የተነገረ ሲሆን ድርጅቱ ሰዎቹን " የአገር ውስጥ ተፈናቃይ (IDP) " ሲል ገልጿቸዋል።
ዜጎችን ወደነበሩበት ቦታ የመመለሱ ስራ በሚቀጥሉት ሳምንታት እንደሚቀጥልም ገልጿል።
ነገር ግን ተመድ ባሰራጨው መረጃ ላይ በርካቶች በቃል አጠቃቀሙ ላይ ያለቸውን ተቃውሞ የገለፁ ሲሆን እነዚህ ተይዘው የነበሩት ዜጎች " ያለአንዳች ፍላጎታቸው በመውሰድ ነው " እንጂ የውሥጥ ተፈናቃይ አይደሉም ብለዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩት እዚህ ዜጎች ለወራት ተይዘው በቆዩበት ካምፕ ውስጥ የምግብ እና ሌሎች አገልግሎቶች ችግሮች እንደነበሩባቸው የተናገሩ ሲሆን ለተለያዩ የጤና ችግሮች ተጋልጠው መቆየታቸውን እንደገለፁለት ቢቢሲ አስነብቧል።

#Oromia #Afar
ዛሬ በኦሮሚያ ክልል እና በአፋር ክልል በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል።
በኦሮሚያ ክልል አደጋው የደረሰው በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ሲሆን በአደጋው የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ከ6 ሟቾች በተጨማሪ 15 ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
አደጋው ከአዳባ ከተማ ወደ ላጆ ከተማ ሲጓዝ በነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዙ መኪና በመገልበጡ የተከሰተ ነው።
መኪናው የመጫን ልኩ 28 ሰው ብቻ የነበረ ቢሆንም ከመጠን በላይ በመጫን 40 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ አደጋው መድረሱ ተገልጿል፡፡
በአፋር ክልል ደግሞ የትራፊክ አደጋ የደረሰው በሎጊያ ከተማ ሲሆን መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ተሽከርካሪው ጥዋት ከሎጊያ 15 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አፍዴራ ሲጓዝ ኮሪ ወረዳ ልዩ ቦታው " ጉያህ " ላይ ተገልብጦ ነው አደጋው የደረሰው። 5 ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 10 ሰዎች ቀለል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው።
አሸክርካሪዎች ይዛችሁ የምትጓዙት ክቡር እና የማይተካውን የሰው ህይወት ነው እና ሁሌም ጥንቃቄ ማድረግ፣ ህግ እና ስርዓትን ማክበር አትዘንጉ።

#Tigray #Afar
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሎጅስቲክስ ክላስተር ትብብር ወሳኝ የሆኑ ህይወት አድን ድጋፎችን በአየር መቐለ መድረሳቸውን አሳውቋል።
መቐለ በአየር ከደረሰው ህይወት አድን ድጋፍ መካከል የUNICEF ክትባቶች እና በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተጎዱ እናቶች እና ህፃናት የሚውል የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድጋፍ የተካተተበት ነው።
UNICEF ይፋ ባደረገው መረጃ 1.4 ሚሊዮን ዶዝ ክትባቶችን መቐለ ደርሷል። ክትባቶቹ በክልሉ 50,000 ህጻናትን እና እናቶችን ለመከተብ እንደሚውሉ የሚውሉ ናቸው ተብሏል። መቐለ ከደረሱት ክትባቶች አሁን ላይ በክልሉ ላሉ ጤና ጣቢያዎች እየተከፋፈሉ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ፤ በዩናይትድ ኪንግደም ድጋፍ በሰሜን ምዕራብ አፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የምግብ እርዳታ የያዙ ተሽከርካሪዎች ስለመንቀሳቀሳቸው ተሰምቷል።
እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል እንዲደረስ በዩናይትድ ኪንግደም የተሰጠው ወሳኝ የሆኑ ህይወት አድን ድጋፎችን የያዙ 54 ተሽከርካሪዎች መሆናቸው ተነግሯል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለሰላምና ግንባታ የመጠቀም ልምድ ደካማ በሆነበት ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ጉዳታቸው ትልቅ ነው።
በተለይ እነዚህ አደገኛ መረጃዎች በከተማም ሆነ ከተማ ወጣ ባሉ አከባቢዎች የሚፈጥሩት ተጽዕኖ ከፍ ያለ ነው።
ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከጥር 13 ጀምሮ ለ4 ቀናት በዲጂታል ሰላም ግንባታ እንዲሁም መሰረታዊ የሚዲያ ክህሎት ላይ ትኩረቱን መሰረት ያደረገው የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተካሂዷል።
በስልጠናው 20 ወጣቶች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ 4 ወረዳዎች (አሚባራ፣ አፋንቦ፣ ጭፍራ፣ ገዋኔ) ለተወጣጡ ሰልጣኞች የዲጂታል ሚዲያ ክህሎትን ስለማሳደግ፣ የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ስለመስራትና ከሀሰተኛና ጥላቻ ንግግሮችን ራስንና ማኅበረሰብን ስለመከላከል በዚህም ምክንያት የሚደርስን ጉዳት መቀነስ በሚቻልበት አግባብ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።
በቀጣይም ወጣቶቹ በወሰዱት ሥልጠና መሰረት ወደ ማኅበረሰባቸው ተመልሰው ለሌሎች እኩዮቻቸው ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን እንዲሰጡ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በአከባቢያቸው አወንታዊ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ለማስቻል ታቅዷል።
በተለይ የመረጃ ተደራሽነቱ በተለያዩ ምክንያቶች ለተገደበባቸው አከባቢዎች መሰል የአቻ ሥልጠናዎች ትርጉም ያለው ለውጥ ከማምጣቱም በዘለለ ወጣቱን አሳታፊ ያደረገ የመፍትሔ ሀሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ እድሉን በሰፊው ያመቻቻል።
ይህንን ስልጠና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከ Mercy Corps Ethiopia ጋር በጋራ በመሆን ለሥልጠናው ከሚያስፈልገው የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ ጀምሮ በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ።
በቀጣይ በድሬደዋና በጅጅጋ ከተሞች መሰል ሥልጠናዎችን የሚሰጡ ይሆናል።

15ኛው የአፋር ሱልጣን በዓለሲመት ሰኞ ይከናወናል።
የፊታችን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ሱልጣን አህመድ አሊሚራሕ 15ተኛው የአፋር ሱልጣን በመሆን በዓለሲመታቸው እንደሚከናወን የአፋር ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘግቧል።
ለዚሁ በዓለሲመት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። አዲስ አበባ ሲገቡ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

#Afar 15ኛው የአፋር ሱልጣን በዓለሲመት ሰኞ ይከናወናል። የፊታችን ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ሱልጣን አህመድ አሊሚራሕ 15ተኛው የአፋር ሱልጣን በመሆን በዓለሲመታቸው እንደሚከናወን የአፋር ማስ ሚዲያ ኤጀንሲ ዘግቧል። ለዚሁ በዓለሲመት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። አዲስ አበባ ሲገቡ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል። @tikvahethiopia
#Afar
ቀጣይ የአውሳ ሱልጣኔት አልጋወራሽ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ በዓለሲመታቸዉን ለመከወን ዛሬ የአፋር መዲና፣ ሰመራ መግባታቸውን የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።
ሱልጣን አህመድ አልሚራህ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመሬሮችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች አቀባባል አድርገዉላቸዋል።
በዓለሲመቱ የሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ/ም በአውሳ ሱስለጣኔት መናገሻ በሆነችው አይሳኢታ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከናወን ይጠበቃል።
በእለቱ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከሚገኙ እና በጀቡቲና ኤርትራ የሚገኙ የአፋር ማህበረሰብ ባህላዊ መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ ሰዎች እንዲሁም የፌድራልና የክልሉ መንግስት አካላት አምባሳደሮች እንደሚገኙ ይጠበቃል ተብሏል።
#አፋብመድ

#Afar ቀጣይ የአውሳ ሱልጣኔት አልጋወራሽ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ በዓለሲመታቸዉን ለመከወን ዛሬ የአፋር መዲና፣ ሰመራ መግባታቸውን የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል። ሱልጣን አህመድ አልሚራህ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመሬሮችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች አቀባባል አድርገዉላቸዋል።…
#AFAR
ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ 15ኛው የሀውሳ ሱልጣኔት ሱልጣን ሆነው በዓለ ሲመታቸው ዛሬ ተከናወነ።
በበዐለ ሲመቱ ላይ ፦ በርካታ ነዋሪዎች፣ በጅቡቲ እና ኤርትራ የሚኖሩ የአፋር ህዝብ ተወካዮች፣ የአርጎባ ህዝብ አመራሮች ተገኝተው ነበር።
በተጨማሪ ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ የአፋር ክልል ርዕሠ መስተዳደር ሀጂ አወል አርባ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት የስራ ሀላፊዎች ፣ አምባሳደሮች በበዓለ ሲመቱ ተገኝተው ነበር።
Photo Credit : Argoba Community Radio

" ከጨው ፓለቲካ ጋር በተያያዘ ከ1,700 በላይ ሰዎች ታስረዋል " - የዶቢ ጨው አምራቾች ማኅበር
" ከጨው ፓለቲካ ጋር በተያያዘ ከ1,700 በላይ ሰዎች ታስረዋል" ሲል በአፋር ክልል የሚገኘው የዶቢ ጨው አምራቾች ኃላ/የተ/የግል/ሕብረት ሽርክና ማኅበር ገለጸ።
ሰዎቹ የታሰሩት የት ማረማያ ቤትና ለምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበለት ጥያቄ ማኅበሩ፣ " የታሰሩት በሰመራ ማረሚያ ቤት ነው፣ የታሰሩበት ምክንያት ደግሞ ጨው ለማምረት በመከልከላቸው ቅሬታ ሲያቀርቡ ነው " ብሏል።
ማኅበሩ እንዳስረዳው ፤ 409 አባላቱ ጨው እንዳያመርቱ በመንግሥት መታገዳቸውን፣ የታገዱበት ምክንያትም እንዳልተነገራቸው ነው።
የሚኅበሩ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሁሴን አሊ የማኅበሩ አባላት በችግር ላይ መሆናቸውን ገልጸው፣ በክልሉ ብዙ #ሙስና እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፤ በጨው ማምረት ሥራ የተሰማሩት በክልሉ የሚገኙ አመራሮች ብቻ ናቸው ብለዋል።
የማኅበሩ አባላት በተናጠልና በጋራ እንደገለጹት ፣ ክልከላው እንዲነሳ ለሚመለከታቸውን የክልሉ የመንግሥት አካላት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም አጥጋቢ ምላሽ አላገኙም።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ፣ በማኅበርና በየፊናቸው በሰጡት ገለጻ፣ በዚህ ሳቢያ በአፋር ክልል ግጭት ከመፈጠሩ በፊት የፌደራል መንግሥት አፋጣኝ መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ጠይቀዋል።
ከዚህም ባሻገር ጨው አምራቾች ምርታቸው የሸጡበት የስድስት ወራት ክፍያ እንዳልተከፈላቸው ፣ የማኅበሩ አባላት በየፊናቸውና በማኅበር በሰጡት ገለጻ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ፤ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ " ተርበናል " ብለው የሚጠይቁ ሰዎች በፓሊስ እየታሰሩ መሆኑን ማኅበሩ አስታውቋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች ሰዎች በርሃብ እየሞቱ ነው ብለው፣ ለአብነትም በአፍዴራ ሰሞኑን ሁለት ሰዎች ሞተዋል ብለዋል።
ዶቢ የጨው አምራች ማኅበር ኃላ/የተ/የግል/ሕብረት ሽርክና ማኅበር በአፋር ክልል በ1992 ዓ.ም በባህላዊ የምርት አሰራር የተመሰረተና በሂደት ወደ ዘመናዊነት የተሸጋገረ 409 አምራች አባላት ያሉት ማኅበር ነው።
መረጃውን የአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያዘጋጀው።

Photo
#Afar #Somali🚨
" የግጭቱ ማገርሸት ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱ ገልጿል።
ኮሚሽሙ ግጭቱ እንዳሳሰበውም አመልክቷል።
ኢሰመኮ በቅርቡ በሚያዚያ ወር የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በሶማሊ ክልል ሽንሌ ዞን እና አፋር ክልል አዋሳኝ ያገረሸው ግጭት አሳሳቢ ነው ብሏል።
ግጭቱ ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት እንዳሆነ ገልጿል።
በኮሚሽኑ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰኢድ ደመቀ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃል ፤ " የአሁኑ ግጭት የተጀመረው ከግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም 2024 ወዲህ ነው " ብለዋል።
" በግጭቱ የተወሰኑ ሰዎች ሞት፤ መፈናቀል እና የአካል ጉዳት፤ የንብረት መውደም እንደደረሰ ነው ያለው መረጃ በእኛ በኩል ግጭቱ እንዳገረሸ። በትክልል ስንት ሰው ሞተ፤ ቆሰለ የሚለውን ገና በምርመራ የምናጣራው ነው " ብለዋል።
" በአሁኑ ወቅት ግን ጠቅለል ባለ መልኩ የሰው መፈናቀል፤ ሞት እና ጉዳት እንዳለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ኢሰመኮ ከሁለቱ ክልሎች የመንግስት አስተዳዳሪዎች ተረዳሁት ባለው መሠረት ፥ በሁለቱም ክልሎች በኩል የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀሎች ተፈጽሟል።
በቅርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተገኘው አዎንታዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ሁለቱ ክልሎች ያሰጡትን አዎንታዊ ምላሽ ያደነቀው ኢሰመኮ፤ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲቀጥል የፌዴራልም ሆነ የሁለቱ ክልሎች መንግስታት የቀጠለውን ግጭት እንዲያስቆሙት ጥሪውን አቅርቧል።
የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የግጭት ማስቆም ጥረት እንዲያስደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የሁለቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በቀጣይ ሕዝበ ሙስሊሙ ከሚያከብረው የኢድ አል-አደሃ በዓል አስቀድሞ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
#DWAmharic #EHRC

#Afar #Tigray
የትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው የተደገፈ ይፋዊ ምክክር አደረጉ።
ዛሬ በዓፋርዋ ሰመራ ከተማ የተሳለጠው ግንኙነት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ እና በዓፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ የተመራ ነው።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ሰመራ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ፕሬዜዳንት አወል አርባ እና ካቢኔያቸው አቀባበል አደርገውለታል።
የሁለቱ አጎራባች ክልሎች ይፋዊ ግንኙነት በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የሻከረው ግንኙነት ለማደስ ያለመ እንደሆነ ድምጺ ወያነ ዘግቧል።

#Afar #Tigray የትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው የተደገፈ ይፋዊ ምክክር አደረጉ። ዛሬ በዓፋርዋ ሰመራ ከተማ የተሳለጠው ግንኙነት በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ጌታቸው ረዳ እና በዓፋር ክልል ፕሬዜዳንት አወል አርባ የተመራ ነው። በአቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ ሰመራ ከተማ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ፕሬዜዳንት አወል አርባ እና ካቢኔያቸው አቀባበል አደርገውለታል። የሁለቱ…
#Afar #Tigray
ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ።
በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል።
ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል አጎራባች ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጸጋይ ገብረተኽለ ፥ " ውይይቱ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ጉርብትና ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያግዝ ውጤታማ ውይይት ነው " ብሎውታል።
" በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ፣ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ፣ ነፃ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ እና የቆየው የሰላም እና የልማት ግንኙነት እንዲቀጥል በውይይቱ ስምምነት ላይ ተደርሷል " ብለዋል።
" ሁለቱ ክልሎች በሚያዋስኑ አከባቢዎች ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚከሰቱ " የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው " ግጭት ጠማቂዎችና ወንጀለኞች ተላልፈው እንዲሰጣጡ ፣ የጋራ የሰላም እና የፀጥታ እቅድ እንዲኖርና በየወሩ እየተገመገመ እንዲመራ ትግራይ እና ዓፋር ተስማምተዋል " ሲሉ አሳውቀዋል።
በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል የነበረው የአንድ ቀን ቆይታ አጠናቅቆ ወደ መቐለ መመለሱ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት በመጥቀስ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

#Afar #Tigray ትግራይ እና ዓፋር ክልሎች በፕሬዜዳንቶቻቸው በኩል ባደረጉት ይፋዊ ግንኙነት የሁለቱም ህዝቦች አብሮነት የሚጎዱ ወንጀለኞች ተላለፈው እንዲሰጣጡ ተሰማሙ። በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራ ልኡክ በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ያደረገው የአንድ ቀን ምክክር አድርጓል። ምክክሩ ውጤታማ እንደነበር ተገልጿል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ልኡክ አባል የዓፋር ክልል…
#Afar #Tigray
" የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ ነው " - ሀጂ አወል አርባ
የአፋር ክልል ፕሬዜዳንት ሀጂ አወል አርባ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከፍተኛ አመራርን ላካተተዉ ሉዑካን ቡድን ምን አሉ ?
" የአፋርና ትግራይ ህዝቦች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግሮችን መፍታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ነው።
በሁለቱ ክልሎች መካከል ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ ነው።
የትግራይ ክልል ሰላም ለክልላችን ሰላም ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ መረጋጋትን ለመፍጠር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል።
ለክልሉ ሰላምና መረጋገት የድርሻችንን እንወጣለን " ብለዋል።

#Attention🚨 በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። " በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል " ብሏል። " በስምጥ ሸለቆች ውስጥ ንዝራቱ ከማሰማት በሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈንታሌ ተራሮች ውጭ የደረሰ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም " ሲል አክሏል። " በደሴ…
#Afar
በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ መፍለቅ መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል።
ከትናንት ሌሊት ጀምሮ መፍለቅ የጀመረው ፍል ውሃ መጠኑ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አፋር ክልል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ ነው።
በክልሉ ጋቢ ራሱ ዞን በሚገኘው ዱለሳ ወረዳ ሳንጋቶ ቀበሌ ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው ትናንት ሰኞ መስከረም 27/2016 ዓ.ም. ምሽት " የመሬት መንቀጥቀጥ " ከተከሰተ በኋላ እንደሆነ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ እና ሁለት የቀበሌው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ነዋሪዎች ምን አሉ ?
- ትናንት ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ መከሰት የጀመረው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ ሶስት ጊዜ ያህል ተደጋግሟል።
- የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የሚናገሩት ካቆመ በኋላ ሌሊት 10 ሰዓት ገደማ ላይ ድምፅ ሰማን። ጠዋት ላይ ድምፅ ወደተሰማበት ቦታ ስናመራ ከመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ እየፈለቀ ተመልክተናል።
- ውሃው የወጣው የአካባቢው ማህበረሰብ በሚኖርበት ሰፈር ውስጥ ነው። ድምፅ ነበረው። ማታ ፈርተን ነው ያደርነው። በጠዋት ሄደን ሁሉንም ነገር ለማየት ችለናል።
- ውሃው በሚወጣበት የመሬት ስንጥቅ ስር ድምፅ ይሰማል። ወደላይ የሚፈናጠረው ፍል ውሃ መጠን እና የሚፈልቅበት ስንጥቅ መጠን እየጨመረ ነው።
ፍል ውሃው በወጣበት ሳንጋቶ ቀበሌ ውስጥ ፍል ውሃ ባለመኖሩ አዲሱ ክስተት ነዋሪዎች ድንጋጤ እና ስጋት ላይ ጥሏል።
የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ ምን አሉ ?
° ከትናንት በስቲያ ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አንጻር የትናንቱ ትንሽ ያነሰ ነው።
° ከዚህ በኃላ ነው ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው።
° ሰዎች በቅርበት እዚያ አካባቢ ይኖራሉ። የእኛ አካባቢ ማህበረሰብ አርብቶ አደር ከመሆኑ አኳያ ከብቶቻቸውን ፍየሎቻቸውን የሚጠብቁበት ቦታ ነው።
° የወረዳው አስተዳደር ክስተቱን ለማጣራት ባለሙያዎችን ወደ ቀበሌው ልኳል።
° የሚፈጠረው ነገር ስለማይታወቅ ነዋሪዎች’ ከዚያ አካባቢ ለቅቀው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው። እንደዚህ አይነት ነገር ታይቶም ስለማይታወቅ ከፍተኛ ስጋት ነው ያለው።
የአፋር ክልል ጋቢ ራሱ ዞን በተደጋጋሚ እያጋጠመ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ነዋሪዎች ከሰፈሩበት አካባቢ እንዲነሱ እየተደረገ ነው።
አንዱ አካባቢው ይኸው የዱለሳ ወረዳ ነው።
አጎራባቹ አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ከሁለት ሳምንት በፊት በአካባቢው በሚገኘው ከሰም ግድብ እና ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የሚኖሩ ከ700 በላይ ሰዎችን ገላጣ ሜዳ ወደሆኑ አካባቢዎች አዘዋውሯል።
መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ሲሆን ፎቶና ቪድዮ የአብዶ ሀሰን፣ ሱልጣን ከሚል ነው።

#Afar በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ መፍለቅ መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል። ከትናንት ሌሊት ጀምሮ መፍለቅ የጀመረው ፍል ውሃ መጠኑ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አፋር ክልል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ ነው። በክልሉ…
#Afar
በአፋር ክልል ፣ ዱለቻ ወረዳ ሳጋንቶ ቀበሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የፈለቀውን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተላለፈ።
ማሳሰቢያውን ያስተላለፈው የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ነው።
ዩኒቨርሲቲው " በክልሉ በቅርቡ በተከሰተው እና ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ በተሰማው ርዕደ መሬት ሳቢያ በአካባቢው ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውኃ መፍለቅ ጀምሯል " ሲል ገልጿል።
ይህንን ፍል ውኃ ጥናት ሳይደረግበት ሰዎችም ሆኑ እንስሳት እንዳይጠቀሙት ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
በሬክተር ስኬል 4.9 በተመዘገበው ርዕደ መሬት የተሰነጠቀው መሬት 1.5 ሜትር ስፋት ያለው ስለመሆኑ አመልክቷል።
ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአፋር ክልል የተከሰተው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መሰጠንቅ፣ መኖሪያ ቤቶች ላይ መፍረስና መሰንጠቅ እንዲሁም እስሳት ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ እና መጠነኛ ጉዳት ስለማስከተሉ ዩኒቨርሲቲው አስረድቷል።
ህብተረተሰቡ በተፈጥሮ አደጋው ከተሰነጠቁ አካባቢዎች፣ ድልድዮች እና ተራራዎች እንዲርቅ ጥሪ ቀርቧል። #ኢቢሲ

#Earthquake
ትላንት ለሊት 9:52 ላይ በርካቶችን ከተኙበት የቀሰቀሰው በሬክተር ስኬል 5.8 ከተለካው የመሬት መንቀጥቀጥ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.4 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ በሬክተር ስኬል ፦
➡️ 4.7
➡️ 4.6
➡️ በድጋሚ 4.7
➡️ በድጋሚ 4.6
➡️ 4.9 የተለኩ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች ተመዝግበዋል።
ሁሉም አዋሽ እና አካባቢው ናቸው።
ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ከፍተኛው ነው።
በሌላ በኩል አፋር ክልል ዱላሳ ወረዳ የሚገኘው የኢፌዴሪ ከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል።
በስኳር ፋብሪካው አስተዳደር ህንፃ፣ በኃይል ማስተላለፊያ ክፍል፣ የላብራቶሪ እና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
አሁን ላይ መሬት መንቀጥቀጡ በከፍተኛ ሁኔታ በአከባቢው እየጨመረ በመምጣቱ ጉዳት በደረሰባቸው ህንፃዎች ውስጥ የሚገኙትን ሌሎች ንብረቶችን ለማዳን የመሬት መንቀጥቀጡ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።
የፋብሪካው ሰራተኞች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስቀድሞ እንዲለቁ መደረጉ ተነግሯል።
ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያለው የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆሙን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በተያያዘ መረጃ ፥ መንግሥት የርዕደ መሬቱ ማዕከል ከሆኑ አካባቢዎች ነዋሪዎችን የማራቅ ሥራ እያከናወነ መሆኑን አሳውቋል።
በተለይም ደግሞ የርዕደ መሬቱ ማዕከል የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሰሳ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማስፈር ርብርብ እየተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
#Ethiopia #Afar #Earthquake