TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በዓለም አቀፍ ርብርብ የተዘጋው ድረገፅ " ጄነሲስ ማርኬት " !

የሰዎችን የይለፍ ቃሎች ጨምሮ የግል መረጃዎችን ለአጭበርባሪዎች በመሸጥ የሚታወቀው ድረ-ገጽ በአለም አቀፍ ፖሊስ ትብብር መዘጋቱን ቢቢሲ አስነብቧል።

ድረገጹ በኢንተርኔት ላይ የማጭበርበር ስራ የሚፈጽሙ ግለሰቦች መረጃዎችን የሚሸምቱበት የዓለማችን ትልቁ የመረጃ መረብ ወንጀል ጣቢያ ሆኖ ቆይቷታ።

" ጄኔሲስ ማርኬት " የተሰኘው ድረገጽ የግለሰቦችን ዲጂታል የጣት አሻራዎችን ጨምሮ፣ አድራሻዎችን እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን ለወንጀለኞች ሲሸጥ ነበር።

ከዚህ ድረገጽ የተገኙ የግል መረጃዎችና የይለፍ ቃሎች የግለሰቦችን #የባንክ_አካውንት ድና የኢንተርኔት ግዢዎችን በቀላሉ ወንጀለኞች እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

ድረገጹ እነዚህንም መረጃዎች አብዛኛውን ጊዜም #ከአንድ_ዶላር ባነሰ ዋጋ ሲሸጥ ቆይቷል።

ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ያሉ የፖሊስና ደህንነት አካላት በመቀናጀት ነው ይህንን የሳይበር የወንጀል ጣቢያ ያዘጉት።

ጉዳዩን በተመለከተ የዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የወንጀል ኤጀንሲ (ኤንሲኤ) ምን አለ ?

" በተከታታይ በተደረገው ክትትልና ፍተሻ ድረገጹን ሲጠቀሙ የነበሩ 24 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከነዚህም መካከል ድረ-ገጹን በመጠቀም የማጭበርበር ስራ እየፈጸሙ ያነበሩ ግለሰቦችም ይገኙበታል። "

ማክሰኞ ረፋድ ላይ በተጀመረው ክትትልና ፍተሻ ከ17 አገራት የተውጣጡ ፖሊሶችና የደህንነት አባላት በቅንጅት ተሳትፈዋል።

ዘመቻው በአሜሪካው የፌደራል ምርመራ ቢሮ / #FBI / እና በኔዘርላንድ ብሄራዊ ፖሊስ የተመራ ሲሆን የዩኬው NCA፣ የአውስትራሊያ ፌደራል ፖሊስ እና በርካታ የአውሮፓ ሃገራት ተጣምረውበታል።

በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ያህል ፍተሻዎች የተከናወኑ ሲሆን በዚህም 120 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ረቡዕ ዕለት ወደ ጀነሲስ ድረገጽ የገባ ማንኛውም ሰው ‘ኦፐሬሽን ኩኪ ሞንስተር’ የሚል ማስጠንቀቂያና ድረገጹም መቆሙን የሚያሳይ መልዕክት አግኝተዋል።

የጄኔሲስ ድረገጽ 80 ሚሊዮን የሚሆኑ የዲጂታል አሻራዎችና የግል መረጃዎችን ለሽያጭ ያቀረበ ሲሆን በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የማጭበርበር ገበያ የተፈጸመበት እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል።

አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው ግለሰብ ላይ የተኩስ መልስ ሲሰጡ ተስተውሏል።

ግለሰቡ የግድያ ሙከራ ባደረገ በሰከንዶች ውስጥ መተገው ገድለውታል።

የግድያ ሙከራውን ያደረገው ማነው ?

- FBI የግድያ ሙከራውን ያደረገው ቶማስ ማቲው የተባለ #የ20_ዓመት_ወጣት እንደሆነ ገልጿል።

- ነዋሪነቱ ምርጫ ቅስቀሳውና የግድያ ሙከራው ከተደረገበት ስፍራ የአንድ ሰዓት ጉዞ የሚፈጅ ቦታ ነው።

- በ2022 ነው ቤተል ፓርክ ከተባለ ሀይስኩል የተመረቀው።

- ወጣቱ በብሔራዊ የሒሳብ እና ሳይንስ ኢኒሼቲቭ ተሸላሚም ነበር።

- የሪፐብሊካን ደጋፊም ጭምር እንደሆነ ተመዝግቧል (የዶናልድ ትራምፕ ፓርቲ ማለት ነው)።

- ቅስቀሳው ከሚደረግበት ቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣራ ላይ ሆኖ ነው ዶላንድ ትራምፕን ለመግደል የሞከረው።

- ለምን ይህን ለማድረግ እንደፈለገ FBI ምርመራ እያደረገ ነው።

#USElection #FBI

@tikvahEthiopia