TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan በሱዳን መዲና ካርቱም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ተሰምቷል። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ያስተላፉት የሱዳን የተቃዋሚዎች እና የፖለቲካ ሀይሎች ኮሚቴ ነው። ሰልፉ በሌተናል ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና በጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ መካከል የተደረሰውን ስምምነት በመቃወም ነው የሚካሄደው። የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪውን ተከትሎ በካርቱም ውስጥ የሚገኘው የደህንነት…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ - #የሱዳን_ተቃውሞ

የሱዳን ጸጥታ ሃይሎች በሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኮሱ።

ዛሬ በሱዳን መዲና ካርቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ጥቅምት ወር የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች ብሄራዊ ቤተ መንግስት አቅራቢያ በነበሩ ተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸውን ኤኤፍፒ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከካርቱም በተጨማሪ በተለያዩ የሱዳን ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ ነው።

Video Credit : UoKEN

@tikvahethiopia