TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
 #Update #TPLF

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም " - የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት

የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኮሚሽኑ አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ " ትናንት ህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት በመረዳት ዛሬ መፀፀትና ለደህንነቱ መትጋት ይገባናል " ብሏል። 

" በኛ ጦስ ምክንያት በህዝባችን ላይ ሊከተል የሚችለው መከራ ከወዲሁ በመገንዘብ ሊካሄድ ከታሰበ ጉባኤ ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በህወሓት አቋም የሚባል ጠፍቶ ቦታውን ኔትወርክና መቦዳደን ተክቶታል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ግልፅነት ፣ አሳታፊ አሰራር እና ዴሞክራሲ ጠፍቶ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይለዋል " ያሉት የኮሚሽን አባላቱ ፥ " 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለይስሙላ ቢቋቋምም ይህንን ወደ ጎን በመተው ስራውን የሚያከናውነው ሃይል የበላይነት አለኝ የሚል አካል ነው " በማለት ድርጊቱ አውግዘዋል።

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም ፤ ከመተማመን መግባባትና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ውጪ የሚካሄድ ህዝባዊ ጠቀሜታ ስለሌለው የዚሁ ተግባር አካልና ተባባሪ መሆን አንፈልግም " ብለዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ፥ " አካሄዳችሁ አስተካክሉ ላለ አካልና ግለሰብ የሌለ ስም እየሰጡ ማጥላላት የትም አያደርስም " ያሉ ሲሆን " ከኔትወርክ እና መጠላለፍ ያልፀዳ ጉባኤ ማካሄድ ህዝብን ይጎዳል እኛም የዘህ ጉዳት ተባባሪ ላለመሆን ይካሄዳል ከሚባለው ጉባኤ ራሳችን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
መቐለ እና የወንጀል የተግባር መስፋፋት !

" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም "
- የመቐለ ከንቲባ

በመቐለ ከተማ በያዝነው ዓመት ከአምናው በ1,841 በመቶኛ ሲሰላ 68 ፐርሰንት / የሚበልጥ የወንጀል ተግባር መፈፀሙ የከተማዋ የሰላምና የፀጥታ ዘርፍ አስታውቋል።

በ2015 ዓ/ም ላይ የተፈፀሙት የወንጀል ተግባራት 2,895 ሲሆኑ በያዝነው 2016 ዓ/ም 4,735 የወንጀል ተግባራት ተፈፅሟል።

ይህ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዘንድሮ የ1,841 የወንጀል ተግባራት መጨመር አሳይቷል።

" ፀጥታ እና ሰላም ከሌለ ሁሉም የለም " ያሉት የከተማዋ ከንቲባ ይትባረኽ ኣምሃ " ለፀጥታና ሰላም መጠበቅና የወንጀል ተግባር ለመቆጣጠር የሚያግዙ የድህንነት ካሜራዎች በተለያዩ የከተማ አከባቢዎች በመገጠም ላይ ናቸው " ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በህገ-ወጦች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ " በከተማዋ የሚካሄደው ህግ የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል " ያሉት ከንቲባው እስካሁን በምን የወንጀል ተግባር የተሳተፉ ፣ ምን ያህል ፣ እነማን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ በይፋ አልገለፁም። 

መቐለን ጨምሮ ሌሎችም ከተሞች ከደም አፋሳሹ ጦርነቱ በፊት በዚህ ልክ ወንጀል ተስፋፍቶባቸው አያውቅም።

በተለይም መቐለ ከተማ በደህንነት እና በጸጥታ ረገድ አንጻር ቀንም ማታም መንቀሳቀስ የሚቻልባት ነበረች። ወንጀልም በዚህ ልክ የተስፋፋባት ከተማ አልነበረችም።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #TPLF " እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  "  - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር። አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ? - የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት…
#Tigray : " ... ከጦርነቱ በኋላ የተቋቋመው መንግስት ስራውን ለመስራት አቅም ያጣበት ወቅት ላይ እንገኛለን " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ሀምሌ 25 እና 26/2016 ዓ.ም " የትግራይ ፓለቲካዊ አስተዳደር " በሚል ርእሰ አንድ መድረክ መቐለ ውስጥ ተካሂዶ ነበር።

የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተውም ንግግር አድርገው ነበር።

ምን አሉ ?

- በትግራይ የሃሳብ ጠቅላይነት ሊኖር አይችልም። ልዩነታችን በሰለጠነ መንገድ ከመፍታት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም።

- የትግራይ ህዝብ ለዘመናት የቆዩ የዓለም ስልጣኔዎች ባለቤት የነበረ ቢሆንም እኛ ሳንሰራው በቀረ ወይንም ባለንበት አከባቢ አቀማመጥ ትውልዶች ወደ ጦርነት እየገቡ ለቀውስ እየተጋለጡ መጥቷል።

- እጅግ አሰቃቂ እና ደም አፋሳሽ በነበረው ጦርነት ጥያቄ ውስጥ የገባው የህዝቡ ህልውናውን በማረጋገጥ አንፃራዊ ሰላም ቢያገኝም ከጦርነቱ በኋላ የተቋቋመው መንግስት ስራውን ለመስራት አቅም ያጣበት ወቅት ላይ እንገኛለን።

- ፓለቲካዊ ልዩነታችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት በጦርነቱ ክፉኛ የተጎዳው ህዝባችን ሁሉንም አቅሞቻችን አሟጠን በመጠቀም መምራት ይጠበቅብናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia
የፅህፈት ቤት ኃላፊው ከግድያ ለጥቂት አመለጡ።

በትግራይ ማእከላዊ ዞን የአክሱም ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ ለጥቂት ማማለጣቸው ተሰምቷል።

በኃላፊው ላይ የግድያ ሙከራ የተፈፀመው ሀምሌ 28/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ነው ተብሏል።

ኃላፊው ስራ ላይ አምሽተው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ከተኮሱባቸው ሁለት ጥይቶች ያለ ጉዳት ተርፈዋል።

የአክሱም ከተማ ፓሊስ የግድያ ሙከራ ተግባሩን የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥረት ላይ እንደሚገኝ ገልፆ ህዝቡ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግለት ጠይቋል።

የቱሪዝም መናገሻዋ የአክሱም ከተማ ከአስከፊውና ደም አፈሳሹ የትግራይ ጦርነት በኃላ በተጀመረው የአውሮፕላን በረራ አገልግሎት የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች መቀበል ጀምራለች።

ስለሆነም ይህንን መሰል የፀጥታ ስጋቶች የቱሪስት ፍሰቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንዳለው በመገንዘብ የፀጥታ መዋቅሩ የተቀናጀና የተናበበ ስራ መስራት እንዳለበት በርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች አስተያየት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia
#ትግራይ

" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ፅ/ቤቱ

በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ወረዳ የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።

የመሬት መደርመስ አደጋው በሰው ህይወት ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም የእህል አዝርእት ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

የመሬት የመደርመስ አደጋ ያጋጠመው ሀምሌ 29/2016 ዓ.ም በዓድዋ ወረዳ በታሪካዊትዋ የይሓ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።

የወረዳው የቁጠባ ዘርፍ ፅ/ ቤት ፤ " በአደጋው የ21 አርሶ አደሮች የተዘራ እህል ሙሉ በሙ ወድሟል " ብሏል። 

' ደምባፍሮም ' በተባለች መንደር የተዘራው ስንዴ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተመላክቷል።

" ከአሁን በፊት በትግራይ ያልተለመደ የመሬት የመደርመስ አደጋ አሁን አሁን መታየት ጀምሯል " ያለው ፅ/ቤቱ " አርሶ አደሩ የክረምቱን ሀያልነት ከግምት ያስገባ ሁሉን አቀፍ ጥንቃቄ እንዲያደርግ " ሲል አሳስቧል።

ዘንድሮ በትግራይ ክልል ያለው ኃይለኛ ክረምት በንብረትና በእንስሳት አደጋ በማደረስ ላይ ይገኛል።

ባለፈው ሳምንት በክልሉ የራያ ጨርጨር ወረዳ ዝናብ ያስከተለው ኃይለኛ ጎርፍ በ106 የቤት እንስሳትና በ11 ሄክታር የእርሻ መሬት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በጎርፉ 91 እንስሳት ሲወሰዱ ፣ 15 ቱ የአካል ጉዳት ደርሷቸዋል። በ11 ሄክታር የተዘራ እህል ከጥቅም ውጭ ሆኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyMK

@tikvahethiopia