TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊያካሄድ እንደሆነ በዛሬው ዕለት አሳውቋል። ይኸው ልዩ ጨረታ የአሜሪካ ዶላር ለሚፈልጉ ባንኮች ነው። ጨረታው ነገ ነው የሚካሄደው። ፍላጎትት ያላቸው ባንኮች እንዲያመለክቱ ጥሪ ቀርቧል። እንደ ገበያው ሁኔታ ደግሞ በመጪዎቹ ሳምንታት ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ሊወጣ እንደሚችል አሳውቋል። (ዝርዝር…
#NEB : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡
የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ፦
☑ አንድን የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ ተሽጧል።
☑ 27 ባንኮች ተሳትፈውበታል።
☑ የዛሬው አማካይ ዋጋም የነገ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ነው ተብሏል።
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ምን አሉ ?
" ተግባራዊ የተደረገው የባንክ ምንዛሪ ዋጋ ከትይዩ የገበያ ዋጋ ጋር ያለው ልዩነት መቀራረቡን የሚያሳይ ተጨባጭ ውጤት መገኘቱ አስደሳች ነው። ይህ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ሊያሳካ ካሰባቸው ግቦች ነው።
የዉጪ ምንዛሪ ግብይት አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ባንክ ሥርዓት እንዲሸጋገር የሚያደርግ ነው። በዚህም የውጭ ምንዛሪ የሚያመጡትን ላኪዎች እንዲሁም ብዙ ኩባንያዎችን እና የውጭ ምንዛሪ ለሚፈልጉ ሥራ ፈጣሪዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። "
@tikvahethiopia