TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዓለም ወደለየለት ቀውስ ውስጥ ትገባ ይሆን ?

የፍልስጤም እና እስራኤል ጦርነት መቆሚያ ማጣቱን ተከትሎ በየጊዜው አዳዲስ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ፤ መካከለኛው ምስራቅ እየታመሰ ነው።

ምንም ሰላማዊ መፍትሄ በመጥፋቱ አሁንም በጦርነቱ ሰዎች እያለቁ ነው።

" ፍልስጤምን አትንኳት " የሚሉና ሃማስን የሚደግፉ ኃይሎችም እስራኤልን በሮኬት / ሚሳኤል መደብደብ አላቋረጡም።

ከሰሞኑን ግን በኢራን ቴህራን ውስጥ ለአዲሱ የኢራን ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት የተገኙት የሐማስ የፖለቲካ ኃላፊ እስማኤል ሃኒያ እንዲሁም ከዛ ቀድሞ የሊባኖሱ ሂዝቦላ ቡድን ከፍተኛ አዛዥ ፉአድ ሽኩር መገደላቸውን ተከትሎ የለየለት ውጥረት አይሏል።

እስራኤል የሐማሱን ሃኒያን ግድያ ስለመፈጸም ወይም አለመፈጸሟን በይፋ ያለቸው ነገር የለም።

ኢራን ግን እስራኤል ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃት ዝታለች።

እስራኤልን ክፉኛ ሳትቀጣት አርፋ እንደማትቀመጥ አሳውቃለች።

የእስራኤል ባለልስጣናትም የማይቀር ጥቃት ከኢራን እና ከሂዝቦላህ እንዳለ በመናገር መዘጋጀታቸውን እያሳውቁ ነው።

አሜሪካም ፤ እስራኤልም በቀጣዮቹ ሰዓታት የኢራን ጥቃት ሊኖር ይችላል የሚል ግምገማ አላቸው።

" እስራኤልን ፍጹም አትንኩብኝ " የምትለው አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ እና አካባቢው የተሰማራውን መከላከያዋን ለማጠናከር የጦር መርከቦች እና ተዋጊ ጄቶችን ልካለች።

የተላያዩ ሀገራት ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነው። የሚመጣው ነገር ያስፈራልና ከሊባኖስ ለቃችሁ ውጡ እያሉ ይገኛሉ።

በተጨማሪም ለጊዜው ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንዳይሄዱና አርፈው እንዲቀመጡ እያስጠነቀቁ ናቸው።

በአጠቃላይ ያሉት ሁኔታዎች ከባለፈውም ጊዜ በባሰ መልኩ አስፈሪ ናቸው።

አንዳንድ ሀገራት ኢራንን " እባክሽ አረጋጊው ! " ብለው ቢማጸኗትም " ቅጣቱ የማይቀር ነው " የሚል አቋም እንደያዘችና ጥቃቱም ከፍተኛ እንደሚሆን እየተነገረ ነው።

በሌላ በኩል ፥ ፍልሥጤም ውስጥ በየዕለቱ ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን እስካሁን በ10 ወራት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 583 መሻገሩን በጋዛ የሚገኘው ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። - @thiqaheth

@tikvahethiopia
📢Attention aspiring candidates in Ethiopia 🇪🇹🇪🇹! We invite you for an info session where the Jasiri team will provide insights into the Jasiri Talent Investor program and answer any questions you may have. Only 150 slots available. Please RSVP for the session at this link bit.ly/3WrVIDV.

#Jasiri4Africa
#SafaricomEthiopia

ምን እየጠበቅን ነው? ቲክቶክ ላይ የሙዚቃች ችሎታችንን እያሳየን እስከ 400,000 ብር ድረስ እንሸለም እንጂ!

የዲጂታል ሙዚቃ ውድድርን ለመቀላቀል፡
🎥 የአንድ ደቂቃ የራሳችን ሙዚቃ ቪዲዮ በTikTok ላይ እንፖስት
🏷 #1Wedefit እና #የምትኖሩበትከተማ አድራሻ ማስገባት እንዳንረሳ
📲የTikTok ደረገጽ @Safaricomet ታግ እናድርግ  እንዝፈን! እንላክ! እናሸንፍ!

መልካም ዕድል!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia 🇪🇹 በፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የማጣሪያ እና ፍፃሜ አትሌቲክስ ውድድሮች ዛሬ ይጠበቃሉ። በዛሬው ዕለት የ10,000 ወንዶች ፍፃሜ እንዲሁም 1,500 ወንዶች ፣ 800 እና 5,000 ሴቶች ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋል። ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ? - ቀን 6:05 :- 1,500ሜ ወንዶች ማጣሪያ ( አትሌት አብዲሳ ፈይሳ ፣ ሳሙኤል ተፈራ እና ኤርሚያስ ግርማ…
#Ethiopia

ዛሬ ሰኞ በፓሪስ ኦሎምፒክ ሀገራችን ምትሳተፍባቸው የፍፃሜ እና ማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የሴቶች 800 እና 5000 ሜትር ፍፃሜ እንዲሁም የወንዶች 3000ሜ መሰናክል ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

🇪🇹 ምሽት 2:04 :- 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ማጣሪያ (አትሌት ጌትነት ዋለ ፣ ለሜቻ ግርማ እና ሳሙኤል ፍሬው)

🇪🇹 ምሽት 4:45 :- 800ሜ ሴቶች ፍፃሜ (አትሌት ወርቅነሽ መሰለ እና ፅጌ ድጉማ )

🇪🇹 ምሽት 4:15 :- 5000ሜ ሴቶች ፍፃሜ (ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ)

መልካም ዕድል !

Via
@tikvahethsport  
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዛሬው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ምን ይመስላል ?

(ሐምሌ 29/2016 ዓ/ም)

በኢትዮያ ንግድ ባንክ የዛሬ ምንዛሬ ከቅዳሜው ምንዛሬ ዋጋ የተለየ ነገር የለም።

የአሜሪካ ዶላር መግዣው 95.6931 ፤ መሸጫው 101.4347 ሆኖ ዛሬ ቀጥሏል።

የሌሎች ውጭ ምንዛሬዎች ላይም በቅዳሜው ነው የቀጠለው።

በግል ባንኮች ግን ፉክክሩ ደርቷል።

ለአብነት (
#CASH)፦

አቢሲንያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.2288 ፤ መሸጫው 113.2585
💷 ፓውንድ መግዣው 122.2153 ፤ መሸጫው 138.1033
💶 ዩሮ መግዣው 109.3596 ፤ መሸጫው 123.5763

➡️ ወጋገን ባንክ

💵 ዶላር 101.6434 መግዣ ፤ መሸጫው 113.8406
💷 ፓውንድ መግዣ 130.1137 ፤  መሸጫ 145.7273
💶 ዩሮ መግዣ 110.9031 ፤ መሸጫው 124. 2115

➡️ ዳሸን ባንክ

💵 ዶለር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 112.0271
💷 ፓውንድ መግዣ 124.0748 ፤ መሸጫ 137.7230
💶ዩሮ መግዣው 109.4334 ፤ መሸጫው 121.4711
🇸🇦የሳውዲ ሪያል 24.3462 መግዣው ፤ መሸጫው 27.0243
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው በ24.8666፤ መሸጫው 27.6019

➡️ ንብ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0959 ፤ መሸጫው 111.2055
💷 ፓውንድ መግዣው 129.3521 ፤ መሸጫው 142.2874
💶ዩሮ መግዣው 110.3056 ፤ መሸጫው 121.3362
🇦🇪የUAE ድርሃም መግዣው 27.5263 ፤ መሸጫው 30.2789
🇸🇦የሳዑዲ ሪያል መግዣው 26.9446 ፤ መሸጫው 29.6390

➡️ ኦሮሚያ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.8445 ፤ መሸጫው 113.9543
💷 ፓውንድ መግዣው 128.5263 ፤ መሸጫው 145.2347
💶 ዩሮ መግዣው 108.8012 ፤ መሸጫው 122.9453
🇰🇼 የኩዌት ዲናር መግዣው 329.8724 ፤ መሸጫው 372.7558

ፀደይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0348 ፤ መሸጫው 111.1383
💷 ፓውንድ መግዣው 123.2017 ፤ መሸጫው 135.5219
💶 ዩሮ መግዣው 110.2390 ፤ መሸጫው 121.2629

ብርሃን ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 96.1716 ፤ መሸጫው 110.5973
💷 ፓውንድ መግዣው 118.2188 ፤ መሸጫው 135.9516
💶 ዩሮ መግዣው 104.2746 ፤ መሸጫው 119.9158

ቡና ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 101.0000 ፤ መሸጫው 113.6250
💷 ፓውንድ መግዣው 125.8698 ፤ መሸጫው 138.4568
💶 ዩሮ መግዣው 106.5545 ፤ መሸጫው 117.2100

ፀሐይ ባንክ

💵 ዶላር መግዣው 100.9253 ፤ መሸጫው 115.0548
💷 ፓውንድ መግዣው 130.1137 ፤ መሸጫው 146.3779
💶 ዩሮ መግዣው 112.5666 ፤ መሸጫው 126.6375

#Floatingexchangerate #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ዓለምአቀፍ : የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺክህ ሃሲና ስልጣን ለቀው ሀገር ጥለው ወጡ።

በባንግላዴሽ ምን ተፈጠረ ?

➡️ ተማሪዎችና ሌላውም ዜጋ የመንግስትን የስራ ቦታ ኮታ ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ተቃውሞ የጀመሩት ከሳምንታት በፊት ነው።

ይህ የኮታ ተቃውሞ ምንድነው ? እኤአ በ1971 ባንግላዴሽ ለነጻነቷ ከፓኪስታን ጋር ጦርነት አካሂዳ ነበር። በዚህም " 30% የመንግሥት ስራ ለነዚሁ ተዋጊዎች ቤተሰቦች እንዲሆን " የሚል አዲስ ኮታ በመንግሥት ወጥቷል።

ተቃዋሚዎች ግን " ይህ ፍጹም አግላይና አድሏዊ ፤ ሆን ተብሎም የጠ/ሚኒስትሯን ፓርቲ ደጋፊዎች ለመጥቀም የተደረገ ነው  " በማለት ነው ተቃውሞ የጀመሩት።

➡️ በኃላ ይህ ተቃውሞ ወደ አመጽ ተቀይሯል። ይህ የሆነው ተማሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች እና ከመንግሥት ደጋፊዎች ጋር በመጋጨታቸው ነው።

➡️ መንግሥት በተቃውሞው 150 ሰዎች ሞተዋል ቢልም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን 200 ነው የሞቱት ብለዋል።

➡️ ኢተርኔትም ተዘግቶ ነበር።

➡️ የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍ/ቤት ተቃውሞው ሲያይል በጉዳዩ ላይ ገብቶ የሰልፈኞቹ ቁልፍ ጥያቄ የሆነውን የኮታ ስርዓቱን ለማስተካከል ሞክሮ ነበር።

እንዴት ? ለተዋጊ ቤተሰቦች የተሰጠው ኮታ ወደ 5% እንዲቀንስ ፤ 93% በሚገባው ችሎታ ብቻ እንዲሆን ፤ 2% ለአናሳ ብሔር አባላትና ለሌሎች እንዲሆን የሚል ነው።

በዚህም ነገሮች የተቀዛቀዙ መስለው ነበር። በኃላ ግን ተቃውሞውም እጅግ ሰፋ።

➡️ ተቃዋሚዎቹ " ጠቅላይ ሚኒስትሯ ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ ናቸው " በማለት ስልጣን እንዲለቁ መቃወም ያዙ።

➡️ ዛሬ ሰኞ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ስልጣን ለቀው ሀገር ጥለው ወጥተዋል።

➡️ ተቃዋሚዎች በዋና ከተማው ዳካ የሚገኘውን መኖሪያቸው / ቤተመንግስት ውስጥ ገብተው ወረዋል።

➡️ ተቃዋሚዎች ለደስታ አደባባይ ወጥተዋል ተብሏል። -
@thiqaheth

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዓለምአቀፍ : የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺክህ ሃሲና ስልጣን ለቀው ሀገር ጥለው ወጡ። በባንግላዴሽ ምን ተፈጠረ ? ➡️ ተማሪዎችና ሌላውም ዜጋ የመንግስትን የስራ ቦታ ኮታ ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ተቃውሞ የጀመሩት ከሳምንታት በፊት ነው። ይህ የኮታ ተቃውሞ ምንድነው ? እኤአ በ1971 ባንግላዴሽ ለነጻነቷ ከፓኪስታን ጋር ጦርነት አካሂዳ ነበር። በዚህም " 30% የመንግሥት ስራ ለነዚሁ ተዋጊዎች…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Bangladesh : ለ15 ዓመታት ያህል ባንግላዴሽን የመሩት ሺህክ ሀሲና የተነሳባቸውን ጠንካራ ተቃውሞ ተከትሎ ሀገር ጥለው  ጠፍተዋል።

የተቆጡ ተቃዋሚዎችም ወደ ሚኖሩበት ቤተመንግስት በኃይል ሰብረው በመግባት ወረው በመኖሪያ ቤታቸው እንዳሻቸው እየፈነጩበት ነው።

ግማሹ አልጋ ላይ ፣ ግማሹ በየክፍሉ እየዞረ እቃቸውን ይፈትሻል፣ ግማሹ ይጨፍራል።

ከመንግሥት የስራ ኮታ ስርዓት ጋር በተያያዘ ተማሪዎች የጀመሩት እና ሌሎችም ዜጎች የተቀላቀሉበት ተቃውሞ ለሳምንታት ቆይቷል፤ በርካቶች ሞተዋል። በመጨረሻ ግን ሀሲናን ሀገር ለቀው እንዲጠፉ አስገድዷቸዋል።

የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከስልጣን ወርደው መሄዳቸውን አሳውቋል።

በሚመሰረት ጊዜያዊ መንግሥት ሀገሪቱ ትመራለችም ብሏል። ህዝቡም በሰራዊቱ ላይ እምነቱን እንዲጥል ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia ለ2017 የበጀት አመት ተጨማሪ በጀት በቅርቡ ይጸድቃል። የዘንድሮ በጀት 1.8 ትሪሊየን ብር እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህ መጠን ባለፈው ሰኔ ወር ለ2017 በጀት አመት ከጸደቀው 971 ቢሊየን ብር አንጻር በእጥፍ የሚጨምር ነው፡፡ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ድጋፍ ማግኘት የጀመረው መንግስት ለውጡን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ጫናዎችን ለመከላከል…
#Ethiopia

የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ " ለማኅበራዊ ድጋፍ " የሚውል ነው ብለዋል።

ተጨማሪ በጀቱ የፌደራል መንግሥቱን ሰኔ ወር ላይ ያጸደቀውን የ2017 ዓ.ም. በጀት 1.5 ትሪሊዮን ብር ገደማ ያደርሰዋል።

የፌደራል መንግስት ዓመታዊ በጀትም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1 ትሪሊዮን እንዲሻገር ያደርገዋል።

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ምን አሉ ?

የህህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከአንድ ወር በፊት አንድ ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት ማጸዕደቁን ያታወሳል።

አሁን 551 ቢሊዮን አካባቢ የሚሆን ተጨማሪ በጀት ለምክር ቤቱ ይቀርባል።

በተጨማሪ በጀት መልክ ለፓርላማ ከሚቀርበው ግማሽ ትሪሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን የሚሆነው ፦
° ለማኅበራዊ ድጋፍ፣
° ለሴፍቲኔት፣
° ለሠራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣
° ለመድኃኒት ድጎማ፣
° ለዘይት ድጎማ፣
° ለነዳጅ ድጎማ የሚውል ነው።

ከወጪው በተጨማሪ የገቢ በጀትንም ለሕ/ተወ ምክር ቤት አቅርበን እናሳውጃለን።

563 ቢሊዮን የነበረው የፌደራል መንግሥት ገቢ ተከልሶ 851 ቢሊዮን ይሆናል። ይሄ የሚሆነው ግን አንድም የታክስ መጠን ሳይጨምረ ነው።

ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ ፦

" ይሄንን ስናደርግ ተጨማሪ ታክስ በመጣል ወይም የታክስ ምጣኔ በመጨመር አይደለም መጨመር ያሰብነው። ኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን distortion ዝንፈት በማስተካከል ነው።

ታክስ ሳይከፍል ይከብር የነበረ ባለሃብት አሁን ቶሎ ወደ መስመር መግባት አለበት። ይሄንን የሚፈቅድ ነገር አይኖርም። ጠንካራ የሆነ enforcement ሥራ ይሠራል። "

#Ethiopia #FBC #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ ይህ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ የተከሰተ የመሬት መንሸራተት ነው። ትላንት ቀን 10:30 በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ 1 ሰው ሲሞት ፣ 1 ሰው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። 8 የአከባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። በተከሰተው ናዳ አደጋ ህይወቷ ያለፈው የ11 ዓመት ሴት ልጅ ናት። አብራት የነበረችው ወላጅ እናቷ ደግሞ ከአደጋው…
#Alert🚨

" እስካሁን የ11 ሰዎች አክስሬን ተገኝቷል " - የካዎ ኮይሻ ወረዳ

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር አሳውቋል።

ከቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ 1 ሰው ህይወቱ ማለፉ እና 1 ሰው ከባድ ጉዳት እንደረሰበት ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከወረዳው ኮሚኒኬሽን ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia