TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ፍትህን እስከምናገኝ ድረስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እንከፍላለን " - ካውንስሉ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ከርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል ላይ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ኢ-ህገ መንግስታዊ ጥሰት እየፈጸመ እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል አሳወቀ። ድርጊቱን በመቃወምም መግለጫ አውጥቷል። ካውንስሉ ፤ የኩሪፍቱ ማዕከል በህጋዊ መንገድ ለቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ…
🔈#የኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተክርስቲያን

በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታ ላይ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እየተወሰደ ነው ያለችው ሕገወጥ እርምጃ እንዲቆም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቅርባለች።

ቤተክርስቲያኗ በዛሬው ዕለት ስለጉዳዩ ሰፋ ያለ ዝርዝር መግለጫ ልካልናለች።

ከመግለጫው መካከል ፦

" በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እየተካሄደ ያለው ሕገወጥ አካሄድ፣ የፍርድ ቤትን ውሳኔን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጉዳዩን ለማጣራት የመጣ ቡድን ግኝቱን ይዞ ሄዶ የበላይ ውሳኔ ባልተሠጠበት ሁኔታ የኮርደር ልማትን ሰበብ በማድረግ ከቤተ ክርስቲያን ይዞታ ላይ #መሬት_በጉልበት_ቀምቶ ለሁለት ግለሠቦች ለመሥጠት የሚደረገው ሥራ በወንጌላውያን አምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ የተቀነባበረ የግለሰቦችን ፍላጎት ለማሟላት ቤተ ከርስቲያናችን ላይ በተደጋጋሚ እየተሰነዘረ ያለ ጥቃት ነው።

ይህ መላው የወንጌል አማኞችን የሚመለከት ኢ-ሕገመንግሥታዊ አካሄድ ስለሆነ፣ ጉዳዩን ለመንግሥትና ለፍትህ አካላት ማቅረባችን ይቀጥላል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና የፌዴራል መንግስት አካላት ይህ ጉዳይ ጥቂት ግለሠቦችን ጠቅሞ ሚሊየኖችን የሚያስከፋ ሕገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ አንድታስቆሙልን እና አስቸኳይ ምላሸ እንድትሰጡን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰባት ያለውን ሕገ ወጥ እርምጃ አጥብቀን የምንቃወምና የምናወግዝ መሆኑን እንገልጻለን።

መላው የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን እና የወንጌል አማኙ ማሕበረሰብ በአጠቃላይ ይህንን ህገመንግስታዊ መብታችንን የሚጋፋ ተግባር እስኪቆም ድረስ በያለንበት በጸሎት እንድንተጋ፣ በተለያየ መንገድ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጻችንን እንድናሰማ፣ ጉዳዩ በዚህ የማይገታ ከሆነ ከወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመምከር ሌሎች ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች እናሳውቃለን። "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM