TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Election2012

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባዘጋጀው እና የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተወካይ ወ/ሮ ሄተር ፈላይን በተገኙበት በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና ምርጫ 2012 አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል፡፡

አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በተካሄደው እና ዓላማው በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የፖለቲካ እና የምርጫ ዝግጅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መረጃ ለመሰብሰብ እንደሆነ በተገለጸው በዚሁ የውይይት መድረክ፣ የምርጫውን የግዜ ሰሌዳ፣ በተፎካካሪ ፓርቲዎች እና በገዥው ፓርቲ መካከል ያለው ግንኙነት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያጋጥሟቸው ችግሮች፣ የምርጫ ቦርድ ዝግጅት እና አቅም፣ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሀሳብ ልውውጥ ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጠቃላይ የለውጥ ሂደቱን እና ምርጫ 2012 አስመልክቶ ያጋጠሟቸውን ችግሮች እንዲሁም ገዥው ፓርቲ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ በማድረስ ላይ ነው ያሏቸውን ልዩ ልዩ ጫናዎች ለኤምባሲው ተወካዮች ገልጸዋል፡፡ የመንግስት ሀብትን እና ሚዲያን በብቸኝነት መጠቀም ፓርቲዎቹ በገዠው ፓርቲ ላይ ካነሷቸው ችግሮች መካከል ይገኙበታል፡፡

የፓርቲዎቹ ተወካዮች የአሜሪካ መንግስት ከሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በእኩል ርቀት ላይ ሊቆም እና በተለይ ለገዢው ፓርቲ የተለየ ድጋፍ ማድረግ የፖለቲካ ሜዳውን እና በዚህ አመት በሚካሄደው ምርጫ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

More https://telegra.ph/ETH-02-21-2

#FreedomandEqualityParty

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FreedomandEqualityParty

ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምርጫ 2013 የሚያደርገውን ዝግጅት አካል የሆነው የቅድመ እጩ ምዝገባ በይፋ ጀምሯል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ሙሐመድ በአማራ ክልል የኦሮሞ ዞን ባቲ ምርጫ ክልል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር የቅድመ እጩነት ፎርም መሙላታቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EZEMA #FreedomandEqualityParty

በኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዘጋጅቶታል የተባለውና “የሃገሪቷ ወቅታዊ የደህንነት ስጋት ትንተና” የሚል ርእስ ያለው ሰነድ ከትላንት ጀምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ነው።

በዚሁ ሰነድ መነሻነትም ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ የፓርቲው ስም አሉታዊ በሆነ መንገድ በመጠቀሱ ማብራሪያ እንዲሰጠው በደብዳቤ ጠይቋል።

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ህዝብ ግንኙነት ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥቷል። በዚህም ከትላንት ጀምሮ ሲዘዋወር የነበረውን ሰነድ'' ኢዜማን የማያወክል እና ኢዜማ የማያዉቀዉ'' ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ፓርቲው ፥ ''...በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ያለውን አረዳድ እና የወደፊት ተስፋ በመፅሀፍት አሳትሞ እና ህዝብ እንዲያዉቅ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ነው ...ለዚህም መፅሃፊት ፩ እና ፪፣ የፓርቲውን ፕሮግራም፣ የዜጎች መድረክ እትሞች እንዲሁም ምርጫ 2013 የቃልኪዳን ሰነድ ማየት ይቻላል'' ሲል ገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia