TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AU #Fraud #CBE

ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ፍድር ቤት ቀርበውም ለፖሊስ ተጨማሪ ቀን ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ምን አሉ ?

" በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካለው የአፍሪካ ህብረት ሒሳብ የወጣ ገንዘብ የለም።

አንድ ሰው ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅሞ ለማውጣት ቢሞክርም እዛው በቦታው ላይ ተይዟል።

የማጭበርበር ሃሳብና ገንዘብ ለመውሰድ ጥረት ቢደረግም ማክሸፍ ችለናል። ይህንን የሞከሩት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ናቸው። እኔ የማውቀው ይህን ብቻ ነው።

በመሰረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ሊሰጥ አይችልም። አጭበርባሪው መጥቶ  ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር።

ሰውዬው እዚህ ሀገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም የትም ውስጥ ሊገባ አይችልም።

አጭበርባሪዎች በየቀኑ ነው ወደ ባንካችን የሚመጡት ፤ ባንክ ስለምንሰራ ይህ የተለመደ ነው። ነገር ን ሁሌም የማጭበርበር ድርጊቶቹ ከመሳካታቸው በፊት እንደርስባቸዋለን። ለፍርድም እናቀርባቸዋለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፥ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት ያንን እያደረግን ነው። የአፍሪካ ህብረት እስካሁን ድረስ በይፋ ቅሬታ አላቀረበብንም። "

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአፍሪካ ኅብረት ምንጭ ምን አሉ ?

"የእኛ ሒሳብ ላይ መሰል ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

አሁን ላይ ማጭበርበሩ #በተከበሩ_ሰዎች አማካኝነት እየተሞከረ ነው። ይህ ደግሞ በጣም አስጨንቆናል። አንድ ቀን ባለስልጣናት ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸው ምንም አይነት ዋስትና የለንም።

እምነት እያጣን ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ (የውጭ ምንዛሬ) ለመያዝ ወስነናል።

ይህን መሰሉ ሁኔታ የድርጅቱን ገንዘብ በውጭ ማቆየት እንድናስብ እያስገደደን ነው። "

https://telegra.ph/The-Reporter-04-21 #ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU #Fraud #CBE ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር) ለማዘዋወር ሲሞክሩ ነው በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ፍድር ቤት ቀርበውም ለፖሊስ ተጨማሪ ቀን ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ ንግድ…
" ከቤተክርስቲያን ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም " - መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ የቀሲስ በላይ መኮንን ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም ብላለች።

" ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚገለግሉ ቢሆንም ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም " ነው ያለችው።

የቀሲስ በላይን ጉዳይ በተመለከተ የመንበረ ፓቲሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ  መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

መምህር ዶ/ር አካለወልድ ፥ " ሊቀአዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች " ብለዋል።

" እስካሁን በተደረገው ክትትል ግን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በቀጣይ ግን ጉዳዩ የቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለወይ ? ለሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል አመልክተዋል።

ቀሲስ በላይ መኮንን ከአፍሪካ ኅብረት ኦፊሳላዊ የክፍያ ሰነድ ጋር ተመሳስለው የተዘጋጁ የተለያዩ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመጠቀም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ #ከ6_ሚሊዮን_ዶላር_በላይ (367 ሚሊዮን ብር የሚሆን) ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ አዟል።

በዋስ ጥያቄያቸው ዛሬም ውድቅ ተደርጓል።

ቀሲስ በላይ መኮንን በችሎቱ ፥ " ፖሊስ ይዞኝ ሳይሆን እራሴ ነው የሄድኩት " ብለዋል፡፡

" #ብዙ_የሀገር_ጉዳይ በእጄ ስላሉ ጥፋ ብባል እንኳ የምጠፋ ስላልሆንኩ ፤ በጤናዬ ላይ በደረሰው እክልና በቤተሰቦቼ ላይ በደረሰው ችግር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት ይጠብቅልኝ " ሲሉ ጠይቀዋል።

የብዙ ልጆች አሳዳጊና የቤተሰብ አስተዳዳሪ እንደሆኑ ጠቅሰው በዋስ ከእስር እንዲወጡ ጠይቀው ነበር።

ፍርድ ቤት ግን ሁሉም ተከሳሾች በፖሊስ ጣቢያ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ አዟል።

ቀሲስ በላይ መኮንን በሀሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ላይ #ከ6_ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል ተብለው አብረዋቸው ከነበሩት ሰዎች ጭምር መታሰራቸው አይዘነጋም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/DW-05-20 #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia