TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን ተወያየ ?

በትግራዩ ጦርነት ለተጎዳዉ የክልሉ ሕዝብ ተጨማሪ ሰብአዊ ርዳታ እንዲደርስ የተባበሩት መንግስታት (UN) የፀጥታው ጥበቃ ም/ቤት አባል ሃገራት ጠይቀዋል።

አስራ-አምስቱ የምክር ቤቱ አባላት ትግራይ ዉስጥ ስላለዉ ስብአዊ ሁኔታ በዝግ ተነጋግረዋል።

የፈረንሳዩ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ ምክር ቤቱ በይፋ ያወጣዉ መግለጫ የለም።

ይሁንና ዜና አገልግሎቱ የጠቀሳቸዉ ዲፕሎማት እንዳሉት የርዳታ ድርጅቶች ለትግራይ ሕዝብ ተጨማሪ ሰብአዊ ርዳታ ለማቅረብ ይበልጥ ይፈቀድላቸዉ ዘንድ ሁሉም ተሰብሳቢዎች ጠይቀዋል።

የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤትን ስብሰባ የጠሩት አየርላንድ ፤ ኢስቶንያ ፈረንሳይ፣ ኖርዌ፣ ብሪታንያ እና ዩናይትድ ስቴትስ ናቸዉ።

ከስብሰባው በኃላ ይፋዊ መግለጫ ባይወጣም ስብሰባውን አስመልክቶ ዲፕሎማቶች ባደረጉት ገለፀ ኬንያ ፣ ቱኒዝያ፣ ቻይናና ሩሲያ አሁን ባለው ደረጃ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደር አይገባም ብለዋል/ፍቃደኛ አልሆኑም።

#DeutscheWelle #AFP #Bloomberg

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kabul ትላንትና ከካቡል ኤርፖርት ውጭ በተፈፀመው አጥፍቶ ጠፊ የፈንጂ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 60 መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል። ከ60 ሟቾች መካከብ 13ቱ የአሜሪካ ወታደሮች ናቸው። በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር በመቶዎች ናቸው። ለጥቃቱ አፍጋኒስታን የሚገኘውና የISIS የአፍጋን ቅርጫፍ ኃላፊነቱን ወስዷል። ይህ የሽብር ቡድን እጅግ ወግ አጥባቂው የታሊባን ቡድን መለሳለስ የሚታይበት ለዘብተኛ ነው…
"...ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን እናድናችኋለን፤ ዋጋ እንድትከፍሉም እናደርጋለን" - ጆ ባይደን

የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ትላንት በካቡል ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ንግግር አድርገዋል።

የሽብር ጥቃቱን ለፈጸሙትም ሆነ አሜሪካን ለመጉዳት የሚመኙ አካላትን ጠንከር ባለ ንግግራቸው አስጠንቅቀዋል።

ባይደን ፥ "ምህረት አይኖረንም፤ አንረሳውምም፤ የገባችሁበት ገብተን እናድናችኋለን፤ ዋጋ እንድትከፍሉም እናደርጋለን" ሲሉ ዝተዋል።

አሜሪካ እና አፍጋኒስታንን የሚቆጣጠረው ታሊባን ቀደም ሲል በደረሱት ስምምነት መሳረት የአሜሪካ ወታደሮች እና ተልዕኮ ከ4 ቀናት በኋላ የፊታችን ረቡዕ ያበቃል።

የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ፔንታጎን ተጨማሪ የሽብር ጥቃት ሊኖር ይችላል ሲል ስጋቱን በመግለጥ ጥንቃቄ እንዲደረግ ከወዲሁ አሳስቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፦ አፍጋኒስታን ውስጥ አሜሪካንን ሲያግዙ ከነበሩ የውጭ ኃይሎች መካከል የጀርመን ወታደሮች ሙሉ በሙሉ ያለምንም ጉዳት ወደ ጀርመን መመለሳቸው ተጠቅሷል።

Source : #DeutscheWelle (DW)

@tikvahethiopia
#ADHD

የስዊድን መንግሥት ፦
° ጥንቃቄ የጎደለው ትኩረት የማጣት፣
° ከፍተኛ የመቅበጥበጥ፣ 
° ብዙ የማውራት፣
° ግትርነት
° እራስን የመግዛት ቀውስ (ADHD -attention deficit hyperactivity disorder) ችግር በብዛት የሚታይባቸው ልጆች በሀገሪቱ ቁጥራቸው መጨመሩን ዛሬ አስታወቀ።

የሀገሪቱ የማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ቃል የስዊድን የጤና እና ደህንነት ቦርድ መረጃ ADHD ተብሎ የሚገለጸው #የአእምሮ_ጤና_ችግር እ.ኤ.አ. ከ2022 ጀምሮ 10 በመቶ በሚሆኑ ወንዶች ልጆች ላይ እንዲሁም 6 በመቶ በሚሆኑት አዳጊ ሴት ልጆች ላይ በምርመራ መታየቱን ይፋ አድርጓል።

የችግሩ ተጋላጭ ልጆች ቁጥር ሊጨምርም ይችላል ተብሏል።

በመላው ዓለምም ከ5 እስከ 7 በመቶ የሚሆኑ ልጆች ለዚህ ችግር የተጋለጡ ናቸው።

ለዚህ ችግር የሚያጋልጡ ምክንያቶች ፦
- የተለያዩ እንደ ሊድ ወይም እርሳስ ባሉ ማዕድናት የተበከለ አካባቢ መኖር፣
- በእርግዝና ወቅት መድኃኒቶች፣ አልኮል ወይም ሲጋራ / ትንባሆ ማጨስ ማዘውተር ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል።

ከዚህም በተጨማሪ በደም አማካኝነት በዘር የአእምሮ ህመሞችም ሊተላለፉ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው።

ይህ የአእምሮ ችግር (ADHD) ያለባቸው ልጆች ቁጥር ለምን እንደጨመረ መንስኤውን ለማወቅ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው።

#DeutscheWelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amhara

በነገው ዕለት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ይጀመራል።

በአማራ ክልል ውስጥ የተፈታኞች ቁጥር ከታቀደው በግማሽ እንደሚያንስ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

ቢሮው በዚህ ዓመት ከ200 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀመጡ አቅዶ ነበር።

ነገር ግን አሁን ፈተና ላይ ይቀመጣሉ የተባሉት  96 ሺህ 408 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ቀሪ 106 ሺህ ያክል ተማሪዎች ፈተና አይወስዱም።

አሁን ላይ ፈተናውን የማይወስዱ ተማሪዎች  ተምረው በመስከረም 2017 ዓ/ም በሁለተኛ ዙር ለመፈተን እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።

በነገ ዕለት ፈተና የሚጀምሩት ተማሪዎች ለፈተናው መቀመጥ የሚያስችላቸውን ትምህርት የተከታተሉ እንደሆኑ ቢሮው አሳውቋል።

ባለፉት በርካታ ዓመታት የሀገሪቱ ከፍተኛው ውጤት የሚመዘገብበት እና እጅግ በጣም ጎበዝ ተማሪዎች የሚገኙበት አማራ ክልል ዘንድሮ የሚጠበቅበትን ያክል ተማሪ ባለማስተማሩ ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዙር ፈተና ላይ መቀምጥ አልቻሉም።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ዘንድሮ ትምህርታቸውን መማር ከነበረባቸው 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች መካከል መማር የቻሉት 3.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው።

ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት አልተማሩም።

ይኸው እስከ ዛሬ ትምህርት ያልጀመሩ ዞኖች እና ወረዳዎች አሉ።

በቅርቡ ቢሮው ዓመቱን ሙሉ በሙሉ ጭራሽ ምንም ያልተማሩ ተማሪዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።

ተማሪዎች ካልተማሩባቸው መካከል ሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ዋነኞቹ ሲሆኑ ምንም አይነት ተማሪ / አንድም እንኳን ተማሪ የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደማያስፈትኑ መግለጹ ይታወሳል።

#AmharaEducationBureau
#NationalExam
#DeutscheWelle

@tikvahethiopia