ሰሞኑን " ዶላር በጣም ጨምሯል " በሚል የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ የንግዱ አካላት እጅግ እያማረሯቸዉ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ብለዋል።
" አሁን ላይ ነጋዴው እቃውን በሌሎች ነጋዴዎች ሱቅና በራሱ መጋዘን ሲያስቀምጥ አይናችን እያዬ እቃዉ የለም በሚል ዋጋ ሊጨምር ሲሞክር ማየት ያማል " ሲሉ ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ ፥ " እስከ 1,080 ብር የነበረዉ ዘይት 1380 ብር ሲገባ ዶላር ነው " አሉን " እሺ የቲማቲምና ሽንኩርቱስ ዋጋ መናር ከየት መጣ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።
1 ኪሎ ሽንኩርት ከ40 ብር ተነስቶ 90 ብር ቲማቲም 20 ብር የነበረው 40 እና 45 መግባቱን ጤፍም በኪሎ ከ10 ብር በላይ እንደጨመረ ጠቁመዋል።
ስሚንቶ ላለፉት ወራት ጥሩ ቢሆንም አሁን ላይ " የለም " እየተባለ እንደሆነ ገልጸዋል።
የነዳጅ ጉዳይ ግን በፊትም አንስቶ ፈተና ነበር አሁን ብሶበት ራስ ምታት ሆኖ ቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።
ሀዋሳ ላይ የገበያውን ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የተቋቋመ ግብረሀይል መኖሩን በመስማታችን የነዋሪዎችን ቅሬታ ይዘን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን አነጋግረናል።
እሳቸውም ፥ " አሁን ላይ እቃ በሚደብቁ እና አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ግብረሀይሉ ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው " ብለዋል
ግብረሀይሉ በሰራዉ ስራ ሁለት ማደያዎች እና 62 የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች የምግብ ግብአትና የብረታብረት አቅራቢዎች በ8ቱ ክፍለ ከተሞች መታሸጋቸዉንና እቃዎችም ተወርሰዉ ህገወጦቹ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል።
ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚገልጹት አዛዡ ማህበረሰቡም ህገወጦችን በመጠቆም የፖሊስን ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
° " ግንባታው እንዲቆም ተደርጎብናል " - መምህራን
° " ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል፤ ምርመራ ተጀምሯል " - የሀዋሳ ፖሊስ
ከሰሞኑን " በማህበር ተደራጅተን የምንገነባውን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በማስቆም እንዲገነባልን ውል የገባውን ተቋራጭ አሰሩብን " ያሉ የሀዋሳ ከተማ መምህራን ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
መምህራኑ " አመራሩ ሊደግፈን ሲገባ እየገፋን ነው " ብለዋል።
" በሀገሪቱ ጠ/ ሚኒስትር ሳይቀር ለመምህራን ድጋፍ ተደርጎ የቤት ባለቤት የምንሆንበት መንገድ ይመቻች በተባለበት በዚህ ወቅት መምህራን የሚገነቡትን ቤት አስቁሞ ተቋራጭን ማሰር መንግስትና መምህራንን ለማጋጨት የታሰበ ሴራ እንጅ ሌላ ምንም አይደለም " ብለዋል።
" ድርጊቱ አሳፋሪ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
መምህራኑ፤ ከሳምንት በፊት አመራሩ በመምጣት " በርቱ " እንዳላቸውና ከፌደራል ሳይቀር እንግዳ ጋብዞ ፣ እገዛ ልናደርግ ዝግጁ ነን " እንዳላቸው ተናግረዋል።
በድንገት ግን ተገልብጦ ስራው ህጋዊ አይደለም ማለቱን ጠቁመዋል።
" ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በውይይት ማስተካከል ይቻላል " የሚሉት መምህራኑ ለ9 አመታት የቆመ ቤት ድንገት መሰራት ሲጀምር ለማስቆም መሯሯጥ ከጀርባው ሌላ ዓላማ ያነገበ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።
መምህራኑ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያሰሩትን የህንጻ ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 መቀየራቸውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት የማህበራት ማደራጃ እና የከንቲባ ጽህፈት ቤት የሚያውቀው እንደሆነ ጠቁመዋል።
ይህ ሆኖ እያለ ግንባታው #እንዲቆም መታዘዙን ገልጸው ፤ " ወቅቱ መምህራን የሚደገፉበት እንጅ ጥሪታቸውን ያፈሰሱበትን የሚቀሙበት አይደለምና እንቅፋት የሆኑብን አካላት ሊተዉን ይገባል " ብለዋል።
" በህግ አምላክ እጃችሁን ከድሀው መምህራን ላይ አንሱልን ፤ ይህ ባይሆን ግን አደባባይ በመውጣት ጩኸታችንን ለማሰማት ዝግጁ ነን " ሲሉም ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማው አስተዳደር ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በአጠቃላይ ለስድስት የመምህራን መ/ቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት የጻፈውን ደብዳቤ ደርሶት ተመልክቷል።
በዚህም ደብዳቤው ፦
- የነበረው ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 ማስተካከያ እንዲደረግ ተጠይቆ የG+4 ዲዛይን መሰጠቱ ፤
- ነገር ግን ይህ ዲዛይን የመምህራን መ/ቤቶች ማህበራት ከተደራጁበት አላማ አንጻር ተጻራሪ ዓላማ እንዳለው ስለተደረሰበት የG+4 ዲዛይን መሰረዙን ሌላ ደብዳቤ እስኪላክላቸው ድረስ ቀድሞ በነበረውም G+3 ዲዛይን ግንባታ ማካሄድ እንደማይችሉ ያዛል።
የመምህራኑን ጥያቄ ይዘን ጥያቄ ያቀረብንለት የከተማው ፖሊስ ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደዉ ምርመራ እንደጀመሩበት በመግለጽ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gamo : ሰሞኑን ለሶስት ተከታታይ ቀናት በጣለ ከባድ ዝናብ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካምአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል። መረጃው የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ነው። @tikvahethiopia
#Update
" አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው " - በጋሞ ዞን የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ
በጋሞ ዞን፣ ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካማአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ በደረሰ የናዳ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይወቃል።
ከዚህ ባለፈ ደግሞ ከሰላሳ ሰባት በላይ የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል ፤ 15 ቤቶችም መፍረሳቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።
የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን ካማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የሟቾችን ቀብር ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በክብር አስፈጽመናል " ብለዋል።
በአካባቢዉ ችግር ይከሰታል የሚል ቅድመ ትንበያም ይሁን ግምት ፈጽሞ እንዳልነበር ይልቁኑ በቀርከሀ የተሞላ ደን እያለ አደጋዉ መከሰቱ ሁኔታዉን አስደንጋጭ አድርጎታል ሲሉ ገልጸዋል።
አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል መሆናቸዉን የገለጹት አስተዳዳሪው በአንድ ቤት ዉስጥ ከነበሩት ሰባት ሰዎች ውስጥ በጓዳ የነበሩት አራቱ ሞተው ሶስቱ ከጓዳ ወጭ የነበሩት መትረፋቸውን ነግረውናል።
የሟቾች ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመ በኃላ ወደ ቀጣይ ተግባር ተገብቷል ሲሉም ገልጸዋል።
አሁን ላይ የዝናቡ መጠን ከፍ እንደሚል መረጃ ማግኘታቸውን ተከትሎ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት እንቅስቃሴ መጀመሩንና የአካባቢውን ሰው በማሸሽ በአጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች የጤና ኬላዎችና የእምነት ቦታዎች ማሳረፍ መጀመሩን አመልክተዋል።

" ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት…
የእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ጉዳይ የት ደረሰ ?
የባህር ዳር ከነማው የመሀል ሜዳ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከወራት በፊት አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ " የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ያለው የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ " ጉዳዩን በፍጥነት በማጣራት በቅርብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የደረስኩበትን አደርሳለሁ " በማለት ቃል ገብቶ ነበር።
ይሁንና በጉዳዩ ላይ ሀምሌ ወር ውስጥ መግለጫ ይሰጣል መባሉ በተጨማሪ ለእስር የተዳረጉት የተጫዋቹ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውን ተከትሎ ጉዳዩ የት ደረሰ ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ያቀረበለት የጋሞ ዞን ፍ/ቤት ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት አለመመራቱንና ክስ ባልተከፈተበት በጉዳዩ ላይ መረጃ መስጠት እንደማይችል ገልጾልናል።
ይህንንም ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ጉዳዩን እንደያዙትና ከምርመራ በኋላ የተደረሠበትን ጉዳይ ለህዝብ እንደሚያደርሱ ቃል የገቡልን በወቅቱ የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩትን ኢንስፔክተር አብርሀምን አነጋግረናቸው ነበር።
አዛዡ በወቅቱ የሟችን ቤተሰቦች በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያካሄዱ እንደነበር አስታውሰው አሁንም ጉዳዩ ምርመራ ላይ እንደሆነ በመግለጽ ከቦታው በመነሳታቸው እንዲሁም የፖሊስ አሰራር በዚህ ሰአት መረጃ መስጠትን ስለሚከለክል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አሁንም ይከታተላል።

" መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " - የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን
" በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ
ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በደረሰን የቅሬታ መልእክት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸዉ በመግለጽ በተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ መሳተፍ እንዳልቻሉ ነግረዉናል።
መምህራኑ እንደሚሉት አሁን ላይ ከፊሉ በመንግስት አቅም ማሻሻያ ፕሮግራሞች ግማሹ ደግሞ በራሱ ፍላጎት ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ቢያቀናም ደሞዝ አለመለቀቁን ተከትሎ ግን ችግር ላይ ወድቀዋል።
አሁን ላይ በገቡባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ አላማቸዉን ካለማሳካታቸዉ ባለፈ ጥለዋቸዉ የመጡ ቤተሰቦቻቼዉ ረሀብ ላይ መዉደቃቸዉን ተከትሎ የሄዱበትን የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ጥለዉ ለቀን ስራ መዳረጋቸዉን ይገልጻሉ።
ከዚህ በተጨማሪ በትራንስፖርት ችግር ምክኒያት ብዙ መምህራን በሚያስተምርበት አካባቢ ቢቀሩም በእንቅርት ላይ እንዲሉ ባሉበት አካባቢም የወባ ወረሽኝ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።
ችግሩን የመንግስት አካላት ያዉቁታል የሚሉት የጎሪጌሻ የሜኒት ማጅና ቱም የጎልዲያና ሻሻ እንዲሁም የጋቺት እና ሱርማ ወረዳ ቅሬታ አቅራቢዎች " መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " ብለዋል።
በጉዳዩ ላይ ከቀናት በፊት ያነጋገርናቸዉ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊዉ አቶ በበኩላቸዉ በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል ብለዋል።
ሀላፊዉ አክለዉም ምናልባትም ችግሩ የበጀት ከሆነ አሁን ላይ በየወረዳዉ ግብር እየተሰበሰበ በመሆኑ በተቻለ ፍጥነት ችግሩ ይፈታል በማለት የደሞዝ ችግሮ በቅርቡ እንደሚፈታ ገልጸዉልናል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
ሲዳማ !
" የማዳበሪያ ችግር የለም ተብሎ በሚዲያ ቢነገርም በቂ ማዳበሪያ እየደረሰን አይደለም " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች
ከሰሞኑ " ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አይሰጣችሁም ተባልን " ያሉ የሀዋሳ ዙሪያ አርሶ አደሮች ቅሬታ ማቅረባቸዉን ዘግበን ነበር።
በወቅቱ የማዳበሪያ ችግር እንደሌለና ወደግብርና ቢሮ በመምጣት መዉሰድ እንደሚቻል ከምርጥ ዘር ጋር በተያያዘ አርሶአደሩን የሚጠቅም አካሄድ መሆኑን ይሁንና ገበሬዉ የራሱ ዘር ካለዉ እንደማይገደደ ተገልጾም ነበር።
ይሁንና ከመረጃዉ በኋላ " የማዳበሪያ ችግር የለም " ተብሎ በሚዲያ ምላሽ ከመሰጠቱ በላይ በስብሰባ ወቅት " መጋዝናችን ሙሉ ነዉ " ብንባልም በአግባቡ እየተሰጠን አይደለም ሲሉ በድጋሜ የአካባቢዉ አርሶአደሮች ቅሬታ አቅርበዉልናል።
" አሁን ላይ የዘር ወቅት እያለፈ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ገብተናል " የሚሉት አርሶ አደሮቹ " አራትና አምስት ኩንታል ለሚያስፈልገዉ አምስት ሄክታር የለሰለሰ ማሳ አንድ ኩንታል ብቻ ስለምን እንደሚሰጠን አይገባንም " በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
" ማዳበሪያዉ በቂ አለመሆኑን የአካባቢዉ የግብርና ባለሙያዎች ያውቃሉ። እንደኛ ከማዘን ዉጭ መፍትሄ መስጠት አልቻሉም " ሲሉ ገልጸዉ ጉዳዩ በአመራሩ እጅ መያዙን አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ፥ " ቀኑን ሙሉ ስራ በመፍታት መጋዝን በር ላይ የሚዉለዉ አርሶ አደር ሀያ ሰላሳ ሰዎች ከተስተናገዱ በኋላ ወደቤታችሁ ሂዱ ይባላል በማለት መጋዝኑን የሞላዉ ማዳበሪያ ለማን ነዉ ? " በማለት ጠይቀዋል።
ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " የማዳበሪያ ችግር የለም ከአካባቢዉ አርሶ አደር ጋርም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል " ያሉት የወረዳዉ አስተዳዳሪ " መሬቱን ያዘጋጀ ገበሬ የፈለገዉን ያክል ማዳበሪያ መዉስድ ይችላል " በማለት አንዳች ቅሬታ ያለበት አርሶ አደር ካለ ሊያናግረን ይችላል ማለታቸዉ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ታጣቂዎቹ ተመልሰው ይመጣሉ በሚል አሁንም በፍርሀት ውስጥ ነን " - የሰገን ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች
ከሰሞኑ በወረዳው ዋና ከተማ ሰገን በድንገት ከወደደራሼ አቅጣጫ ተነስተው መጥተዋል ከባሉ ታጣቂዎች በፖሊስ ፣ በከተማው አስተዳደርና ፣ በንጹሀን ዜጎች ላይ በከፈቱት ጥቃት ከ10 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸዉን ተሰምቷል።
ቅዳሜ አመሻሽ ጀምሮ ጥቃቱ መከፈቱን የገለጹት ነዋሪዎች በከተማዉ ውስጥ የነበሩ ፖሊሶችና የአስተዳደር ቢሮ የጥቃቱ ኢላማና ቀዳሚ ሰለባ ከመሆናቸው በላይ የመጀመሪያ ዙር ጥቃት እንደተፈጸመ ድጋፍ የሚሰጥ ሀይል ከተለያዬ ቦታ ወደስፍራዉ በፍጥነት አለመላኩን ተከትሎ ሁለተኛ ዙር ጥቃት በበነጋታዉ ጠዋት መከፈቱን አስረድተዋል።
የወረዳው ነዋሪዎች " የሰው ነፍስና በርካታ ንብረት መዳን ሲችል ጉዳት ደርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።
እስከእሁድ ጠዋት በቀጠለዉ ተኩስ ሱቆች መዘረፋቸውን ፣ ቤቶች መቃጠላቸዉና አካባቢው አስፈሪ መልክ መያዙን ተከትሎ አሁን ላይ በርካታ ሴቶችና ህጻናት ወደአጎራባች መንደሮች እየተሰደዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
" ከሀይቤና ቀበሌ በመነሳት የተለመደ የከብት ዘረፋና የነብስ ማጥፋት ወንጀሎች ነበሩ " ያሉት ነዋሪዎቹ " ካሁን በፊት ሁኔታውን መንግስት ይቆጣጠረዉ ዘንድ ጥያቄ ማንሳታቸውን ለአብነት እንኳን ከሳምንት በፊት በወረዳው አስተዳደር ከማህበረሰቡ ጋር በነበረው ስብሰባ መነሳቱን " ገልጸዋል።
አሁንም ቢሆን ድንገት በመምጣት ጥቃት ያደርሳሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
" ሁኔታዉ ከቁጥጥር ዉጭ ከመሆኑ በፊት ከወረዳው ባለፈ የዞንና የክልል አመራሮች ጣልቃ መግባት አለባቸው " በማለት " ቤታቸዉ ለተቃጠለባቸውና ንብረታችዉ ለወደመባቸው ግለሰቦች ዝናብ ላይ በመሆናቸው አፋጣኝ ድጋፍ እንፈልጋለን " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
" ነዋሪዎቹ የመንግስት ኃይሎች ለእርምጃ መዘግየት ዋጋ አስከፈለን ሲሉም " አክለዋል።
ግጭቱን አስመልክተዉ የሰገን ዙሪያ አስተዳዳሪ አቶ ኡርማሌ ኡጋንዴ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገጅ በሰጡት ቃል አስራ አንድ ሰው መሞቱን ጠቁመዋል።
ነዋሪዎቹ ግን የሟቾቹን ቁጥር አስራ ሶስት በማድረስ ስምንቱን ነዋሪ አምስቱ ደግሞ ፖሊስ መሆናቸዉን ገልጸዉ ከዚህም ሊያልፍ ይችላል ብለዋል።
አሁን ላይ ከወረዳዉ ባለፈ በዞኑ ደረጃ የኮንሶ ዞን የሀዘን መግለጫ በማዉጣት ሁኔታዉን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የዞኑን ህዝብ ግንኙነት ቢሮና የፖሊስ መምሪያ ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም።
ዞኑ " ጽንፈኛ እና አሸባሪ " ያላቸው ኃይሎች በኮንሶ ዞን የሰገን ዙሪያ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ንጹሃን ሰዎችና የፖሊስ አባላት መገደላቸውን አረጋግጧል።
ምን ያህል ሰው እንደተገደለ የሰጠው ቃል የለም።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Omo
የኦሞ ወንዝ ሙላት ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን ተከትሎ የአካባቢው አርሶአደር በ4ቱም አቅጣጫ ንብረቱን ጥሎ መሸሽ ላይ ነው።
ችግሩ እንደሚከሰት ታውቆ በርካታ ስራ ሲሰራ ቢቆይም የኦሞ ወንዝ መጠን ከተለመደውና ከታሰበው ውጭ መሆኑን ተከትሎ ግን ለዞኑ መንግስትም ሆነ ለግብረሰናይ ድርጅቶች ሁኔታው ከባድ ሆኖባቸዋል።
የወንዙ ሙላት ከባድ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ አርብቶ አደሩን በአራት ጊዜያዊ መጠለያ እንዳስቀመጡትና ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያሻዉ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማልኮ ገልጸው " በአሁኑ ወቅት የውሃው መጠን ከተለመደው ውጪ እየጨመረና ሰፊ ቦታ እየያዘ ከመምጣቱ የተነሳ ለኦሞራቴ ከተማ ማህበረሰብ እንደሚያሰጋ " ተናግረዋል ።
ችግሩ እየባሰ የመጣው የውሃውን አቅጣጫ የማስቀየርና የማፍሰስ ስራዎች በኢንቨስተሮች እርሻ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያስከተለ ነው በሚል በጅምር በመቆሙ መሆኑን የሚያነሱት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በበኩላቸው ችግሩ በየአመቱ የሚፈጠር በመሆኑ ኑሯቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገዉ ይገልጻሉ።
በመሆኑም አሁን ላይ ማህበረሰቡ ቤቱ እየተዋጠበት ከብቱ እየሞተበትና የሚቀምሰውም በመጥፋቱ ተስፋ በመቁረጥ አካባቢውን ጥሎ መሸሽ መጀመሩ ተሰምቷል።
ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኦሞ ወንዝ ሙላት ጋር ተያይዞ በአከባቢው በተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሲከሰት እንደነበር የገለጹት የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ በበኩላቸው አምና ከ79 ሺህ በላይ አርብቶ አደሮች በወንዙ ሙላት መጥለቅለቅ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን ይናገራሉ።
እነዚህ አርብቶ አደሮች እስከ ዛሬ በጊዜያዊ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ የተደረገ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ታደለ ለእርሻ ስራ በሚል ወደ ቀድሞ ቀያቸው በተመለሱት ላይ አሁንም ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል ።
አሁን ላይ ወንዙ መደበኛ የፍሰት አቅጣጫውን በመልቀቅ የጉዳት መጠኑን አስፍቶና አርብቶ አደሩን አፈናቅሎ ለማህበራዊ ችግር እየዳረገ ሲሆን በኢፌዴሪ ውሃና ኢነሪጂ ሚኒስቴር አማካኝነት ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመረው የመከላከያ ፕሮጀክት መፍትሄ ያመጣል ቢባልም ሊጠናቀቅ አልቻለም።
በዚህ ምክኒያትም አሁን ላይ በ33 ቀበሌዎች የነበሩ መሠረተ ልማቶች ትምህርት ቤቶች ጤና ኬላዎችና መኖሪያ ቤቶች በውሃ ሊከበቡና ነዋሪው ለከፋ ችግር ይጋለጥ ዘንድ ምክኒያት ሆኗል።

#Omo የኦሞ ወንዝ ሙላት ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን ተከትሎ የአካባቢው አርሶአደር በ4ቱም አቅጣጫ ንብረቱን ጥሎ መሸሽ ላይ ነው። ችግሩ እንደሚከሰት ታውቆ በርካታ ስራ ሲሰራ ቢቆይም የኦሞ ወንዝ መጠን ከተለመደውና ከታሰበው ውጭ መሆኑን ተከትሎ ግን ለዞኑ መንግስትም ሆነ ለግብረሰናይ ድርጅቶች ሁኔታው ከባድ ሆኖባቸዋል። የወንዙ ሙላት ከባድ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ አርብቶ አደሩን በአራት ጊዜያዊ…
#ALERT🚨
⚠️ " በውሀ ተውጠን ከማለቃችን በፊት ድረሱልን " - የኦሞራቴ ከተማ ነዋሪዎች
🔴 " የውሀው አመጣጥ እጅግ አስፈሪ ነው ፤ የፌደራል መንግስት ማሽነሪዎች ቶሎ እንዲያቀርብልን እየጠየቅን ነው " - የአካባቢዉ አስተዳደር
የኦሞ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ ሀብት ንብረቴ የሚላቸዉ ከብቶች ማለቁን ያየዉ የደቡብ ኦሞ አርብቶ አደር በአራቱም አቅጣጫ እየተሰደደ መሆኑን ጠቅሰን አካባቢው ትኩረት ይሻል ስንል ከቀናት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።
ይሁንና አሁን ላይ የኦሞ ወንዝ ከአቅም በላይ በመሙላቱና የአካባቢዉ መሬት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መተኛቱን ተከትሎ የወረዳዉ ዋና ከተማ የሆነችዉን ኦሞራቴን ደሴት ሲያደርጋት ህዝቡም መዉጫ በማጣት ጭንቀት ውስጦ መግባቱን ሰምተናል።
የድረሱልን ጥሪያቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረሱት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ለአመታት በወንዙ ሙላት ሲቸገሩ መቆየታቸውንና አሁን ግን ከርቀት ወደምትገኘው ኦሞራቴ ከተማ በእጅጉ መጠጋቱ እንዳስደነገጣቸው በመግለጽ ከመዋጣቸው በፊት የሚመለከተዉ አካል እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል።
በአካባቢው የነበሩት አርብቶ አደሮች በበኩላቸው ሙሉ በሙሉ የግጦሽ መሬቶች በወንዙ ተቆርሶ መወሰዱንና ከብቶቻቸው ማለቃቸውን ገልጸዉ አሁን ላይ የተጠለሉባቸው ጊዜያዊ መጠለያዎች በውሀው እየተጥለቀለቁ በመሆኑ ህይወታቸዉ አደጋ ላይ መውደቁን አስተድተዋል።
ስለሁኔታዉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡን የወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ " የዉሀዉ አመጣጥ እጅግ አስፈሪ ነው " ብለዋል።
ማህበረሰቡ አፈር በማዳበሪያ እየቋጠረ ግድብ መስራቱ ውሀውን ስላላስቆመው የፌደራል መንግስት ማሽነሪዎች ቶሎ እንዲያቀርብልን እየጠየቅን ብለዋል።
" አሁን ላይ የኦሞራቴ ከተማ ከጊዜያዊ መጠለያዎችም ሆነ ራቅ ካሉ አካባቢዎች ለመገናኘትም ሆነ ለመሸሽ ቱርሚን የሚያገናኘዉ ድልድይ በመሰበሩና ወደኬኒያ የሚወስደዉ ዋና መንገድ በውሀው ክራክ በማድረጉ ደሴት ሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።
በመሆኑም " የኦሞራቴ ህዝብ የከፋ ችግር ላይ በመሆኑ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ድጋፍ ሊያደርግለት ይገባል ሲሉ " ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ድምጻቸውን ለማሰማት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተሰባስበው በመመካከር ላይ የነበሩ መምህራን በፖሊስ ተበተኑ።
በወላይታ ዞን ስር ያሉ መምህራን " ሀሳባችን እንዳንገልጽ ፖሊስ አደናቀፈን " ሲሉ ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
" ወደመንግስት አካላት በመሄድ ረሀባችን እወቁልንና ደሞዛችን በወቅቱ ክፈሉን በማለት ልናሳዉቅ እንጅ ረብሻ ለመፍጠር አልነበረም ተሰባስበን ስንመካከር የነበረው " የሚሉት መምህራኑ " ከረሀባችን በላይ ተሰባስበን በመመካከር ድምጻችን እንዳናሰማ መደረጉ አሳዝኖናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ላለፉት 3 ወራት ያለደሞዝ ቆይተን የሰኔን ብቻ ሰጥተውናል ይሄ ለመምህራን ችግር ግድ የለሽ መሆናቸውን " አሳይቶናል ብለዋል።
አሁን ላይ በዱቤ ይሰጡን የነበሩ ነጋዴዎችም መከልከል በመጀመራቸዉ ተቸግረናል ሲሉ ለቲክቫህ አስረድተዋል።
" ስራቸውን ለመስራትና የባለስልጣናቱን ትእዛዝ ለመፈጸም የመጡ ፖሊሶች እንኳን ረሀባችሁን እኛም እናውቀዋለን " በማለት እያዘኑ በተኑን በማለት ሀዘናቸውን የገለጹት መምህራኑ " ከዚህ በላይ ሞት እንጅ ሌላ ተስፋ እየታየን አይደለም " ሲሉ ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።
" በመሆኑም አሁን ላይ በፖሊስ በመገፋታችንና ባለስልጣናቱም ስብሰባ ገቡ በመባላቸዉ ወደመጣንባቸው አካባቢዎች ብንመለስም ረሀባችን የከፋ መሆኑን ለመግለጽ ተጠናክረን መጮሀችን ይቀጥላል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በክልሉ ስላለዉ የመምህራን ደሞዝ መዘግየትና መቆራሪጥ ላነሳንለት ጥያቄ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ወረዳዎች ከገቢያቸዉ ክፍያ የሚፈጽሙበት አስራር መዘርጋቱንና ችግሮች ከተፈጠሩ ጣልቃ በመግባት እርማት እንደሚደረግ መግለጹ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM