TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ በ6 ወራት ለ66 ሺህ 741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” - አማኑኤል ሆስፒታል

አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 ዓ/ም፣ “ በ6 ወራት ለ66,741 የማህበረሰብ ክፍሎች የሥነ አዕምሮ ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዚህም 64,256 የተመላላሽ፣ 257 ህፃናት የአዕምሮ፣ 410 ሰዎች የሱስ ህክምና መሰጠቱን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አብዩ የኔአለም ገልጸዋል።

እንዲሁም ለ240 የተሃዲሶ፣ ለ921 የአስተኝቶ፣ ለ1,564 ሰዎች ደግሞ የድንገተኛ የህክምና አገልግሎት መሰጠቱን አቶ አብይ አስረድተዋል።

በተመላላሽ፣ በአስተኝቶና በድንገተኛ የህክምና አገልግሎት ከተሰጣቸው ታካሚዎች መካከል 36,300 የጤና መድን ተጠቃሚዎች መሆናቸው ተመልክቷል።

በተመላላሽና በተኝቶ ህክምና በስድስት ወራት የወንጀልና የፍትሃ ብሔር ተመርማሪ ለሆኑ 413 የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱም ተገልጿል።

“ በሆስፒታሉ አማካኝ አስተኝቶ የቆይታ ጊዜ በ2016 ዓ/ም ከነበረው 36 ቀናት በ2017 ዓ/ም 6 ወራት ወደ 33 ቀናት ማድረስ፣ የአልጋ የመያዝ ምጣኔም በመጀመሪያ 6 ወራት መጨረሻ ላይ 85.2% መፈጸም ተችሏል ” ተብሏል።

ሆስፒታሉ ከ1930 ዓ/ም ጀምሮ በተኝቶ፣ በተመላላሽ፣ በድንገተኛ፣ የጭንቅላት ምርመራ፣ በኤሌክትሪክ ንዝረት፣ በህፃት የአዕምሮ፣ ከህግ ጋር የተያያዙ የአዕምሮ ህክምናና ምርመራ እንዲሁም የነርቭ ህክምናዎችን እየሰጠ የሚገኝ አንጋፋ ሆስፒታል ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ብሩህ እናት !

ሴቶችን እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያሸልም “ ብሩህ እናት ” የተሰኘ የፈጠራ ውድድር መዘጋጀቱ ተገለጸ።

የሴቶችን ድካም የሚያቀሉ ቴክኖሎጂ ተኮር የፈጠራ ሀሳቦችን በማቅረብ ለሚያሸንፉ ሴቶች ቋሚ ችግር ፈቺ ተቋም የሚሆኑበትና ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ብር የሚያሸልም ውድድር ለሴቶች ብቻ ማዘጋጀቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገልጿል።

የፈጠራ ውድድሩ የተዘጋጀው ከኢንተርፕርነሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከእናት ባንክ፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ ጋር በጋራ በመሆን መሆኑን መስሪያ ቤቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በዚህም “ ማሰልጠን፣ መሸለም፣ ማብቃት ” በሚል መሪ ሀሳብ በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ ላሉ ሴቶች እድሉ እንጀተመቻቸ፣ ከተመዘገቡት 5ዐ የተሻለ ሀሳብ ላቀረቡ ተወዳዳሪዎች ስልጠና እንደሚሰጥ አመልክቷል።

“ ፕሮግራሙ ላይ የላቀ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ሴቶች ተወዳዳሪዎች መከካልም 10 ለሚሆኑት አሸናፊ የቢዝነስ ሀሳብ ፈጣሪዎች እውቅናና የገንዘብ ሽልማት እንዲያገኙ ይደረጋል ” ሲል መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል።

ለውድድሩ አሸናፊዎች ሽልማቱ ምንድን ነው ?

ከተመዝጋቢዎቹ የተሻለ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሀሳብ ያቀረቡ 1ዐ ተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ሽልማት መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በገለጻው መሠረት፣ ለ1ኛ አሸናፊ 500 ሺሕ፣ ለ2ኛ አሸናፊ 400 ሺሕ፣ ለ3ኛ አሸናፊ 300 ሺሕ፣ ለ4ኛ አሸናፊ 200 ሺሕ፣ ለ5ኛ አሸናፊ 150 ሺሕ እንዲሁም ከ6 እስከ 10ኛ ላሉ አሸናፊዎች 100 ሺሕ ብር ይሸለማሉ።

በመግጫው የተገኘው እናት ባንክ በበኩሉ፣ ለአሸነፉበት ሴቶች ቴክኖሎጂ ተግባራዊነት የሚያስፈልገውን የገንዘብ ብድር እንደሚያመቻች ገልጿል።

ምዝገባው መቼ ተጀምሮ ? መቼ ይጠናቀቃል ?

ምዝገባው ከዛሬ (ሰኞ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ጅምሮ እስከ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ደረስ እንደሚከናወን ተነግሯል።

ለተወዳዳሪዎች የቡት ካምፕ ስልጠና ከመጋቢት 8 እስከ መጋቢት 19/2017 ዓ/ም እንደሚሰጥ እና የውድድሩ ማጠቃለያና ሽልማት መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሚሆን ተመላክቷል።

ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://shorturl.at/8g9mv

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
“የተነሳበትን አካባቢ ጉዳት አድርሷል። ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም” - ባለስልጣኑ

በአፋር ክልል ሃላይዳጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርክ ከተነሳ ቀናት ያስቆጠረው ቃጠሎ በቁጥጥር ሥር ባለመዋሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ናቃቸው ብርሌው በሰጡን ማብራሪያ፣ የእሳት ቃጠሎ በተነሳበት አካባቢ ጉዳት እንዳደረሰ፣ የጉዳት መጠኑን የሚታወቀው ቃጠሎው ሲቆም መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ናቃቸው በዝርዝር ምን አሉ ?

“ በእርግጥ ብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ነው የእሳት ቃጠሎው የተነሳው። ምክንያቱ በሂደት የሚጣራ ቢሆንም በሰው ሰራሽ ምክንያት እንደተከሰተ ነው የሚገመተው።

በባሕሪው ብሔራዊ ፓርኩ ሳራማ ምድር (Grass land) ነው። ለመቆጣጣር አስቸጋሪ እንደነበር ነው ያገኘነው መረጃ የሚያሳየው።

በአካባቢው አውራ ጎዳና መንገድ የሚሰሩ፣ የአፋር ብሔራዊ ክልል ከአሚባራ ወረዳ ጋር በመተባበር የፍየር ብሬኪንግ (የመጥረግ፣ የመቁረጥ ስራ) በግሬደር እየተሰራ ነው።

ፋየር ብሬኪንግ ተርቷል እሳቱ ወደ ሌላኛው ክፍል እንዳይዛመት የመጥረግ ሥራ እየተሰራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

አሁንስ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ውሏል ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ “ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ፣ ወደልላኛው የፓርኩ ክፍል እንዳይስፋፋ ነው የቆረጣ ሥራ የሚሰራው ሳሩ ልክ የመንገድ ያክል በግሬደር እየተቆረጠ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

“ የተነሳበትን አካባቢ ጉዳት አድርሷል። ግን አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እስካሁን በቃጠሎው በምን ያክል ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ “ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር ሲውል ወይም መጥፋቱ ሲረጋገጥ የጉዳቱ አይነቱና መጠኑ የሚታወቀው ያኔ ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

“ እስቲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የሰው ኃይል የሎጂስቲክስ ድጋፍ በማድረግ፣ ባለሙያዎችን በመመደብ በአዋሳኝ የሚገኘው የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ተሽከርካሪዎችን ጭምር በመውሰድ እሳቱን ለሚያጠፉ ኃይሎች ድጋፍ እየተደረገ ነው ” ብለዋል።

ሰሞኑን በተለያዬ ፓርኮች እየተከሰቱ ያሉ የእሳት ቃጠሎን ምንነት ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽም፣ “ በእርግጥ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች የሚከሰቱት ከወቅቱ ጋር ተያይዞ ነው። ከፍተኛ ሙቀት፣ ደረቅ የአየር ሁኔታ ስላለ ” ነው ያሉት።

“ እነዚህ ጥብቅ ቦታዎች በባህሪያቸው ደንም ይሁን ሳር ስላላቸው ትንሹም ቃጠሎ በቀላሉ የመስፋፋት እድል አለው። ብዙዎቹ የሚስተዋሉትም በተፈጥሮ አይደለም በሰው ሰራሽ ነው የሚሰቱት ” ብለዋል።

ማህበረሰቡ እሳት ቃጠሎ ሲያጋጥም በማጥፋት እንደሚተባበር፣ ከማህበረሰቡ ውስጥ እንዲህ አይነት ድርጊት የሚፈጽሚ አንዳንድ እንደማይጠፉ ገልጸው፣ " በጋራ ለመከላከል ሲከሰት ለማጥፋት የሚደረገውን ሁሉ ጥረት በህገ ወጦች ላይ በማተኮር ሁሉም ኃላፊነቱን ቢወስድ ” ሲሉ አሳስበዋል።

“ በአንዳንድ አካባቢዎች ሲኬድ ከግጥሽ ጋር የተያያዙ ናቸው። አዲስ ሳር እንዲያወጣላቸው የሚደረጉ ድርጊቶች አሉ። እናም የብዙኀንን ተሳትፎ ስለሚጠይቅ ሁሉም በኃላፊነት ቢከላከል ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

(ጉዳዩን ተከታትለን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ExitExam

🔴" የተፈተነው ፈተና ኮንተንቱ(ይዘቱ) ህክምና ያልሆነ ነው በትምህርት ሊገኝ የማይችል ነው " - ተፈታኝ ተማሪዎች

🔵" የተማሩት ነው የሚወጣው የተፈተኑትም ይህን መሰረት አድርጎ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ሃገር አቀፍ የመውጫ ፈተና (Exit Exam)  ከጥር 26-30/2017 ዓም በ 87 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱ ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፈተናው ከተጠናቀቀ በኋላ " ፈተናው ለፈተና ዝግጅት ከሚያግዘው ' ብሉፕሪንት ' ውጪ ነው ይዘቱም ከተማርነው ትምህርት ጋር የማይገናኝ ነው " የሚሉ ቅሬታዎችን ከተፈታኞች ተቀብሏል።

ከተለያየ የትምህርት ክፍል ፈተናውን የወሰዱ ተፈታኞች ፈተናውን ከብሉ ፕሪንት ውጪ የመጣ መሆኑን በመግለጽ ትምህርት ሚኒስቴር ምላሽ ይስጠን ብለዋል።

ቅሬታውን ካቀረቡ ተፈኞች መካከል የሆኑ የህክምና ተማሪዎች " የመጣው ፈተና በጣም ከስታንዳርዱ የወጣ የህክምና ተማሪዎችን የማይመጥን ነበር " ብለዋል።

አክለውም " የተፈተነው ፈተና ኮንተንቱ (ይዘቱ) ህክምና ያልሆነ ነው በትምህርትም ሊገኝ የማይችል ነው " ያሉ ሲሆን " የሚመለከተውን አካል ለማናገር ብንሞክርም ከውጤት በፊት ንግግር እንደማይኖር ተነግሮናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከእኛ በፊት አምና የተመረቁ ተማሪዎች የተፈተኑትን ፈተና ተመልክተናል ሰርተንም ስለገባን እናውቀዋለን ትክክለኛ ፈተና ነበር የተፈተኑት ይዘቶቹም ጥሩ ነበሩ  ዘንድሮ ምን እንደተፈጠረ አናውቅም የወጣው ፈተና ከህክምና ጋር የማይገናኝ ጥያቄ ይበዛው ነበር " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪ ከጤና ተማሪዎች ውጭ የፊዚክስ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከብሉ ፕሪንት ውጪ ተፈትነናል የሚለው ቅሬታ " ውሸት ነው " ብለዋል።

" ከስልጠና ፕሮግራም ብቃት (Competency) ውጪ የሚዘጋጅ አንድም ጥያቄ የለም " ያሉት ስራ አስፈጻሚው የተባለው ቅሬታ " ውሸት ነው ሪፖርትም አልቀረበልንም እንደዚህ ብሎ የጠየቀንም የለም ከኮምፒተንሲ ውጭ የሚወጣ ፈተና የለም " ነው ያሉት።

አክለውም "ፈተናው ከብቃት ጋር የተገናኘ ከሁለተኛ ዓመት እስከ መጨረሻ ዓመት የተማሩት ነው የሚወጣው የተፈተኑትም ይህን መሰረት አድርጎ ነው " ብለዋል።

" ጥያቄው ከዚህ ውጪ ወጣ የሚል ቅሬታ ከሱፐር ቫይዘር፣ ፈታኝ ፣ተማሪ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የቀረበልን አንድም ሪፖርት የለም መረጃው የለንም ሪፖርቱም አልቀረበልንም " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሃገር አቀፉ የመውጫ ፈተና ውጤት ነገ አልያም ከነገ በስቲያ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር መስማቱን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ህብረቱ ፥ ሚኒስቴሩ ከComprehensive Nursing የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የቀረበ ቅሬታን እያጣራ እንደሚገኝ አስረድቷል።

ረቡዕ ወይም ሐሙስ አጠቃላይ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ እንደገለጸለት ህብረቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 26 ሰዎች ወዲያ ነው ህይወታቸው ያለፈው። ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል " - ፖሊስ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ፤ ጉዳያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አደጋው ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡ በደረሰው አደጋ የ26 ወገኖቻችን ሕይወት ወዲያው ሲያልፍ 42 ወገኖቻችን ላይ ደግሞ…
#Update

“ አደጋው በጣም አሰቃቂ ነው። 28 ሰዎች ሞተዋል። 45ቱ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” - የኦሮሚያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ ደረሰ በተባለው የትራፊክ አደጋ፣ እስካሁን የሟቾች ቁጥር 28 መድረሱን የኦሮሚያ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ኮሚሽኑ ስለአደጋው መንስኤ በሰጠን ቃል፣ “የፊት ጎማው በሮ ወጥቶ ነው። በፍጥነት ላይም ነበር። የፍሬን ቴክኒክ ችግር እንዳለም መረጃ አለ” ብሏል።

የሟቾች ቁጥር ከ26 ጨመረ እንዴ? ስንል የጠየቅናቸው የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋና መረጃ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሰለ አበራ፣ “እስካሁን ባለው መረጃ የሟቾች ቁጥር 28 ነው” ብለዋል።

“ ከባድ አደጋ የደረሰባቸው 45 ሰዎች ናቸው። እነርሱም በባኮ ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው ” ነው ያሉት።

የደረሰባቸው ጉዳት ቀላል ጭምር ነው ወይስ ከባድ ብቻ ነው ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ ዋና ኢንስፔክተሩ፣ “ 45ቱም ከባድ አደጋ ነው የደረሰባቸው ” ሲሉ መልሰዋል።

“ ከሻምቡ ወደ አዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ማርሴዲስ ኮድ 3A 12661 መኪና ጉደያ ቢላ ወረዳ ጎንካ ኢጃ ቀበሌ ጅማ ወንዝ የሚባል ልዩ ቦታ ነው የፊት ጎማው በሮ ገደል የገባው ” ሲሉም የአደጋውን መንስኤ ጨምር አስረድተዋል።

አክለው፣ “ የፊት ለፊት ጎማው በሮ ወጥቶ ነው። በፍጥነት ላይም ነበር። የፍሬን ቴክኒክ ችግር እንዳለም መረጃ አለ። ፓሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል ” ነው ያሉት።

የተሳፈሩ ሰዎች ስንት ነበሩ ? ጉዳት ሳይደርስባቸው የተረፉ ይኖሩ ይሆን? ስንል ላቀረብነው ጥያቄም፣ “ አሁን ባለው መረጃ 28 ሟች፣ 45 ከባድ ጉዳት አጠቃላይ ሹፌርና ረዳት፣ ተሳፋሪን ጨምሮ ነው። መኪያው ውስጥ የነበሩት እነዚሁ ናቸው ” ብለዋል ዋና ኢንስፔክተሩ።

“ አደጋው የደረሰበት ማርሴዲስ ተሽከርካሪ ስሪቱ በጣም የቆዬ በመሆኑ ለረጅም ርቀት መመደብ አልነበረበትም ” የሚል አስተያዬት ሲሰጥ ተስተውሏል፤ የፓሊስ አስተያዬት ምንድን ነው ? የሚል ተጨማሪ ጥያቄም አቅርበናል። 

ኢንስፔክተሩ፣ “እኛ ይሄ መረጃ አልደረሰንም። መንገድ ትራንስፓርት መረጃውን አይቶ ከመናኸሪያ የሚመድበው ስለሆነ ከትልቁ መናኸሪያ ነው ይሄ ስምሪት የሚሰጠው” ብለዋል።

“የሚመለከተው አካል፣ ፌደራል መንገድ ትራንስፓርት አይቶ ስሞሪት የሚሰጥ ስለሆነ እንደኛ እንዲህ አይነት ችግር ካለ እነርሱም ፍተሻ እንዲያደርጉና እንዲህ አይነት ርቀት ቦታም ባይመደብ ጥሩ ነው” ሲሉም አክለዋል።

የፍጥነትም ሆነ የቴክኒክ ችግር እንዲህ አይነት አደጋዎች እንዳይደገሙ ባስላለፉት መልዕክት፣ “ይሄ አሰቃቂ አደጋ ነው። እንደ ኦሮሚያ የደረሰው ከባድ አደጋ ነው። በድጋሚ እንዳይከሰት ባለ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ሳይሰማሩ በፊት የቲክኒክ ችግር ቢመረምሩ” ሲሉ አሳስበዋል።

ዋና ኢንስፔክሩ በምላሻቸው፣ “የቲክኒክ ችግር በጣም ለአደጋ ስለሚያጋልጥ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው መልዕክት የማስተላልፈው” ሲሉም አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" እያጠፋን በነበርንበት ወቅት የኤሊና እባብ ዝርያዎች ተቃጥለው አግኝተናል። ከ350 እስከ 400 ሄክታር ሳራማ ቦታ ተቃጥሏል ብለን እንገምታለን " - ፓርኩ

በሃላይደጌ አሰቦት እጩ ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የቆየውና ለቀናት ከቁጥጥር ውጪ ለማድረግ አስቸግሮ የነበረው ቃጠሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፓርኩና የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ይህን ተከትሎም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያክል እንደሆነ የጠየቀ ሲሆን፣ እንስሳት መቃጠላቸውንና ከ350 እስከ 400 ሄክታር የሚገመት ሳራማ ቦታ መቃጠሉን ሰምቷል። 

የፓርኩ ኃላፊ አቶ አሕመድ እንድሪስ ምን አሉ ? 

" የካቲት 1/2017 ዓ/ም መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ነበር። ትላንት 10 ሰዓት በቁጥጥር ስር ተደርጓል። ዛሬም ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምረን ጫካ ነበርን ሙሉ በመሉ መጥፋቱን አረጋግጠናል።

ተራማጅ የሆኑና መሮጥ የሚችሉ የዱር እንስሳት ብዙዎቹ አምልጠዋል። ግን መራመድ የማይችሉ፣ አዲስ የተወለዱ የዱር እንስሳት ጉዳት ሊያደርስ ችሏል።

እያጠፋን በነበርንበት ወቅት የኤሊና እባብ ዝርያዎች ተቃጥለው አግኝተናል። ግን የጉዳቱን መጠን ሰርቨይ መሰራት አለበት "  ብለዋል።

የፓርኩ ምን ያክል ክፍል እንደተቃጠለ ታውቋል? ለሚለው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ፣ " መለካት ያስፈልጋል። ከ350 እስከ 400 ሄክታር ሳራማ ቦታ ተቃጥሏል ብለን እንገምታለን "  የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

" ደረቃማ ሳር ስላለ በትንሹ ነው የሚቀጣጠለውና በሰው ኃይል ለመቆጣጠር አስቸጋሪ አድርጎት፣ በሰው ኃይል ከመቆጣጠር በላይ ሆኖ ነው በግሬደርና፣ ከእሳቱ ርቆ በሎደር የማስራብ ሥራ የተሰራው” ሲሉ አስታውሰዋል።

ፖርኩ ወደ 244 የአእዋፍ ዝርያዎች፣ 42 አጥቢዎችና ሌሎች እንስሳት እንዳሉበት አስረድተው፣ “የተመሰረተው በኬንያና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኘውን ትልቁ የሜዳ አህያ ለመጠበቅ ነው” ብለዋል።

ኮቪድ ከመከሰቱ በፊት እስከ 200 ሺሕ፣ ኮቪድ ተከስቶ ከቆዬ በኋላ የቱሪስት ቁጥር በመቀነሱ ከ50 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ገቢ የሚገኝበት እጩ ፓርክ መሆኑ ተነግሯል።

ፓርኩ ከአዲስ አበባ በ27ዐ ርቀት ላይ ያለ፣ ኤሪያው 1099 ስኩየር ኪሎሜትር የሆነ፣ ወይራ፣ የሀበሻ ጽድ፣ ዝንባ የመሳሰሉ እፅዋቶች ያሉበት፣ 40 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሜዳ ላይ ያረፈ ሳር ያለበት ነውም ተብሏል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
🔊 #የሠራተኞችድምፅ

“ ያለፈቃዳችን ከአመት ደመወዛችን 100% እየተቆረጠብን ነው። ወዴት እንጩህ ? ” - ሠራተኞች

በምዕራብ አርሲ ዞን ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ ያሉ ጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች “አመራሮች ደመወዛችንን እንደፈለጉ ነው የሚቆርጡት። ለምን? ብሎ መጠየቅም አይቻልም” ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ምሬታቸውን አሰምተዋል።

“‘የቀበሌ ቤት መስሪያ’ በሚል ያለፈቃዳችን ከአመት ደመወዛችን 100% እየተቆረጠብን ነው" ያሉት ስሞታ አቅራቢዎቹ፣ "ወዴት እንጩህ?” ሲሉ ጠይቀዋል።

“ለቀበሌ ቤት መስሪያ" እንዲሁም "ለቡሳ ጎኖፋ” በሚል ደመወዛቸው ያለፈቃዳቸው እንደሚቆረጥ፣ የዲቲ ክፍያ በወቅቱ እንደማይከፈላቸው፣ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያም እንዳልተፈጸመላቸው አስረድተዋል።

“ዝም ብለው ነው የሚቆርጡብን ፈቃዳችንንም እንኳ አይጠይቁንም” ያሉ ሲሆን፣ የኑሮ ውድነቱን ተቋቁመው ቤተሰብ ማስዳደር ስላልቻሉ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

ሠራተኞች ስላማረራቸው ጉዳይ ምን አሉ?

“ ከደመወዛችን እንደፈለጉ ነው የሚቆርጡት። ያለ ማንም ፍላጎት ሰሞኑን 100% ከደመወዛችን ቆርጠዋል። ደመወዙ የሚቆረጠው ለፈረሙትም ላልፈረሙትም ነው።

በአመት 100% በደመወዝ ስኬል ነው የሚቆረጠው። ይህ በወር ከ500 እስከ 800 ሊሆን ይችላል። እንደዬ ስኬሉ መጠኑ ይለያያል። በዚህ ወር ደመወዛችን ተቆርጧል። 

የዱዩቲ ክፍያም የአሁኑ ዘግይቷል። ሌላው የሦስት ወራት የዱቲ ክፍያ አልተፈጸመልንም ገና እየጠበቅን ነው። ፋይናንስ ነው ያልከፈለን። ፎርሙ ፋይናንስ ጋ ደርሷል።

የሁለት ወራት አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ አልተከፈለንም። ደመወዛችንን አናውቅም የማይቆረጥ የለም። ዝም ብለው ነው የሚቆርጡት ያለምንም ፈቃድ። እኛን አይጠይቁንም። እንደፈለጉ ነው የሚያደርጉን። ሠራተኛም አይጠይቅም።

ገንዘባችን በብዛት እየተቆረጠ ያለው ‘የቀበሌ ቤት መስሪያ’ ተብሎ ነው። ከዚህም በፊት ያለፍላጎታችን ይቆርጡ ነበር። የትም አቤት ቢባል መልስ አይገኝም።

ይህ ድርጊት የሚፈጸመው እኛ ወረዳ ብቻ እንጂ ሌላ ወረዳ ላይ አልሰማንም ደመወዝ እየቆረጡ ያሉት ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለቅሬታው ምላሽ ለማካተት ከክልል፣ ዞን እንዲሁም ወረዳ ባለስልጣናት ለቀናት ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው ምላሽ አልተገኘም። ሆኖም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኞች ከሆኑ በድጋሚ ጥረት ያደርጋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 🚨“ በጣም ብዙ ችግር ነው እየደረሰባቸው ያለው። ጣታቸው የተቆረጠ አሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰጠው መግለጫ በመነሳት፣ “ አንዳንድ ሚዲያዎች መንግስት በማይናማር የታገቱ ዜጎችን አስለቀቀ ” በማለት መዘገባቸው ስህተት መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። የታጋቾቹ ቤተሰቦች በዝርዝር ምን አሉ ? “ አጋቾች  ያገቷቸውን ልጆቻችንን…
#Update

" ከ3,000 ወጣቶች ወደ 130 የሚሆኑት ወጡ ተብሎ ዝም የሚባል ከሆነ ለቀሪዎቹ አደጋ ነው " - የወላጆች ኮሚቴ

ሰርተው ለመለወጥ በሚል ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ዜጎች በማይናማር በአጋቾች የከፋ ስቃይ እያሳለፉ በመሆኑ መንግስት ከስቃይ እንዲታደጋቸው በተደጋጋሚ መጠየቁ አይዘነጋም። 

የወላጆች ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያዊያኑ በታገቱበት የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ አጋቾች ልጆቹን ዶላር ማጭበርበር ላይ እንደሚያሰሯቸው በመግለጽ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ደጋግሞ መፍትሄ መጠየቁ ይታወቃል። 

አሁንስ ኢትዮጵያዊያኑ ተለቀቁ
?

ለመፍትሄው ቅርብ የሆኑ አካላት ሁሉ መረጃ በመጠየቅ የታጋቾቹን ጉዳይ በጥልቀት የሚከታተሉ አንድ የታጋች ቤተሰብ በሰጡን ቃል፣ " ከሌሎች ዜጎች ጋር ተደምሮ 261 ልጆች ተለቀዋል። ከ261 ውስጥ ከ126 እስከ 138 ይደርሳል የወጡት የኢትዮጵያዊያኑ ቁጥር " ሲሉ ገልጸዋል።

የታጋቾቹ ወላጆች ኮሚቴ በበኩሉ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን እንዳልተለቀቁ፣ ነገር ግን  የታይላንድ የጸጥታ ኃይሎችና ኤንጂኦዎች ጥረት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ከእገታው እንደወጡ ገልጾልናል።

ኮሚቴው በሰጠን ቃል፣ " ከቀናት በፊት 6ዐ ኢትዮጵያዊያን አጥር ዘለው ጠፍተው ከሌሎች አገር ዜጎች ጋር ወጥተው ፓሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸው ነበር " ብሏል።

" ትላንት ደግሞ ወደ 70 ኢትዮጵያዊያን ከተለያዩ ቦታዎች፣ ከ60ዎቹ ጋር በአጠቃላይ 130 ኢትዮጵያዊያን ወጥተው ወደ ባንኮክ እየተጓዙ ነው " ያለው ኮሚቴው፣ ቀሪዎቹም ልዩ ትኩረት እንደሚሹ ገልጿል።

" እንዲወጡልን ብለን ካመለክትንላቸው ልጆቻችን አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት እንኳ ገና አልወጡም " ብሎ፣ " የኢትዮጵያ መንግስት ልጆቻችንን ችላ ብሎብናል " ሲል ወቅሷል።

" ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአሁኑ ወቅት ትንሽ ቢንቀሳቀስ በጣም ጥሩ ነው " ሲልም በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል አስገንዝቧል።

ወጡ የተባሉ ልጆችን ያወጣቸው የኢትዮጵያ መንግስት ነው ወይስ ሌላ ? ስንል ጠይቀነው በሰጠን ምላሽ ኮሚቴው፣ " የኢትዮጵያ መንግስት ምንም እጁ የለበትም። ካሁን በኋላ እጁን ካስገባልን ግን አናውቅም " ሲል መልሷል።

ማነው ያወጣቸው ታዲያ ? ስንል በድጋሚ ላቀረብነው ጥያቄ በምላሹ ፣ " ያወጧቸው ኤንጂኦዎችና የታይላንድ መንግስት ማይናማር ያሉ የጸጥታ አካላት ናቸው " ብሏል።

" ለሚዲያ ከቨሬጅ ብለው እንደሆነም አናውቅም። ከተለያዩ አገራት ያሉ ልጆችን ‘አንተን፣ አንተን’ እያሉ ነው አሉ ያወጡት " ሲልም ስጋቱን ተናግሯል።

ኮሚቴው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል በዝርዝር ምን አለ ?

" ከ3,000 ወጣቶች ወደ 130 የሚሆኑት ወጡ ተብሎ ዝም የሚባል ከሆነ ለቀሪዎቹ አደጋ ነው። ቀሪዎቹም ብዙ ናቸው። ማንም ካሁን በኋላ ዘወር ብሎ የሚያቸውም አይኖርም።

ያልወጡት ልጆቻችን ላይ አሁንም እዛው ያሉ አጋቾች የከፋ እርምጃ ሊወስዱባቸው የሚችሁሉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው እንደወጡት ሁሉ ቶሎ የማውጣት ስራ ካልተቀላጠፈ።
 
እስቲ እንዲያው መንግስት ይድረስላቸው። የኢትዮጵያ መንግስት እዛው ቆሞ አለሁ ይበላቸው ልጆቻችንን። ታይላንድ ላይም ሰው ይመደብልን።

በእርግጥም የማይናማር አካባቢ የጸጥታ አካላት የእገታውን አካባቢ ተቆጣጥሯል ተብሏል። ስለዚህ ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከማይናማር መንግስት በአስቸኳይ ቀርቦ ልጆቹ የሚወጡበትን መንገድ ይነጋገርልን።

አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት ይድረስልን እያልን ነው። የታይላንድ መንግስትና በማይናማር ያሉ አካላት ተባብረው የቻይና መንግስትም እየረዳቸው ነው እየተንቀሳቀሱ ያሉት። 

ቶኪዮ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በከስቸኳይ ሰዎች መድቦ እንዲየጋገርና ሁሉም ልጆቻችን እንዲወጡልን አሁንም በድጋሚ መልዕክቴ ነው " ሲል አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ExitExamResult " የፈተናው ውጤት ተለቆ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል " - የትምህርት ሚኒስቴር አመራር 🔴" የፈተና ውጤት ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መጥቷል " -  የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት የሀገር አቀፍ መውጫ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲዎች መላኩን የትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አጭር ቃል ፥ " ፈተናው…
#UPDATE #ExitExamResult

“ ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። ከዚህኛው ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑም እስከነጨረሻውም የሚይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

ሃገር አቀፉን የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከሰዓታት በፊት መለቀቁን ትምትርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸውን ነግረናችኋል።

በወቅቱም የፈተናው ውጤት የሚታይበት ሊንክ ስንጠይቅ “ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል ” በመባሉ የተለዬ መመልከቻ ካለ እንደምናጋራችሁ ቃል ገብተንላችሁ ነበር።

በዚህም፣ የውጤት መመልከቻው ሊንክ የትኛው ነው ? ስንል የጠየቅናቸው አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አመራር በሰጡን ቃል፣ “ ውጤት የሚታይበት ሊንክ ኖርማሊ ለዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል። ከተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ውጪ ሁሉም ማዬት እንዲችሉ ተነግሯቸዋል ” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።

“ ሊንኩ፦ ባለፈው ኦንላይን ሳፓርቲንግ የምንጠቀምበት ፔጅ ነበረ፤ እዛ ፔጅ ላይ ተለቋል። ያውቁታል እነሱ ፤ ከዚህ በፊት የተለቀቀ ሊንክ ነው ለኤግዚት ኤግዛም የተመዘገቡበት ሊንክ ላይ ውጤት ማየት ይችላሉ ” ሲሉ አስረድተዋል።

ስንት ተማሪዎች እንዳለፉና እንደወደቁ ጠይቀናቸው ገና እንዳልታወቀ በገለጹበት አውድ፣ “ አናላይስሱ አልተሰራም። አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ቅዳሜ እለት ስለሚያስመርቁ ለእነሱ ተብሎ ነው በችኮላ የተለቀቀው ” ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ የዲሲፒሊን ጉድለት የታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የፈተና ውጤት አለመለቀቁንም እኝሁ አካል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ የዲሲፒሊን ግድፈት ጎልቶ የታየባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ውጤት አልተለቀቀም፤ ወደ 6 በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች። ከዛ ውጪ ተለቋል። ስለዚህ አናላይሲሱ የ6ቱም ተጨምሮ ሲያልቅ ይሰራል ” ሲሉ ነግረውናል።

ስለዚህ የፈተናው ውጤት በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ነው የተላከው ማለት ነው ? ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ ፣ “ የፈተና ኮራፕሽኑ፤ ስርቆቱ የጎላባቸው 6 ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ላይ ነው እንጂ ያልተለቀቀው ሁሉም ላይ ተለቋል ” የሚል ምላሽ ነው የሰጡን።

በፈተናው ወቅት የተፈጠረ ችግር ነበር ወይስ በሰላም ተጠናቋል ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የአመራሩ ምላሽ፣ “ በዚህኛው ፈተናችን በሰላም ነው የተጠናቀቀው። የጎላ ቸግር አልነበረም ” የሚል ነው።

አክለው ደግሞ፣ “ የተለመዱ የዲሲፒሊን ችግሮች ናቸው የነበሩት፣ የተማሪዎች ከስርቆት ጋር በተገናኘ ያልተፈቀዱ እንደ ሞባይል ያሉ ኤሌክትሮኒክ ዲቫይሶችን ለመጠቀም ሙከራ ማድረግ፣ ወጣ ያለ ደግሞ ከዚህ በፊት የተፈተኑ ተማሪዎች ገብተው ለመፈተን ሙከራ ማድረግ፣ ናቸው እንጂ በጣም የጎላ ችግር አልታዬም ” ነው ያሉት።

ከዲሲፒሊን ግድፈት ጋር በተያያዘ ስንት ተማሪዎች ተገኝተዋል ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡን ምላሽ፣ “ ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ እስካሁን ድረስ ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። የዚህኛው ራውንድ ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑ እስከነጨረሻውም የማይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” ብለዋል።

“ እስካሁን ግን አልተወሰነም። ለጊዜው ግን የዚህኛው ውጤት ዲስኳሊፋይድ እንደሚደረግ ነው 54ዐ ተማሪዎች የተለዩት። ቁጥሩ ሊበልጥ ይችላል፤ ለጊዜው ግን ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል ” ሲሉም አክለዋል።

(ስንት ተፈታኞች እንዳለፉና እንዳላለፉ ውጤቱን ተከታትለን በቀጣይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል)

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Breaking : የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል። ሚኒስትሩ አብረዋቸው ለውድድር የቀረቡትን የኬንያውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ እንዲሁም የማዳጋስካሩን ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው የተመረጡት። @tikvahethiopia
#Update

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት ቦታ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ 6 ዙር ከፈጀው የድምጽ አሰጣጥ በኋላ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው መመረጥ ችለዋል።

የምርጫ ሂደቱ ምን ይመስላል?

በምርጫው የሚያሸንፈው ተመራጭ ድምጽ መስጠት ከሚችሉት 48 አባል ሀገራት ሁለት ሶስተኛውን ድምጽ (33 ድምፅ) ማግኘት ይጠበቅበታል።

በሚደረገው ምርጫ ለማሸነፍ የሚያስፈልገውን 33 ነጥብ ማግኘት ካልተቻለ ተከታታይ ምርጫዎች የሚካሄዱ ሲሆን ዝቅተኛ ድምጽ ያገኘው ከውድድሩ ተሰናብቶ ቀሪ ተወዳዳሪዎች ለማሸነፍ የሚያስችላቸውን ነጥብ እስኪያገኙ ይወዳደራሉ።

በዚህም ለ7ኛ ጊዜ በተደረገው በዚህ ውድድር አሸናፊውን ለመለየት 6 ዙሮች ፈጅቷል።

በመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዙሮች የኬንያው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መምራት ቢችሉም የማሸነፊያ ነጥብ ሳያገኙ ቀርተዋል።

በስድስተኛው ዙር ድምጽ የጅቡቲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለማሸነፍ የሚያስፈልጋቸውን 33 ነጥብ በማግኘታቸው ምርጫውን አሸንፈዋል።

በዚህም ለቀጣይ 4 ዓመታት የቀድሞውን የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂን በመተካት 7ኛው የኅብረቱ ሊቀመንበር በመሆን መመረጥ ችለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia