TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FakeNews በጅማ ከተማ አንድ አባት ታርደው ወንዝ ዳር ተጥለው ተገኙ ተብሎ በፌስቡክ እና በቴሌግራም የሚሰራጨው መረጃ #ከእውነት_የራቀ ነው። ይህንን ያረጋገጡልንም የጅማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ናቸው።

ሼር የምታደርጉትን መረጃ በቅድሚያ አጣሩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKENEWS

የፈጠራ ወሬ ወይም FAKE NEWS አንባቢን ወይም አድማጭን ለማታለል ወይም ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚሠራጭ አሳሳችና የሃሰት ዜና ነው።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሠራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሃሣቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በማኅበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግሥትና ሕዝብን፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያጋጫል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የሚዘጉ መንገዶች ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ ነው። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለከተማው ነዋሪዎች ባሰራጨው መረጃ በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ የሚደረግ ስብሰባ፣ ሰልፍም ሆነ የሚዘጋ መንገድ የለም ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

የህዳሴው ግድብ የማመንጨት አቅሙ በ1ሺህ300 ሜጋዋ ዋት ቀነሰ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰት ነው ተባለ። የግብጽና የተለያዩ የአገር ወስጥ መገናኛ ብዙሃን ስለ ህዳሴው ግድብ ያወጡት መረጃ ከእውነት የራቀ እንሆነ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።

የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳሉት የግድቡ የማመንጨት አቅም እንዲቀንስ ተደርጓል የሚባለው መረጃ ትክክል አይደለም ብለዋል። የግድቡ የማመንጨት አቅም የሚወሰነው ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን እና ውሀ ከተርባይን ማእከል በሚኖረው ከፍታ ነው ብለዋል አቶ ሞገስ፡፡

የግድቡ ውሀ ከፍታ በጨመረ ቁጥር የተርባኖች የማመንጨት አቅም ከፍ ያደርገዋል እንጂ ተርባይኖች ብዛት የማመንጨት አቅም እንደማይጨምረው ነው ዳይሬክተሩ የነገሩን። አሁን ባለው ሁኔታ የግድቡን የውሀ መጠን የሚቀንስ ስራ ወይም የግድቡን ከፍታ የሚቀንስ ስራ እየተሰራ አይደለም እየተደረገ ያለው የተርባኖች ቁጥር የመቀነስ ስራ ነው ብለዋል፡፡

የተርባይኖች ቁጥር እንዲቀንስ ቢደረግም በማመንጨት አቅሙ ላይ ምንም ተጽእኖ አይኖረውም ምክንያቱም የግድቦች የማመንጨት አቅም የሚወሰነው በተርባይኖች ብዛት ሳይሆን ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡ ከግብጾች አንጻር አሁን የተነሳው ጥያቄ ግድቡ የሚይዘው የውሀ መጠን የግድቡ ከፍታ እንደማይቀንስ ካሁን በፊት የግብጽ ባለሙያዎች እርግጠኛ ነበሩ ስለሆነም ያንን ተከትሎ የተነሳ እንደሆነም ነው አቶ ሞገስ የተናገሩት፡፡ በመሆኑም የህዳሴው ገድብ 6400 ሜጋዋ ዋት እንዲያመነጭ ከዚህ በፊት በታቀደው መሰረት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews "የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸው" ተብሎ በፌስቡክ የተሠራጨው ወሬ ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

ይህ በማህበራዊ ሚዲያ በብዛት ሼር ሲደረግ የነበረ "ሀሰተኛ ዜና" ደግሞ አምቦ ከተማን የሚመለከት ሲሆን "በአምቦ ከፍተኛ ብጥብጥ ተነስቷል፣ ግርግርም አለ፤ ቤተክርስቲያንም ሊቃጠል ነው" የሚል ነው። አምቦ ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቅሴ ውስጥ ነው የዋለችው። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ እልቂት እንዲገባ የሚያነሳሱ ብዙ የፌስቡክ ሰዎች ስላሉ ከፍተኛ ማስተዋል እና ጥንቃቄ ይጠይቃል። በተለይም ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የሚፃፉ ፅሁፎችን ደግሞ ደጋግሞ ማረጋገጥ ተገቢ ነው። የምትሰሙትን መረጃ ሁሉ ሼር ከማድረግ ተቆጠቡ።

ሌላው አምቦ ከተማ ዛሬ "ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ታግተው ነበር፤ በሂሊኮፕተር ነው ያመለጡት" እየተባለ በተለያዩ ገፆች ሲወጡ የነበሩት መረጃዎች ፍፁም ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎች ናቸው። ይህም ሆን ተብሎ ሌላ አከባቢ ያለው ህዝብ ለማነሳሳት እና ወደጥፋት ለመውሰድ የተደረገ ድርጊት ነው። የአምቦ ወጣቶች ጥያቄዎቻቸው፣ ቅሬታቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሰምተው ወደየቤቶቻቸው እንደገቡ ቀን ገልጬላችሁ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ የሚለው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በወላይታ እና ሲዳማ ዞኖች መካከል እልባት ባላገኙ 8 ወረዳዎች ላይ የህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ምርጫ ጣቢያ እንዳይቋቋም ከስምምነት ተደረሰ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የምርጫ ቦርድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አረጋግጧል።

የቦርዱ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ቦርዱ የሚያውቀው እንዲህ አይነት ስምምነት የለም፤ ጭምጭምታዎችንም ቦርዱ አይሰማም ብለዋል።

(ETHIO FM- ትዕግስት ዘላለም)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
EBC ዋልታ የሰራውን ዘገባ #FakeNews ብሎታል!

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥን አስመልክቶ የሀዋሳ ከተማ ም/ከንቲባ አሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ እርሳቸው ያላሉት መሆኑን አስታወቁ!

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ በሀዋሳ ከተማ የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በሰጡት መግለጫ “90 በመቶ የሻፌታ ምልክት አሸነፈ” ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ እርሳቸው ያላሉት መሆኑን ምክትል ከንቲባው ለኢቲቪ አረጋግጠዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የተናገሩት “በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ድምጽ ለመስጠት በመራጭነት ከተመዘገበዉ ህዝብ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ መስጠቱን በየምርጫ ጣቢያዎች እየወጣ ያለው ውጤት ያሳያል፡፡” የሚለውን ነው፡፡

(EBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FakeNews🚨

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ምንም አይነት የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ከወራት በፊት መሰል የፈጠራና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ የ #የሶማሊያ አክቲቪስቶችና የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከሰሞኑን ዳግም የፈጠራ ወሬዎችን ፅፈው ማሰራጨትን ይዘዋል።

እያሰራጩ ካሉት ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ አንዱ " በአዲስ አበባ የተለየ ሁኔታ እንዳለ ፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደጨመረ፣ በየቦታው ወታደሮች እንደተበተኑ " የሚገልጽ ነው።

ይህ ሀሰተኛ እና የፈጠራ ወሬ ሲሆን በከተማዋ ውስጥ አንዳችም የተለየ የወታደራዊ እንቅስቃሴ የለም።

ምንም እንኳን ጉዳዩ ውሸት ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ ሀሰተኛ መረጃ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ፣ እያጋሩት እንደሆነ መመልከት ተችሏል ስለሆነም ጥንቃቄ አድርጉ።

#AddisAbaba #Ethiopia

@tikvahethiopia