TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#JawarMohammed #BekeleGerba

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጀዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ የደህንነት ስጋት አለን በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የልደታ ምድብ ችሎት የተከሳሾች የንብረት እግድ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው።

ይሁን እንጂ ከተከሳሾች መካከል አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት አልተገኙም።

ፍርድ ቤቱም አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ በጠየቀበት ወቅት፤ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ተከሳሾቹ የደህንነት ስጋት አለብን በሚል ምክንያት አለመቅረታቸውን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

በእነ አቶ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ውስጥ የተከሰሱት አቶ ሐምዛ ቦረና፤ "አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ 'አገሪቱ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ስጋት ስላለን በዚህ ቀጠሮ መገኘት አንችልም' ብለዋል" ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

"አሁን ባለው ሁኔታ አይደለም ጉዳት ይቅርና ሙከራ [የግድያ] ቢደረግብን አገሪቱ ወደ ከፋ አደጋ ውስጥ ስለሚያስገባት ለአገሪቱ በማሰብ ወደ ፍርድ ቤት ከሚደረግ ጉዞ እራሳችንን ቆጥበናል" ስለማለታቸው አቶ ሐምዛ ቦረና ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም አሁን አገሪቱ ውጥረት ውስጥ እያለች በንብረት ጉዳይ ላይ ለመከራከር ፍርድ ቤት መመላለስ 'ለእኛ ሃፍረት' ነው በሚል ምክንያት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን አቶ ሐምዛ፤ አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለን ወክለው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ በንብረት እግዱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሕዳር 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል። (BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ የካቲት 8 የነአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቆች በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ጉዳዩን ለሚያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ ጀዋር መሀመድ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ከቀናት…
አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ወደሆስፒታል ሲወሰዱ ምን ተፈጠረ ?

"አባቴ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም" - ቦንቱ በቀለ

ትላንት የእነአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች በእስር ላይ የሚገኙትን የፖለቲከኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ በቀለ ገርባ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ትእዛዝ አቶ በቀለ፣ አቶ ጃዋር፣አቶ ሃምዛ፣ አቶ ደጀኔ አ/አ ሜክሲኮ አካባቢ ላንድማርክ ጄነራል ሆስፒታል በአጃቢ አስፈላጊውን ጥበቃ ተደርጎ ህክምና እንዲወሰዱ የሚል ነው።

ነገር ግን በዛሬው ዕለት አቶ በቀለ ገርባ ወደ "ላንድማርድ ጄነራል ሆስፒታል" እንደሚወሰዱ ከተነገራቸው እና ከማረሚያ ከወጡ በኃላ የአጃቢ መኪኖቹና እሳቸውን የያዘው አምቡላንስ ከመንገድ ላይ ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንደወሰዷቸው ልጃቸው ቦንቱ ተናግራለች።

https://telegra.ph/BekeleGerba-02-16
#BekeleGerba #USA🇺🇸

አቶ በቀለ ገርባ በአሜሪካ ሀገር #ጥገኝነት መጠየቃቸውን አሳወቁ።

ለረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በግል እና በፓርቲ ደረጃ ተሳታፊ የነበሩት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ተቀዳመ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ በቀለ ገርባ በፓርቲያቸው የነበራቸውን ተሳትፎ አብቅተው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናገሩ።

አቶ በቀለ ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገልም ሆነ በግል በነጻነት መኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል የሆኑት አቶ በቀለ፣ በውጭ አገር ሆነው ሥልጣኑን ይዘው መቀጠጣለቸው ጠቃሚ ስላልሆነ እራሳቸውን ከፓርቲው ለማግለል መወሰናቸውን ተናግረዋል።

አቶ በቀለ ገርባ ፤ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን ሁከት ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ውለው ለ18 ወራት በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁ በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘዋል። አሜሪካ ከሄዱ 1 ዓመት ከሶስት ወር ሆኗቸዋል።

አቶ በቀለ ከእስር ከወጡ በኋላ ወደ አሜሪካ ሲጓዙ ዓላማቸው የእርሳቸውን ከእስር መለቀቅ ሲጠይቅ ለነበረው የዳያስፖራ ማኅብረሰብ ምስጋና ለማቅረብ ነበር።

ነገር ግን አሜሪካ በቆዩባቸው ያለፉት 15 ወራት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በመቀየሩ " ወደዚያ አገር መመለሱ አስፈላጊ መስሎ አልታየኝም "  በማለት እዛው ጥገኝነት መጠየቃቸውን እና ከፓርቲው ኃላፊነትም እራሳቸውን ማግለላቸውን ለቢቢ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

More - https://telegra.ph/BBC-08-28-2

@tikvahethiopia