TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በድሬዳዋ ከተማ የሰው ህይወት አለፈ‼️

ትላንት ቅዳሜ ምሽት በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ቦዬ ተብሎ በሚጠራው መንደር በተቀሰቀሰው #ግጭት የአንድ ወጣት ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። ምሽቱ በጥይት እሩምታና በአስለቃሽ ጭስ ተኩስ ነዋሪዎችን ጭንቀት ውስጥ ከቶ ያለፈ ነበር።

በምሽቱ ግጭት ህይወቱን ያጣው ወጣት #አብዱረዛቅ_ሪቫቶ ከፀጥታ ሀይሎች በተተኮሰበት ጥይት ለአካል መቁሰል ተዳርጎ ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ለማትረፍ አልተቻለም።

ፍፁም መከሰት የሌለበትና በቀላሉ ሊፈታ የሚገባው ችግር ማመዛዘን በጎደለውና በቸኮለ እርምጃ የሰው ህይወት በድሬዳዋ ተቀጥፏል ብሏል ዜናውን ያሰራጨው ድሬ ትዩብ።

ጨምሮም የህግ አስከባሪዎች ለሚወስዱት ማንኛውም እርምጃ ሞያዊ ክህሎት የተላበሰና ማስተዋል የተጨመረበት መሆን አለበት፤ ኮሽ ባለ ቁጥር አፈ ሙዝ የሚደቅን የፀጥታ ሀይል አላግባብ በሆነ መልኩ ህይወትን ያሳጣል ብሏል።

በድሬዳዋ ገንደ ቦዬ መንደር በመሬት ጉዳይ የተነሳው ውዝግብን ለመፍታት የፀጥታ ህይሎች ችግሩ ሳይፈጠር መፍታትና #መቆጣጠር ሲችሉ የረፈደ እርምጃቸው ውዱን የሰው ህይወት አላግባብ እንዲመክን ምክንያት ሆኗል ሲል ድሬ ትዮብ ጨምሮ አስነብቦናል። በወጣቱ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

ምንጭ፦ ድሬ ትዩብ
@tsegabwolde @tikvahethiopia