TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሹመት!

አቶ #ነቢያት_ጌታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ መለስ አለም የኬንያ አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ አቶ ነቢያት ጌታቸው ቃል አቀባይ ሆነው የተሾሙት።

አቶ ነቢያት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለበርካታ አመታት ያገለገሉ ሲሆን በዲፕሎማሲ ልምድ አካብተዋል። በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካና ካሪቢያን ጉዳዮች ዳይሬክተር ሆነውም አገልግለዋል። በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካና የአኢኮኖሚ ትብብር አማካሪ፤ በስዊድንና በኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የፖለቲካ ደስክ ዲፕሎማት ነበሩ።

አቶ ነቢያት ከእንግሊዙ ሊድስ ዩኒቨርስቲ በአለም አቀፍ ኮሚዪኒኬሽን ማስተርስ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሰሩት ደግሞ በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ ነው።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በታንዛኒያ የሚገኙ 541 #ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን አገራቸው እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ #ነቢያት_ጌታቸው የጉዞ ሰነድ የተሰጣቸው 541 ኢትዮጵያውያን በመጪዎቹ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት የታንዛኒያ መንግሥት 1900 ኢትዮጵያውያንን ከእስር ለመልቀቅ መወሰኑን አስታውቆ ነበር። አሁን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተዘጋጅተዋል የተባሉት 541 ኢትዮጵያውያን የታንዛኒያ መንግሥት በምኅረት ከለቀቃቸው መካከል ስለመሆናቸው #የታወቀ ነገር የለም።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ናዝራዊት ቻይና ውስጥ #በሞት እንድትቀጣ አልተፈረደም!"

ቻይና ውስጥ ላለፉት #ሶስት_ወራት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ ስለምትገኘው #ናዝራዊት_አበራ በዛሬው ዕለት የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ #ነቢያት_ጌታቸው ከአለም አቀፉ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። የሰጡት መረጃምይህንን ይመስላል፦

"ቻይና ሀገር ያሉ የኛ የቆንስላ ፅ/ቤት ሰራተኞች ሶስት ግዜ እስር ቤት ሄደው አይተዋታል። የመጨረሻው ጉብኝት እንደውም ያለፈው አርብ ነበር። ላረጋግጥልህ የምችለው የሞት ፍርድ ተፈረደባት የሚባለው ውሸት መሆኑን ነው። ሂደቱ ገና ነው። የሀገሪቱ አቃቤ ህግ ገና ክሱን ያቀርባል። ከዛ በሁዋላ ነው ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሄዶ የሚወሰነው። እስካሁን እፅ ነክ በሆነ ወንጀል ተጠርጥራ ነው ያለችው። እንደ ዜጋችን አሁን መጠየቅ የምንችለው የኮንሱላር ድጋፍ ማረግ ነው። እሱን ደሞ እያገኘን ነው። #ትክክለኛ_ፍርድ እንድታገኝ እና ጠበቃ የማግኘት መብት እንዲኖራት ክትትል ይደረግበታል። የፍርድ ደረጃ ላይ ሲደረስም clemency (ምህረት) የሚጠየቅበት ሁኔታ የተለመደ ነው። እነሱም ያሉን ጉዳዩ በቻይና ህግ የተያዘ ነው ብለውን ነው።"

ምንጭ፦ ETHIO-NEWSFLASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ #ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት #በቅርቡ እንደሚለቀቅ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ #ነቢያት_ጌታቸው ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ ሪፖርቱን ይፋ የሚያደርገው ትራንስፖርት ሚንስቴር ነው፡፡ ውጤቱ ለአውሮፕላኑ የተገጠመለት (MCAS) ሶፍትዌር #ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ አውሮፕላኑ አፍንጫውን ቁልቁል ዘቅዝቆ እንዲከሰከስ እንዳደረገው እንደሚገልጽ ይጠበቃል፡፡ #ቦይንግ ኩባንያ ሶፍትዌሩን አሻሽያለሁ ብሏል፤ በሚዲያ ዘመቻ ራሱን ለመከላከል እየሞከረ ነው፡፡

Via ሮይተርስ(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia