TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቦይንግ

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ማምረት #ሊያቆም እንደሚችል ገለጸ፡፡ ቦይንግ ከዚህ ቀደም ያመረታቸው አውሮፕላኖች ወደ በረራ ካልተመለሱ የ737 ማክስ ምርቱን ሊያቋርጥ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

ኩባንያው ይህን ያለው በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኪሳራ በሩብ ዓመት ብቻ በማስመዝቡ ነው፡፡ አሁንም በዓለማቀፍ ደረጃ የበረራ ባለስልጣናት ፈቃድ ካልሰጡና አውሮፕላኖቹ ወደ ሥራ ካልተመለሱ ምርቱን ሊቀንስ በሂደትም ማምረቱን ሊያቆም እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡

የቦይንግ ኃላፊ ዴኒስ ሙይልበርግ ግን በመጭው ጥቅምት አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንደሚመለሱ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ‹‹ጥረታችንን ቀጥለናል፤ 737 አውሮፕላኖቻችን ችግሮቻቸው ተቀርፈው ወደ በረራ እንደሚመለሱ ተስፋ እናደርጋለን›› ብለዋል፡፡

‹‹ነገር ግን ወደ በረራ የመመለሻ ጊዜው ከተገመተው በላይ ጊዜ ከወሰደ ምርትን ከመቀነስ አልፎ የማክስ አውሮፕላኖችን ምርት ወደ ማቆም እንገባለን›› ብለዋል ኃላፊው፡፡

ባለፈው መጋቢት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ 157 ሰዎች መሞታቸውና አደጋው በጥቅምት ወር መጨረሻ አካባቢ ሌላ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በኢንዶኔዥያ ተከስክሶ 189 ከሞቱበት አደጋ ጋር መመሳሰሉ ምርቱ ችግር እንዳለበት ፍንጭ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህንን ተከትሎም አብዛኞቹ የዓለም ሀገራት ሞዴሉን ከበረራ አግደውታል፤ ይህም ኩባንያውን ለኪሳራ ዳርጎታል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ/AMMA/
@tsegabwolde @tikvahethiopia