TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Congratulations #Somaliland Military Officers graduate from #Ethiopian Military Academy, Won medals!

Via Horn
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Somaliland

በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ማቅናቱ ተነግሯል።

ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተደረገላቸው ይፋዊ ግብዣ መሰረት ነው ወደኢትዮጵያ እንደሚመጡ የተገለፀው።

በሌላ በኩል ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢሳ ካይድ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከፕሬዜዳንቱ ሙሴ ቢሂ አብዲ ቀደም ብሎ ትላንት አዲስ አበባ ገብቷል። የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ቡድኑን ተቀብለው አነጋግረዋል።

#MFA_Somaliland

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
#ETHIOPIA 🤝 #Somaliland #RedSea #Port

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ምን አሉ ?

" ... እንኳን የኢትዮጵያ ስብራት ጥገና ቀን በጋራ አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

በተደጋጋሚ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ኢትዮጵያ ካሏት ዋና ዋና ስብራቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀይ ባህርን #access የማድረግ በዛውም #የማልማት ፍላጎት ከሶማሌላንድ ወንድሞቻችን ጋር በተደረገው የትብብር ስምምነት ዛሬ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመናል።

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳነሳነው እኛ ያሉንን ሃብቶች የመጋራት ፣ የመካፈልና በጋራ የመልማት ፍላጎት እንጂ ማንንም በኃይል የማስገደድ ፍላጎት የለንም ስንል የነበረው ሃሳብ በተግባር ዛሬ በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ቀን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ የሶማሌላንድ ህዝብና ለሰላም ወዳድ ህዝብ ለልማት ወዳድ ህዝብ የምናበስረው የምስራች ይሆናል።

ስብራቶቻችን ይጠገናሉ፣ ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች። በገባነው ቃል መሰረት ሀገራችንን ወደሚቀጥለው ደረጃ እናሸጋግራለን።

ስለሆነው ሁሉ ያደረገልንን ፈጣሪን እናመሰግናለን። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሶማሊያ ካቢኔ በነገው ዕለት አስቸኳይ ስብሰባ እንደተጠራ ተሰምቷል። አስቸኳይ ስብሰባው ፤ ዛሬ በሶማሌላንድ (ሶማሊያ ሶማሌላንድን እንደ ሰሜናዊ ክልሏ ነው የምትቆጥራት) እና በኢትዮጵያ መካከል ተደርጓል ስለተባለው ስምምነት በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ለማሳለፍ ነው ተብሏል። ከዚሁ ከነገው አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ዝግጅት ጋር በተያያዘ #በአሁን_ሰዓት በሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት…
#Ethiopia 🤝 #Somaliland

" ታሪክ እየተሰራ ነው " - አሊ ሀሰን ሞሃመድ

ኢትዮጵያ እስካሁን በይፋ ከሶማሌላንድ ጋር በተፈረመው የትብብር ስምምነት የባህር በር ለመጠቀም እና የባህር ኃይል ቤዝ እንዲኖራት በምላሹ ደግሞ የ " ሶማሌላንድን " የነፃ ሀገርነት እውቅና እንደምትሰጥ አንዲትም ቃል #አልተናገረችም

የሶማሌላንዱ ፕሬዜዳንት ግን ከስምምነቱ በኃላ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ የነፃ ሀገርነት ውቅና እንደምትሰጥ በምላሹ የባህር በር እና የባህር ኃይል እንዲኖራት 20 ኪሎሜትር መሬት በሊዝ እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ባለስልጣናትም ተመሳሳይ መረጃዎችን ሰጥተዋል።

ለአብነት አሊ ሀሰን ሞሃመድ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ፤ " ታሪክ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሊዝ የ20 ኪሎሜትር የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን በምላሹ ደግሞ #እውቅና እና የኢኮኖሚ እድገት እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

" ይህ ጨዋታ ቀያሪ፤ ትልቅ ትርጉም ያለው ስምምነት ነው " ያሉት ባለስልጣኑ " ትልቅና ደፍረትን የሚጠይቅ እርምጃ ነው ፤ ወደፊት ለሶማሌላንድ እና ኢትዮጵያ የብሩህ አድማስ በሮችን የሚከፍት ነው " ብለዋል።

ይህንኑ የአሊ ሀሰን ሞሀመድ ሃሳብን ሞባረክ ታኒ የተባሉት የፕሬዜዳንቱ ዋና ፀሐፊ ተጋርተውታል።

በሌላ በኩል ፤ ሶማሊያ እንደራሷ አንድ ግዛት የምታያት " ሶማሌላንድ " ከኢትዮጵያ ጋር ተፈራረመች ስለተባለው የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ ነገ ካቢኔዎቿ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሏል።

ለነገው አስቸኳይ ስብሰባ ዝግጅት ዛሬ ምሽት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ምክትላቸው እና ከፍተኛ የካቢኔ አባላት የተገኙበት ሰብሰባ ሲደረግ አምሽቷል።

የሶማሊያ ባለስልጣናትም የመግባቢያ ስምምነቱ ክፉኛ እንዳስቆጣቸው ተነግሯል።

የሶማሊያ የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሩ አብዲሪዛቅ ሞሀመድ ፤ " ሶማሊያ አትከፋፈልም ፤ በሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነታችን አንደራደርም " ብለዋል።

ሚኒስትሩ ፤ " ኢትዮጵያ ከግዛት (ክልል) አስታዳዳሪ ጋር ወደብን ለመከራየት / ወታደራዊ ስምምነት (MOU) ማድረግ እንደማትችል በደንብ አድርጋ ታውቃለች ይህ ስልጣን ሙሉ በሙሉ የፌዴራላዊ ሶማሊያ መንግሥት ነው ፤ ኢትዮጵያ የግዛት አንድነታችንን የሚጥስ ተግባር መፈፀም አትችልም " ሲሉ ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የዛሬውን " ታሪካዊ " የተባለ የትብብር ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ " ኢትዮጵያ #ቀይ_ባህርን የመጠቀምና በዛውም የማልማት ፍላጎት ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል " ሲሉ አብስረዋል።

ዶክተር ዐቢይ፤ " እኛ ያሉንን ሃብቶች የመጋራት ፣ የመካፈልና በጋራ የመልማት ፍላጎት እንጂ ማንንም በኃይል የማስገደድ ፍላጎት የለንም ስንል የነበረው ሃሳብ በተግባር ታይቷል " ሲሉም ነው ያሳውቁት።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🤝 #Somaliland

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) ኢትዮጵያ በሱማሌላንድ በምትወስደው የወደብ ስፍራ ላይ ልማት ለማከናወን ሲዘጋጅ መቆየቱን አስታውቋል።

ትላንት የተፈረመው ስምምነት ለስራችን ትልቅ ዜና ነው ያሉት የኢባትሎ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር)፤ በድርጅቱ ስራ ላይ ትልቅ እመርታ የሚያመጣ ነው ብለውታል።

በተለይ ከዋጋ እና አላስፈላጊ ወጪ ጋር በተገናኘ እንደ አገር ትልቅ እፎይታ የሚያመጣ ነው ሲሉ ስምምነቱን አሞግሰዋል።

ድርጅታቸውም በተወሰደው ቦታ ላይ መሰረተልማት ለማከናወን ሲዘጋጅ እንዲሁም የሚያስተዳድራቸውን መርከቦች መጠን ለመጨመር ሲሰራ እንደቆየ ነው የገለፁት።

ትላንት ይፋ በተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ በሱማሌላንድ የበርበራ ከተማ በስተ ሰሜን አቅጣጫ በሚገኝ የባህር ዳርቻ የራሷን የጦር ሰፈር እና የንግድ ወደብ እንደምታለማ ተገልፀጿል።

Via CAPITAL

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ ይፋዊ መግለጫ ወጥቷል። በዚህም መግለጫ ስምምነቱ ታሪካዊ ነው ተብሏል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እውቅና በመስጠት በሊዝ የባህር በር / ለባህርኃይሎቿ የባህር መዳረሻ እንደምታገኝ መግለጫው ይገልጻል። " ስምምነቱ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ነው " ያለው መግለጫው ለኢትዮጵያ የባህር ኃይል ተጠቃሚነት 20 ኪሎሜትር የባህር በር እንደሚሰጥ…
#Ethiopia #Somaliland

አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ምን አሉ ?

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ የኢትዮጵያ የባህር በር መዳረሻ መኖር ለቀጠናዊ ውህደት ቁልፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሶማሊላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም አሳውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " የሶማሌላንድ መንግስት ያወጣውን መግለጫ በደስታ እንቀበላለን። " ብለዋል።

የሶማሊላንድ መንግስት ዛሬ ጥዋት ባወጣው መግላጫ ኢትዮጵያ በሊዝ የባህር ወደብ እንድታገኝ በምላሹ ደግሞ ለሶማሊላንድ እውቅና እንድትሰጣት የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሶማሊያ በኢትዮጵያ ያሉትን አምባሳደሯን መጥራቷን ተከትሎ አምባሳደር አብዱላሂ ዋርፋ ወደ #ሞቃዲሾ ማቅናታቸው ተሰምቷል። በሌላ በኩል ደግሞ ፤ የሶማሊያ ሁለቱ የፌደራል ፓርላማ ምክር ቤቶች በአሁን ሰዓት አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ የተቀመጡ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል። ከ100 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ የወደብ እና…
#Somalia #Somaliland

" የሶማሊያ ደካማ መንግስት ይሄን ታሪካዊ ስምምነት ለማስቆም ምንም አይነት ሕጋዊነት የለውም " - አብዱላሂ አርሼ (የሶማሊላንድ ባለስልጣን)

የቀድሞ የሶማሊላንድ " የሀገር ውስጥ " ሚኒስትር አማካሪ እና በአሁን ሰዓት በሶማሌላንድ " የሀገር ውስጥ " ሚኒስቴር የሚዲያ እና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አብዱላሂ አርሼ የሶማሊያን መንግሥት " ደካማ መንግሥት " ሲሉ ጠርተው በኢትዮጵያ እና በሶማሊላንድ ሪፐብሊክ መካከል የተፈረመውን #ታሪካዊ_ስምምነት ለማስቆም ምንም አይነት ሕጋዊነት የለውም ብለዋል።

" የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና የሰጠው የሶማሊያ ስርዓት እንደ ወቀደ መንግስት ነው፣ ሞቃዲሾ ውስጥ የአስተዳደር ስርዓት የለም። " ሲሉ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።

ኢስማኤል ሺርዋክ የተባሉ የሶማሊላንድ ዲፕሎማት ደግሞ ፤ " ሀገራችን አንድ እርምጃ ወደፊት ስትሄድ ሶማሊያ በታሪክ ግልፅ የሆነ ጥላቻ  አሳይታለች። " ያሉ ሲሆን " ሶማሌላንድ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (#UAE) ስምምነት ላይ ሲደርሱ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል፣ ነገር ግን ምንም አይነት ውጤት አላመጣም። " ብለዋል።

" እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር የዜጎቻችንን ጥቅም መሰረት አድርገን የሚያስፈልገውን እንወስናል " ሲሉ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ለሁለቱ የፌዴራል ም/ቤት አባላት ንግግር ማድረጋቸው የተሰማ ሲሆን የሶማሊላንድ እና የኢትዮጵያን የትብብር ስምምነት ሰነድ ተቃውመዋል።

" አንድም ኢንች የሶማሊያ ግዛት በማንም ሊፈረም አይችልም ፤ሉዓላዊነታችንንና የግዛት አንድነታችንን እንጠብቃለን ፤ በዓለም አቀፍ ህጎች መሰረት እናስከብራለን፤ እያንዳንዱን ኢንች መሬት እንጠብቃለን፤ ሶማሊያ የሶማሊያውያን ነች ፤ ይሄ የመጨረሻው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" አቶ መለስ ዜናዊ በሶማሊያ ውስጥ የገቡት ጣልቃ ገብነት የአልሸባብን መነሳት አስከትሏል " ሲሉ የተደመጡት ፕሬዜዳንቱ " የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እርምጃም ያሸነፍነውን አልሸባብ ዳግም እንዲነሳሳ ሌላ ዕድል የሚሰጥ ነው " ብለዋል።

" የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጥር 1 ከያዙት መንገድ እንዲመለሱ " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ ያላቸው አማራጭ አንድ ብቻ ነው እሱም በሰላም መኖር ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

የሶማሊንላንድ ባለልስጣናት ስምምነቱን የደገፉ ሲሆን በሶማሊያ ባለስልጣናት ላይም ጠንክራ ትችት እየሰነዘሩ ይገኛሉ። ስምምነቱን የማስቆም ምንም አይነት አቅም የላቸውም ሲሉ እየተደመጡ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Somaliland #Somalia

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ፤  ዛሬ ወደ ሶማሊላንድ መዲና ሃርጌሳ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የሶማሊያ አየር ክልል ውስጥ ከመግባቱ በፊት እንዲመለስ መደረጉን ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ሃርጌሳ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላን ከሶማሊያ በኩል " ፍቃድ የለውም " በመባሉ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ለማረፍ ተገዷል ብለዋል።

" ወደ ሃርጌሳ እየሄደ የነበረው አውሮፕላን ተመልሷል። ምክንያቱም በረራውን ከጀመረ በኋላ ከሶማሊያ በኩል ፍቃድ አልሰጠንም የሚል ጥያቄ ተነስቶ ነው። " ሲሉ አስረድተዋል።

የበረራ መከታተየ " ፍላይትራዳር24 " በተባለው ድረ ገጽ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ዛሬ ጥር 8/2016 ዓ.ም. ሁለት በረራዎች ወደ ሶማሊያ ተደርገዋል።

መደበኛው የበረራ ቁጥር ኢቲ372 ረፋድ 5 ሰዓት ላይ ሃርጌሳ ማረፉን ፍላይትራዳር ያሳያል።

ይሁን እንጂ የበረራ ቁጥር ኢቲ8372 የሆነው ዲ ሃቪላንድ-400 አውሮፕላን ጠዋት 2፡30 ከአዲስ አበባ ተስቶ ወደ ሃርጌሳ አቅጣጫ እየበረረ ሳለ የጂግጂጋ ሰማይ ላይ በመዞር ረፋድ 4፡30 አካባቢ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመልሶ አርፏል።

አቶ መስፍን ጣሰው ፤ የትኛው የአየር መንገዱ አውሮፕላን እንዲመለስ እንደተደረገ እና እንዲመለስ በተደረገው አውሮፕላን ተሳፍረው ስለነበሩት መንገደኞች ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ነገር ግን ወደ ተነሳበት መድረሻ እንዳይበር ተከልክሎ ጉዞው የተስተጓጎለውን አውሮፕላን በተመለከተ ንግግር ከተደረገ በኋላ በረራው ዳግም እንዲቀጥል መደረጉን ተናግረዋል።

የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ዳውድ አዌይሳ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የያዘ አውሮፕላን ፍቃድ ስላልነበረው ወደ ሃርጌሳ እንዳይገባ ተከልክሏል ሲሉ ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል።

የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ምን አለ ?

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ8372 ፍቃድ ስላልነበረው ሃርጌሳ ላይ እንዳያርፍ ተከልክሏል።

- የኢቲ 8273 በረራ ከሶማሊያ ማግኘት የነበረበትን ፈቃድ ስላልነበረው የዓለም አቀፍ የበረራ ሕግን በመተላለፉ ወደ አገሪቱ የአየር ክልል እንዳይገባ ተደርጓል።

- ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ከተደረገው አውሮፕላን ውጪ በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረጉት መደበኛ በረራዎች ቀጥለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ...

የተለያዩ የሶማሌላንድ አክቲቪስቶች እና ጋዜጠኞ ዛሬ ወደ ሶማሌላንድ በገባው አውሮፕላን የኢትዮጵያ መንግሥት ልዩ ልዑካን ስለመኖራቸው እየገለፁ ይገኛሉ።

እኚህ ልዑካን ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር ለመምከር የመጡ ናቸው ብለዋል።

ምንም እንኳን ጋዜጠኞቹና አክቲቪስቶቹ ይህን ቢሉም የሶማሌላንድ መንግሥት በይፋ ምንም ያለው ነገር የለም።

የኢትዮጵያ መንግሥት እየተባለ ስለሚገኘው ጉዳይ ሆነ ወደ ሶማሌላንድ ልዑክ ስለመላኩ ያለው ነገር የለም።

በሌላ በኩል የሶማሊያ ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች የኢትዮጵያ ልዑካን የያዘ አውሮፕላን ወደ ሀርጌሳ እንዳይገባ መደረጉን ሲፅፉ ተስተውለዋል።

የኢትዮ-ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ በኃላ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት የሻከረ ሲሆን ሶማሊያ ኢትዮጵያ ላይ ዛቻ እንስከመሰንዘር ደርሳለች።

ኢትዮጵያ ከሶማሌለንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የትኛውንም ሀገር / አካል የማይጎዳ፣ ዓለም አቀፍ ህግንም ያልጣሰ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች። የህዝቧን ጥቅም ለማስጠበቅ በሁሉም የሰላማዊ መንገዶች ፍላጎቷን እንደምታሳካም አሳውቃለች።

@tikvahethiopia
#Somaliland

" የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን በባህላዊ መንገድ የመፍታት ዘዴ በአስገድዶ መድፈር ሰለባዎች ላይ ኢ-ፍትሃዊነትን ያሰፍናል " - ፕሬዜዳንቱ

የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ፥ ማንኛውም የአስገድዶ መድፈር ጉዳይ በፍርድ ቤት እንዲታይ እና የፍትሕ ተቋማት እንዲከታተሉ ማዘዛቸው ተሰምቷል።

ፕሬዜዳንቱ ከካቢኔያቸው አባላት ጋር ምክክር ካደረጉ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን የፍትህ አካላት እንዲከታተሉት / በፍርድ ቤት ብቻ እንዲዳኝ አዘዋል።

" አስገድዶ ደፋሪዎች ወደ ህግ ፊት መቅረብና በፍርድ ቤት መዳኘታቸው አስፈላጊ ነው " ብለዋል።

የፖሊስ ኮሚሽነር እና የጠቅላይ አቃቤ ህግ የአስገድዶ መድፈር ክስ ወደ ፍርድ ቤት መቅረቡን እንዲያረጋግጡ አሳስበዋል።

የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን በባህላዊ በሆነ መንገድ የመፍታት ዘዴ በአስገድዶ መድፈር ሰለባዎች ላይ " ኢ-ፍትሃዊነትን የሚያሰፍን ነው " ብለዋል።

የፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ የጎሳ መሪዎች የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባትን የሚከለክል እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህን ትዕዛዝ ለማስተላለፍ የተገደዱት በሶማሌላንድ ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መበራከታቸውን ተከትሎ ነው።

@tikvahethiopia
#Somaliland #Turkey

የራስ ገዟ የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሳ ካይድ ሀርጌሳ ካሉት ከቱርክ የቆንጽላ ጄነራል ሌቬንት ቼሪ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ተሰምቷል።

ንግግራቸው ሶማሌላንድ ስለሚያሳስባት ጉዳዮች እና ከቱርክ ጋር ስላላት ግንኙት ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር ተብሏል።

ምንም ዝርዝር መረጃ ግን ይፋ አልሆነም።

ንግግሩ ግን በቀጣይ አብሮ ለመጓዝ እና በትብብርም የመስራት አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት በመስጠት መጠናቀቁ ተነግሯል።

በሶማሌላንድ ያሉ በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቱርክ፣ ሶማሊያን ፦
- የምታስታጥቅ፣
- የምትደግፍ፣
- የምታሰለጥን ሀገር እንጂ የሶማሌላንድ ወዳጅ ሀገር ስላልሆነች ከእሷ ጋር ግንኙነትን ማቋረጥ እንደሚገባ እና ቆንጽላ ጽ/ቤቱ እንዲዘጋ  ጥሪ ሲያደርጉ ተመልክተናል።

ከሰሞኑን የቱርክ ስም ተደጋግሞ እየተነሳ ይገኛል።

ሀገሪቱ ኢትዮጵያና ራስ ገዟ ሶማሌላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ በሶማሊያና ኢትዮጵያ በመካከል የተፈጠረውን መቃቃር መፍትሄ እንዲያገኝ የማሸማገል ስራ እየሰራች እንደሆነ የሚገልጹ ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው።

በኢትዮጵያም ይሁን በሶማሊያም በኩል ይፋዊ መረጃ ባይሰጥም በአንካራ የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፊት ለፊት ተገናኝተው ይነጋገራሉ እየተባለ ይገኛል።

ትላንት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ በX ገጹ ከኢትዮጵያ ጋር ለሚደረግ ንግግር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚመራ ልዑክ ወደ ቱርክ አንካራ እንዳቀና ከገለጸ በኃላ መረጃውን ከገጹ ላይ አጥፍቶታል።

@tikvahethiopia
#Somaliland #US

ዛሬ በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ነበሩ።

አምባሳደር ሪቻርስ ሪሌይ ፤ ሶማሌላንድ ሀርጌሳ ሄደው ከሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ጋር መክረዋል።

ከሌሎችም ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎች ፣ የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋርም መወያየታቸው ተሰምቷል።

አምባሳደሩ ፤ አሜሪካ በቀጠናው ብልጽግናን እና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለመደገፍ የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት እንዳላት አረጋግጠዋል።

ዲፕሎማሲያዊ እና የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ቀጠናዊ ትብብር እና ውይይትን ያበረታቱም ሲሆን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የምርጫ ጊዜን በማክበር አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

ከግሉ ሴክተር መሪዎች ጋር በመገናኘት ከአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነት እንዴት እንደሚጠናከር መነጋገራቸው ታውቋል።

የነቃ ሲቪል ማህበረሰብ እና ነፃና ሙያዊ ስርዓቱን ያከበረ ፕሬስ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል ተብሏል።

ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂም ከአሜሪካው አምባሳደር ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን አሳውቀዋል።

በቀጠናዊ ጉዳዮች ፣ በአፍሪካ ቀንድ ትብብርን ማጎልበት ፣ በምርጫ ጉዳይ ፣ በሶማሌላንድ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በሶማሊያ፣ ሞቃዲሹ ያለው ኤምባሲ የዛሬውን የአምባሳደሩን የሀርጌሳ ጉብኝት በተመለከተ ያሰራጨውን የጽሁፍ መግለጫን አንዳንዶች ' ያልተለመደ ነው ' ብለውታል።

ሀገሪቱ " ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ፤ የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት " እያለች መጥራቷ በቋንቋ አጠቃቀም ላይ የታየ ጉልህ ለውጥ ነው ያሉ አልጠፉም።

የአምባሳደሩን ሀርጌሳ ላይ መገኘትን የኮነኑም አሉ። ገለልተኛ አይደሉም ሶማሊያን ይደግፋሉ በሚል።

ሶማሊያውያን ደግሞ በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ አሜሪካን መቃወም ይዘዋል።

" መግላጫው ሶማሌላድ ስለ ተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ምንም ያለው ነገር የለም " በማለት እንዲሁም " ሶማሌላንድ የሶማሊያ ግዛት እንደሆነች ሳይገለጽ መቅረቡ ሌላ ነገር ከጀርባው የያዘ ነው " በሚል ነው የተቃወሙ ያሉት።

#Somaliland
#Hargeisa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ዴሞክራሲ 👏 #ሶማሌላንድ

" የምርጫ ውጤቱን እንቀበላለን " - ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ

ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።

በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " ምርጫውን አሸንፈዋል።

በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ " የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን " ብለዋል።

ተመራጩ ፕሬዜዳንትንም " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

" ባስመዘገቡት ድል እንኳን ደስ አልዎት " ያሉት ፕሬዜዳንት ቢሂ " ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ  " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" የአገልግሎት ዘመንዎ ሰላምን ፣ እድገትን እና ዘላቂ ስኬትን ለሀገራችን እንዲያመጣ እመኛለሁ " ብለዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ቢሂ ለህዝቡ ባስተላለፉት መልዕክት " ፕሬዝዳንታችሁ ሆኜ እንዳገለግላችሁ ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ " ሲሉ ገልጸዋል።

" የስልጣን ዘመኔ ማብቂያ ላይ ሆኜ የምለው ነገር ለሀገራችን እድገት ያለኝ ቁርጠኝነት ጸኑ መሆኑን ነው " ሲሉ አክለዋል።

" በአንድነት እና በጋራ ተነስተን ለሶማሌላንድ ብልፅግና እንስራ " ብለዋል።

6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ " ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት። ከሶማሊያ መንግሥት ጋርም ግንኙነት የላትም። ላለፉት በርካታ ዓመታት ራሷን በራሷ እያስተዳደረች ነው።

እጅግ ሰለማዊ ፣ የተረጋጋ ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግ ትወደሳለች።

#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
#Somaliland

@tikvahethiopia