TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ATTENTION

የተከለከሉ ተግባራት እና ግዴታዎች ፦

- ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት።

- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዓላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና ለሽብር ቡድኖች ዓላማ መሳካት አስተዋፅዖ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር ንግግር በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጨት የተከለከለ ነው።

- በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።

- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ በተዋረድ ውክልና ከሰጣቸው አካላት ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።

- ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ወይም ሌሎች ፈቃድ ከሚሰጣቸው የፀጥታ አካላት ወይም ከነዚህ አካላት እውቅናና ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

- በከተሞች አካባቢ የነዋሪ መታወቂያ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የሰራተኛ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም ከነዚህ ተመጣጣኝ የሆነ መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

- ማንኛውም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው።

- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ የተከለከለ ነው።

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION የተከለከሉ ተግባራት እና ግዴታዎች ፦ - ሁሉም ሰው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአዋጁ መሰረት የሚያወጣቸውን መመሪያዎችና የሚሰጣቸውን ትዕዛዞች የመቀበል ግዴታ አለበት። - የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዓላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና ለሽብር ቡድኖች ዓላማ መሳካት አስተዋፅዖ የሚያደርግ፣ የሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን…
#ETHIOPIA

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ምን ማድረግ ይችላል ?

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የሃገርን ህልውና እና ሉዐላዊነት፣ እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ደህነንት ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን ፦

- በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል መከላከያ ኃይልን ወይም የትኛውንም ሌላ የጸጥታ አካል በማሰማራት ሰላምና ፀጥታ እንዲያስክብሩ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።

- እድሜያቸው ለወታደራዊ አገልግሎት የደረሱ እና የጦር መሳርያ የታጠቁ ዜጎች ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ፣ ወታደራዊ ግዳጅ እንዲቀበሉ፣ ወይም ይህን ማድረግ የማይችሉ ሲሆን በአማራጭ ትጥቃቸውን ለመንግስት እንዲያስረክቡ ሊያዝ ይችላል።

- የሰዓት ዕላፊ ገደብ ሊወሰን ይችላል።

- ማናቸውም የህዝብ የመገናኛ እና የህዝብ መጓጓዥ ዘዴ እንዲዘጋ ወይም እንዲቋረጥ ሊያዝ ይችላል።

- ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራል ብሎ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠረ ማንኛውንም ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ሥር ለማድረግ፣ ይህ አዋጅ ተፈፃሚ ሆኖ ባለበት ጊዜ ድረስ ይዞ ለማቆየት ወይም በመደበኛ ሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ ይችላል።

- ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራል ብሎ ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠረ ማንኛውንም ሰው ወይም ድርጅት ንብረት የሆነን ማኛውንም ቤት፣ ህንፃ፣ ቦታ፣ መጓጓዣ ለመበርበርና እንዲሁም ማንኛውንም ሰው ለማስቆም ማንነቱን ለመጠየቅ፣ ለመፈተሽ ይችላል፤ በብርበራ ወይም በፍተሻ የተያዙ የጦር መሳሪያዎችን መውረስ ይችላል።

- ለተወሰነ ጊዜ መንገዶችን፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለመዝጋት እንዲሁም ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ፣ ወደ ተወሰነ አካባቢ እንዳይገቡ ወይም ከተወሰነ ቦታ እንዲለቀቁ ለማዘዝ ይችላል።

- ከፍተኛ የፀጥት ችግር እና ስጋት በተፈጠረባቸው የሃገሪቱ ክፍሎች የአካባቢ አመራር መዋቅርን በከፊልም ሆነ በሙሉ፣ ማገድ፣ መለወጥ እና በሲቪልም ሆነ በወታደራዊ አመራር መተካት ይችላል።

- በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት እንቅስቃሴ በሚመለከተው ባለስልጣን በኩል እንዲታገድ ወይም ፍቃዱ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል።

- በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራል ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚያምነውን የመገናኛ ብዙሃንን ወይም ጋዜጠኛ በሚመለከተው ባለስልጣን በኩል እንዲታገድ ወይም ፍቃዱ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል።

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* ዝርዝር መረጃ ! ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል ያንብቡ። @tikvahethiopia
#የወንጀል_ተጠያቂነት

መላው ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ትገኛለች፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ድንጋጌዎች እንዲሁም አዋጁን መሰረት አድርጎ የወጡትን መመሪያዎች መተላለፍ የወንጀል ተጠያቂነትን ያመጣል ፤ ቅጣትን ያስከትላል።

ይህም የወንጀል ተጠያቂነት ፦

- የአዋጁን ድንጋጌዎች እና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ 3 አመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም እንደጥፋቱ ክብደት እስከ 10 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል።

- የአዋጁን ድንጋጌዎች እና በአዋጁ መሰረት የወጡ መመሪያዎችን በመተላለፍ የተፈፀመው ወንጀል በሌሎች ሕጎች ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣት የሚያስከትል ከሆነ የከበደው ቅጣት ተፈጻሚ ይሆናል።

- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተፈፀሙ የአዋጁ እና በአውጁ ማዕቀፍ የወጡ መመሪያዎች ጥሰቶች የአዋጁ ተፈጻሚነት ጊዜ ቢያበቃም፣ የሚያስከትሉት የወንጀል ተጠያቂነት በመደበኛው የወንጀል ሥነ ስርዐት ሕግ መሰረት ይቀጥላል።

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* ዝርዝር መረጃ ! ከዛሬ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተከለከሉ ተግባራትና ግዴታዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል ያንብቡ። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ትገኛለች።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ተመጣጣኝ ኃይልን ስለመጠቀም እና ስለማይታገዱ መብቶች ምን ይላል ?

- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተመለከቱ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን ለማስፈጸም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሕግ አስከባሪ አካላት ተመጣጣኝ ኃይል እንዲጠቀሙ መመሪያ ለመስጠት ይችላል።

- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ በሚያወጣቸው መመሪያዎች በሚወስናቸው ውሳኔዎች እና በሚወስዳቸው እርምጃዎች በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 93 (4)(ሐ) መሰረት ሊታገዱ የማይችሉ የሕገ መንግስት ድንጋጌዎችን እና
መብቶችን ማክበር ይኖርበታል።

NB : በኢትዮጵያ ከትላንት ጀምሮ ተፈፃሚ እየሆነ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሃገር ህልውና እና ሉዐላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል የታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነው።

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia
#StateofEmergencyEthiopia

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ መግለጫ ቁ.2 !

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ሀገራዊ ሁኔታ እና የአዋጁን አፈጻጸም ትላንት ማምሻውን መገምገሙን አሳውቋል።

ዕዙ ለኅብረተሰቡ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ፣ የአዋጁን አፈጻጸም እና ወታደራዊ ርምጃዎች በመገምገም የተለያዩ ድሎች መመዝገባቸውን ማረጋገጡን ገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ " በአማራና በአፋር ክልሎች የክተት አዋጁን ተከትሎ በጠላት ላይ እየተወሰደ ያለው ርምጃ አመርቂ ሆኖ ተገኝቷል" ብሏል።

" ለዚህ መሠረቱ የሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ መነሣሣትና ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የፈጠረው ንቅናቄ መሆኑ ተረጋግጧል " ሲል ገልጿል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ፥ በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ፣ በምዕራብ ሸዋ፣ በሆሮጉድሩ እና በምሥራቅ ወለጋ አንዳንድ ወረዳዎች በአሸባሪ ቡድኑ ሸኔ ላይ በክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና ሀገር መከላከያ በጋራ ከፍተኛ ድል ተጎናፅፈዋልም ብሏል።

ዕዙ ድሉን ለማስቀጠል 3 ትእዛዞችን ማስተላለፉንም ገልጿል።

(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#AWI

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጫት ቤቶች እንዲዘጉ ተወሰነ።

ብሔረሰብ አስተዳደሩ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል የመጀመሪያው ጫት ቤቶች እንዲዘጉ የሚል ነው።

በተጨማሪም ከየትኛውም ከተማ ከምሽቱ 2:00 በኋላ መንቀሳቀስ እንደማፈቀድ (በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት) ተገልጿል።

የመንግሥት እና የግል መሳሪያ የያዙ ግለሰቦች ወደ ግንባር እንዲዘምቱ ተወስኗል።

መኝታ ቤት የሚያከራዩ ሰዎች ማንነትን እንዲያረጋግጡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በተከራይ ችግር ቢፈጠር ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ማንም ሰው ተኩስ ከተኮሰ መሳሪያውን እንደሚቀማ ውሳኔ ተላልፏል።

ማንኛውም ግለሰብ በየአካባቢው ተደራጅቶ በሮንድ አካባቢውን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት የማይተባበር ከሆነ በህግ እንደሚጠየቅ ተወስኗል።

ከመንግስት በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት ድጋፍ ያላደረጉ አካላት እንዲደግፍ ፣ እንዲከፍሉ ካልከፈሉ ድርጅታቸው ታሽጎ አገልግሎት እንዳያገኙ እንዲደረግ ተወስኗል።

(አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ከላይ በዝርዝር ተቀምጧል)

#StateofEmergencyEthiopia

@tikvahethiopia