#CNNHero2019 #FerweyniMebrhatu
«አሸናፊ መሆኔ የሚገርም ነገር ነዉ። ብቻ እንደ ግለሰብ በጣም ያኮራል። ትልቁ ግን ግን ሃገርን ማስጠራት ማለት ኩራት ነዉ። ለአፍሪቃም ኩራት ነዉ። ስለዚህ ይህን ጉዳይ ጉዳያችን ብለን ለዓለም ሕዝብ ፤ ለመጀመርያ ጊዜ ለመላዉ ዓለም ያሳወቅንበት ነዉ። ጥሩ ስራ ተሰርቶአል እስካሁን ድረስ ፤ ግን ብዙ ስራ እንደሚጠብቀን ነዉ የሚያሳየን። ሆኖም ግን ብቻችንን የምንሰራዉ ስራ ስላልሆነ፤ የዓለም ሕዝብ በሙሉ ድምፅ ሰጥቶ እዚህ ደረጃ ላይ አድርሶናል። ዘንድሮ ለዉድድር ከኔጋ የቀረቡት አስሩም ጀግኖች በጣም ጥሩ ስራን ሰርተዉ ነዉ የቀረቡት። ሆኖም ግን የኛ በለጥ ብሎ የታየበት ምክንያት፤ ሁሉንም ማኅበረሰብና ዜጋ የሚነካ ጉዳይ በመሆኑ ነዉ። የሴቶች ጉዳይ ደግሞ ለዘመናት የቆየ ጮክ ብለን የማንናገርለት ችግራችን ነበር። አሁን ግን እዚህ ላይ የደረስነዉ የችግሩን መፍቺያና የግንዛቢ ማስጨበጫ በመስራታችን ነዉ። እናም ለሃገር በተለይ ጥሩ ጥሩ መፍትሄ ነዉ የሚሆነዉ። እንደ አፍሪቃዉያንም በጣም ትልቅ ኩራት ነዉ። አንድ የ «CNN» ጀግና ከአፍሪቃ ሲገኝ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ። ለ «CNN» ኖች ስለሸለሙኝ ምስጋናዬን ገልጬላቸዉ ነበር። ነገር ግን « ድምፅ የሰጠሽን ህዝብሽን አመስግኝ» ነዉ ያሉኝ መላዉ ኢትዮጵያዉያንን አመሰግናለሁ!» - ፍሬወይኒ መብርሃቱ
#DW
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#CNNHero2019 #FreweiniMebrahtu
በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሞዲስ እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ ለማቅረብ የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።
በዚሁ መሰረት የፊታችን ታህሳስ 28 ቀን 2012. ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን አስተባባሪዎቹ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ 700 ሺህ ሞዴስ እና 200 ሺሕ የሴቶች ፓንት ለማሰባሰብ እቅድ መያዙ የተገለጸ ሲሆን በመርሃ ግብሩም ከ20 ሺህ በላይ በጎ ፍቃደኞች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል።
በዚህ ዕለትም በአሜሪካው የዜና አውታር ሲ.ኤን.ኤን የአመቱ ጀግና (CNN Hero 2019) ተብላ የተሸለመቺው ፍሬወይኒ መብረሃቶም የክብር አቀባበል እንደሚደረግላት ተገልጿል።
ማንኛውን የከተማዋ ነዋሪዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚችሉትን ሞዴስ ፣የሴቶች ፓንት እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመያዝ መግባት እንደሚችሉ አዘጋጆቹ አመልክተዋል። ማንኛዉም ሰዎች የሚሉችን ሞዴስ እና የሴቶች ፓንት እንደመግቢያ መያዝ በፕሮግራሙ መታደም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የወይዘሮ ፍሬወይኒ መብራህቱ ያገኙት የሲኤን ኤን የ2019 ጀግና የስራ ፈጠራ ሽልማት ለኢትዮጵያዊያን ሴቶች ትልቅ ኩራት መሆኑን በትግራይ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕርግ የንግድና ኢንዱስቱሪና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብረሀም ተከስተ ገለጹ። የክልሉና መቐለ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች በጋራ በመሆን ለጀግናዋ ስራ ፈጣሪ ፍሬወይኒ መብራህቱ ትላንት የእንኳን ደስ አልዎት ፕሮግራም የእራት ግብዣ አድርገውላቸዋል።