TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AmharaScholarsCouncil

በአማራ ክልል የምሁራን መማክርት ጉባኤ በላከልን መግለጫ ፤ በክልሉ ውስጥ አሁን የተፈጠረው ቀውስ በዘላቂነት የሚፈታው በውይይት መሆኑን ገልጾ መንግስትና የታጠቁ ሀይሎች ተኩስ አቁመው እንዲወያዩ ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው  በመግለጫው ፤ " ሕዝባችን ባለፉት አመታት ተደጋጋሚ የሆኑ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግፎች እና በደሎች እየደረሱበት ይገኛል " ብሏል።

ይህንን ለማስቆምና መሠረታዊ ጥያቄዎቹ መልስ እንዲያገኙ በተደራጀ መልኩ መታገል እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

ይህ አይነቱ ፖለቲካዊ ትግል ዘላቂ መፍትሔ እንዲያስገኝ በ #መነጋገር እና በ #ውይይት ላይ የተመሠረተ ሊሆን እንደሚገባው አስገንዝቧል።

" በዚህ ረገድ ባለፉት አመታት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል " ሲልም ገልጿል።

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፤ " ዛሬ ሕዝባችን ዘር የሚዘራበትና የማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ዕጥረቱን ለመቀነስ አይን አይን እያየበት ያለበት ወቅት ነው። በተጨማሪም ትላንት አብረውት ተሰልፈው የተዋደቁ ኃይሎች ዛሬ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር የሚጋጩበት ሁኔታ ሊፈጠር አይገባም። " ብሏል።

ስለሆነም ክልሉ ውስጥ አሁን የተፈጠረው ቀውስ በዘላቂነት የሚፈታው በውይይት መሆኑ ታውቆ መንግስትና የታጠቁ ሀይሎች ተኩስ አቁመው እንዲወያዩ ጥሪ አቅርቧል።

በየአካባቢው ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች እና ምሁራን ሰላም እንዲሰፍን ችግሮች በውይይት እና በሰላም እንዲፈቱ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል።

(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia