TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ/ቪድዮ ፦ በኬንያ፣ ናይሮቢ በአፄ ኃይለስላሴ ስም የተሰየመ የፈጣን መንገድ መውጫ ፕላዛ ቅዳሜ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተሰምቷል።

እንደ ኬንያ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ፤ በ " ናይሮቢ ፈጣን መንገድ " ላይ የተገነባው የፈጣን መንገድ መውጫ ፕላዛ ከባለፈው ዓመት ሃምሌ 2023 አንስቶ በቻይና እና ኬንያ ተቋራጮች ሲገነባ የቆየ ሲሆን በአካባቢው ላይ ያለውን የትራፊክ ፍሰትን ያቀላጥፋል ፤ ወደ #ናይኖቢ_ከተማ ማዕከል ለመግባትም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሏል።

ይኸው የኃይለስላሴ የፈጣን መንገድ መውጫ 5 መስመሮች እንዳሉት ተጠቁሟል።

አፄ ኃይለስላሴ #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ለረጅም አመታት በንጉሰ ነገስትነት የመሩና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት - OAU / የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት - AU እንዲመሰረት ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ መሪ ነበሩ።

@tikvahethiopia