TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኢራቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1 ቀን ከ1,000 በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል። ባለፉት 24 ሰዓት 1,006 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 9,846 ደርሰዋል።

- ፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር መቻሏን አሳውቃለች።

- በዩናይትድ ኪንግደም በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ40,000 በልጧል። ባለፉት 24 ሰዓት 357 ሰዎች ሞተዋል።

- የኡጋንዳው ጠቅላይ ሚንስትር ሩሃካና ሩጉንዳ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ ራሳቸውን አግልለው ተቀምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸውን ያገለሉት ከሳቸው ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ ነው - #BBC

- ባለፉት 24 ሰዓት #በኬንያ ተጨማሪ 134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ፤ 51 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 2,474 ፣ ሞት 79፣ ያገገሙ 643 ናቸው።

- በኬንያ የኮቪድ-19 ህክምና የሚሰጥባቸው የለይቶ ማቆያ ማከሚያ ማዕከላት መሙላታቸውን ተከትሎ ለህሙማኑ ህክምና በቤት እንዲሰጥ መወሰኑን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል - #BBC

- በጅቡቲ 69 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 22 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 4,123 በቫይረሱ ተይዘዋል ፤ 1,707 አገግመዋል፣ 26 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ : ቡጢ የተሰናዘሩት የጆርዳን ፓርላማ አባላት ! የጆርዳን የፓርላማ አባላት በቀጥታ ስርጭት ላይ እየተላለፈ በነበረ ስብሰባ ላይ ክርክራቸው እና የቃላት ምልልሳቸው ወደከፍተኛ ፍጥጫ ተቀይሮ ወደ ድብድብና ቡጢ መሰናዘር ሲገቡ ታይተዋል። ይህም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። አባላቱ የሁሉንም ዜጎች የእኩልነት መብት በሚያረጋግጥ የሕገ መንግሥቱ ክፍል ላይ የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች እንዲደረጉ (የሴቶች…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : ድብድብ በኬንያ 🇰🇪 ፓርላማ !

ዛሬ ከሰአት #በኬንያ የፓርላማ አባላት አወዛጋቢ ነው በተባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች (ማሻሻያ) ረቂቅ ህግ ላይ ሲያደርጉት የነበረው ጠንከር ያለ ክርክር ተካሮ የፓርላማው አባላት ሲደባደቡ ታይተዋል።

ከሰሞኑን ብቻ ፓርላማ ውስጥ የተከሰቱ መሰል ክስተቶችን ስናጋራችሁ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ዛሬ ጥዋት የጆርንዳን ፓርላማ አባላት እንዲሁም ከቀናት በፊት በጋና የፓርላማ አባላት ክርክራቸው ጦፎ ወደ ድብደብ እና ቡጢ መሰናዘር ሲገቡ የሚታዩበትን ቪድዮ እንዳጋራናችሁ ይታወሳል።

Video Credit : TheStarKenya

@tikvahethiopia
የተመድ ፀጥታ ም/ቤት በኢትዮጵያ ገዳይ መክሯል ?

ትላንት ለሊት የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ #ኢመደበኛ_ዝግ ስብሰብ ያደርጋል ተብሎ ነበር። ስብሳባው ስለመደረግ አለማደረጉ እስካሁን በይፋ የሚታወቅ ነገር የለም።

ስለዚህ ስብሰባ የሚታወቀው ነገር የሚከተለው ነው ፦

- ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ መስከረም 2 (እኤአ) አይርላንድ ከአልባኒያ ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጋር በመሆን ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ በክፍት እንዲሰብሰብ ጠይቃ ነበር። አይርላንድ " በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በግጭት ምክንያት በረሃብ እየተሰቃዩ በመሆናቸው ለሰብአዊ ዕርዳታ እንቅፋት የሚሆኑ ነገሮች በጣም ያሳስበናል " በሚል ነው ክፍት የሆነ ስብሰባ እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርባ የነበረው፤ ሀገሪቱ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙና በአፍሪካ ህብረት (AU) ወደሚመራው የሰላም ንግግር እንዲመለሱ እንደምትፈልግ ነው የገለፀችው።

- የክፍት ስብሰባ ጥያቄው በ #A3 ሀገራት ማለትም #በኬንያ#በጋቦን እና #በጋና ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ሀገራቱ ይህን የስብሰባ ይዘት የተቃወሙ ሲሆን የተስማማቱ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) እንዲካሄድ ነው። ይህም ኢትዮጵያ የምትመርጠው አይነት የስብሰባ ይዘት እንደነበር ተነግሯል።

ℹ️ መደበኛ ያልሆነ ስብሰባ (IID) ማለት ምንድነው ? IID መደበኛ ያልሆነ ዝግ ስብሰባ ሲሆን የምክር ቤት አባላት ያልሆኑትን እንዲሳተፉ የሚያስችልም ነው። የዚህ  የስብሰባ ይዘት የስብሰባ መዝገቦች የሌሉት ሲሆን በም/ቤቱ ወርሃዊ የስራ መርሃ ግብር ውስጥም አይካተትም።

- አይርላንድ ሁሉም ወገኖች በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ጦርነት እንዲያቆሙ እና ለተቸገሩ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚጠይቅ ረቂቅ ጋዜጣዊ መግለጫ አሰራጭታ ነበር ሆኖም ግን #A3#ቻይና እና #ሩሲያ በረቂቅ ጽሑፉ ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ አልነበሩም። ሀገራቱ መግለጫውን ከስብሰባው በኃላ ከግምት ውስጥ ማስገባትን ነው የመረጡት ተብሏል። በዚህም በመግለጫው ላይ የነበረ ውይይት ባለበት እንዲያዝ ተደርጓል።

- ትላንትና ይካሄዳል የተባለው እና እስካሁን ተካሂዶ ስለመሆን አለመሆኑ በይፋ ያልታወቀው የተ.መ.ድ. ፀጥታ ምክር ቤት የIID ስብሰባ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሃና ተቴህ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ነበር። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆም አጭር መግለጫ እንዲሰጡ ተጋብዘው እንደነበር ታውቋል ፤ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ እንድትሳተፍም ተጋብዛ ነበር።

- ትላንት ለሊት በተያዘው እቅድም መሰረት ኢመደበኛ ስብሰባው (IID) መካሄዱ ከተረጋገጠ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ዳግም ካገረሸ በኃላ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነጋገረበት ነው የሚሆነው።

መረጃው ከSCR ፣ ከተመድ የአይርላንድ እና ኖርዌይ ተልዕኮ ፅ/ቤት የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመጨረሻው ዙር።
#Update

የሀገራችን ልጆች በውድድሩ ብርቱ ትግል ቢያደርጉም ድል አልቀናቸውም።

የ5000ሜ የሴቶች ፍፃሜ ውድድር #በኬንያ አትሌት ኪፕዬጎን የበላይነት ተጠናቋል።

ሁለተኛ ሲፋን ሀሰን ወጥታለች።

ሶስተኛ እና አራተኛ ኬንያ አትሌቶች ሲሆኑ ፤ አምስት ፣ ስድስት ፣ ሰባት የኢትዮጵያ አትሌቶች ወጥተዋል።

@tikvahethiopia