TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሂጃብሂጃብ #አክሱም

" ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ #እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ ታዟል " - ፍርድ ቤት

በአክሱም ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎችን ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ክልከላ አድርገዋል በተባሉት አካላት ላይ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ህጋዊ ክስ መስርቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ከምክር ቤቱ ጠበቃ አረጋግጧል።

በተመሰረተው ክስ መሰረት ተከሳሾች ለጥር 16/2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸው እንዲሰጡ የመጥሪያ ትእዛዝ ተፅፎላቸዋል።

የአክሱም ከተማ ፍርድ ቤት ለተከሳሾች የፃፈው የመጥሪያ ትእዛዝ ሙሉ ይዘት ምን ይላል ?

ከሳሽ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሲሆን ተከሳሾች ደግሞ :- 
የአክሱም ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት
የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 
አብራሃ ወ አፅብሃ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ወርዒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ክንደያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ናቸው።

በዚሁ ደብዳቤ ላይ ተከሳሾች በወሰኑት አስተዳደራዊ ውሳኔ መሰረት የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን በቀረበቅ ማመልከቻ መረዳት እንደተቻለ ተገልጿል።

ፍርድ ቤቱ ፤ የተሰጠው አስተዳደራዊ ውሳኔ እግድ ካለተጣለበት በሴት ተማሪዎቹ ላይ የማይመለስ የመብት ጥሰት ሊያጋጥም ስለሚችል ተከሳሾች የሰጡት አስተዳደራዊ ትእዛዝ መዝገቡ እልባት እስኪያገኝ ወይም ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ
እንዳይተገበር ለጊዜው በእግድ እንዲቆይ አዟል።

ተከሳሾችም በቀረበው የእግድ ማመልከቻ መሰረት ቀርበው ቃል እንዲሰጡ በፍርድ ቤቱ ለቀን 16/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተቀጥረዋል።

NB. ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደብዳቤውን ትክክለኝነት ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠበቃ ማረጋገጥ ችሏል።

159 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከሂጃብ ክልከላ በተያያዘ ትናንት የተጠናቀቀውን 12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የሚያስችላቸውን ፎርም ሳይሞሉ መቀረታቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መግለጹ ይታወሳል።

ጉዳዩን እስከመጨረሻውን የምንከታተለው ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia