TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" አሁኑኑ የተሰረቀውን ነዳጅ መልሱ " - WFP የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊ ድርጅታቸው ለእርዳታ ሥራው የሚያውለውን 570,000 ሊትር ነዳጅ " የትግራይ ባለሥልጣናት ሰርቀዋል " ብለዋል። " ምግብ ለማድረስ ነዳጅ ከሌለን በሚሊዮኖች ይራባሉ " ያሉት ቢዝሊ ድርጊቱን " የሚያስቆጣ እና አሳፋሪ " ብለውታል። አሁኑን የተሰረቀው ነዳጅ እንዲመለስ ጠይቀዋል። @tikvahethiopia
#WFP #UN

" ነዳጁ በቅርቡ በWFP የተገዛ እና ከመሰረቁ ጥቂት ቀናት በፊት መቐለ የደረሰ ነበር " - WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ከመቐለ ተሰረቀ ባለው ነዳጅ ጉዳይ ላይ በዋና ዳይሬክተሩ ዴቪድ ቢዝሊ በኩል ማብራሪያ ሰጥቷል።

ዋና ዳይሬክተሩ ትላንት ጥዋት የተዘረፈው ነዳጅ ከግማሽ ሚሊዮን ሊትር  በላይ (12 ታንከር) መሆኑንና የታጠቁ ቡድኖች ወደ WFP ግቢ ገብተው መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

ነዳጁ በቅርቡ በWFP የተገዛ እና ከመሰቀሩ ጥቂት ቀናት በፊት የደረሰ መሆኑን አስረድተዋል።

WFP ያለ ነዳጁ ምግብ፣ ማዳበሪያ፣ መድሃኒት እና ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎችን በመላው ትግራይ ሊያደርስ እንደማይችል ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጄነሬተሮችን እና ተሽከርካሪዎች ለማንቀሳቀስ እንደሚቸገር የገለፀው WFP 5.2 ሚሊዮን የሚደርሰውን ረሃብ የተጋረጠበትን ህዝብ ለመድረስ እንቅፋት እንደሚሆንበት አስረድቷል።

የነዳጁ መሰረቅ በግጭት ሳቢያ እየተፈተነ ያለውን በትግራይ ያለውን ማህበረሰብ ወደ ረሃብ አፋፍ ይገፋል ብለዋል።

የትግራይ ባለስልጣናት በአስቸኳይ የነዳጅ ክምችቱን እንዲመልሱ አሳስበዋል።

ህወሓት በበኩሉ " ከወራት በፊት ለዓለም ምግብ ፕሮግራም ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስድኩ እንጂ ዘረፋ አልፈጸምኩም " ሲል መልሷል።

ዋና ዳይሬክተሩ መሰል አስተያየት ከመስጠታቸው በፊት ዝርዝር ሁኔታውን ማጣራት ነበረባቸው ብሏል።

ከ600 ሺ ሊትር በላይ ነዳጅ ለWFP አበድርያለሁ ያለው ህወሓት " በነበረን ስምምነት መሠረት ያበደርነውን ነዳጅ ተመላሽ እንዲሆን ነው የጠየቅነው " ሲል ገልጿል።

የወሰድነው ነዳጅ እንደ ሆስፒታል ፣ ክሊኒክ እና ሌሎች የጤና ማዕከላትን ለማንቀሳቀስ ጥቅም ላይ ይውላልም ሲሉ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተርን ክስ አጣጥሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USAID " ... ኢትዮጵያውያን ሲቪሎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው። የተዘረፈውን ነዳጅ መልሱ  " - ሳማንታ ፓወር የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ፤ ህወሓት (TPLF) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስራ የሚጠቀምበትን 150,000 ጋሎን ነዳጅ መዝረፉን በመግለፅ ድርጊቱን አጥበቀው አውግዘዋል። በተጨማሪም በእርዳታ ሰራተኞች…
#UN_OCHA

" ውጤቱ እስከፊ ሊሆን ይችላል " - ማርቲን ግሪፊትስ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በትላንት በስቲያ በትግራይ ክልል፣ መቐለ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል የነዳጅ ታንከሮች መወሰዱን መስማታቸው እጅግ እንደረበሻቸው ገልፀዋል።

የነዳጅ ታንከሮቹ 12 መሆናቸውን ያመለከቱት ግሪፊትስ 570,000 ሊትር ነዳጅ መያዛቸውን ገልፀዋል።

ነዳጁ ተመድ እና አጋሮቹ በከፋ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሰዎች አስፈላጊ ድጋፍ ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን አመልክተዋል።

ያለዚህ ነዳጅ ሰዎች ያለ ምግብ፣ ያለ ድጋፍ ሰጪ ንጥረነገሮች፣ ያለ መድሃኒት እና ያለሌሎች ወሣኝ አስፈላጊ ነገሮች ይቀራሉ ብለዋል።

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና የምግብ ዋስትና እጦት እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት #ውጤቱ_አስከፊ_ሊሆን_ይችላል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ይህን መሰሉን ድርጊት አወግዛለሁ ያሉት ግሪፊትስ " የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች በመላው ኢትዮጵያ ሊጠበቁ ይገባል። የሰብዓዊ ዕርዳታ ማደናቀፍ መቆም አለበት " ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ የባንክ ፣ የመብራት እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲመለሱ የጠየቁ ሲሆን ይህ በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ ለማሻሻል አስተዋፆ እንዳለው አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
#UN_ETHIOPIA

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ህወሓት ህፃናትን ለውትድርና እየመለመለና ህፃናትን በህዝብ ማዕበል ስትራቴጂ እየተጠቀመ ነው ሲሉ ገለፁ።

አምባሳደሩ ፥ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ዓይነት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎችንም ፤ " እውነት ስለ ህፃናት ያሳስበናል የምትሉ ይህን ድርጊት አውግዙ " ብለዋል።

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ዳግም ካገረሸ ቀናት ተቆጥረዋል። አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ወታደራዊ ግጭቶች መቀጠላቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA " አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው። ብሊንከን ፤…
#UN #EU

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በአስቸኳይ ለማቆም እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ማሳወቁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።

በተጨማሪ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው የሰላም ሂደት ፍቃደኛ መሆኑን አበረታተዋል።

ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ይህንን እድል ለሰላም እንዲጠቀሙበት እና ግጭት እንዲቆም እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንዲሁም ለውይይት አማራጭ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁለቱም በቅን ልቦና ሳይዘገዩ እንዲሁም ለውይይቱ መካሄድ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አበረታተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ዋና ፀሀፊው በመጨረሻም አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን የደስታ እና የሰላም እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአውሮፓ ህብረት የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአስቸኳይ ግጭት ለማቆም እና በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን መግለፁን ተከትሎ " አሁን ፤ ይህንን እድል ሁሉም ሊጠቀምበት ይገባል " ብሏል።

የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ ህብረትን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#UN

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በሽሬ ያሉ ሲቪሎች እና የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ደህንነት ያሳስበኛል ብለዋል።

ግሪፊትስ ፤ በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ገልፀው ፤ " ትላንት ሁለት የፊት መስመር ሰራተኞች መቁሰላቸውን ሰምቼ ደንግጫለሁ " ብለዋል።

" ጦርነቱ እነሱ ወዳሉበት እየቀረበ መሆኑን ተከትሎ ያደረባቸውን ጭንቀት እጋራለሁ " ያሉት ግሪፊትስ ፤ " ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ እስከዚያው ድረስ ግን ሲቪሎችን እና የረድኤት ሰራተኞችን እንዲጠብቁ በድጋሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#UN

እ.ኤ.አ. ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሰብአዊ ድጋፍ አጋሮች አማካኝነት ከ17,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የእርዳታ እህል ትግራይ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዛሬ አሳውቋል።

ድርጅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ተጨማሪ በግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለመድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እስራኤል ኔታኒያሁ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ከእስራኤል ለማስወጣት ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸው ተነገረ። በትላንትናው ዕለት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ በኤርትራዊያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን አስከፊ ግጭት ተፈጥሮ ነበር። ይህን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ደም በተቃባው ግጭት ላይ የተሳተፉት ስደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።…
#Update #UN

እስራኤል ኤርትራውያንን በጅምላ ከማባረር እንድትቆጠብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠይቋል።

የእስራኤል ባለሥልጣናት በዛቱት መሠረት ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሀገሪቱ የሚያስወጡ ከሆነ፣ “ዓለም አቀፍ ሕግን እንደሚተላለፉ” እና ከፍተኛ ሰብዓዊ ችግር እንደሚያስከትልም ድርጅቱ አስታውቋል።

በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከል፣ ባለፈው ቅዳሜ በቴል አቪቭ - እስራኤል በተፈጠረ ግጭት፣ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውንና ንብረት መውደሙን ተከትሎ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት፣ በግጭቱ የተሳተፉ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከሀገር እንደሚያስወጧቸው ዝተው ነበር፡፡

የኤርትራን 30ኛ ዓመት የነፃነት ቀን አስመልክቶ፣ በቴል አቪቭ ተዘጋጅቶ በነበረ ክብረ በዓል ላይ፣ የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች በአንድ ወገንና ተቃዋሚዎች በሌላ ወገን ተሰልፈው በተፈጠረ ኀይል የተቀላቀለበት ግጭት ዐያሌዎች ተጎድተዋል።

የፖሊስ አባላትም ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የተፈጠረው ግጭት እጅግ እንዳሳሰበው የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ገልጾ፣ መረጋጋት እንዲኖር እና ሁለቱም ወገኖች ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ጠይቋል።

ባለፈው ሰኔ በወጣ መረጃ፣ 17 ሺሕ 850 ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች በእስራኤል እንደሚገኙ ታውቋል።

በግጭቱ 170 ጥገኝነት ጠያቂዎች እና በደርዘን የሚቆጠሩ የእስራኤል ፖሊስ አባላት እንደተጎዱ የስደተኞች ኮሚሽኑ ገልጿል።

(ቪኦኤ)
ቪድዮ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
A_HRC_54_55_AdvanceUneditedVersion.docx
79.2 KB
#ETHIOPIA #UN

ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት እንዲቆም ስምምነት ከተፈረመ አንድ አመት ሊሞላው ቢቃረብም አሁንም ግፍ፣ የጦር ወንጀሎች እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ነው ሲል በተመድ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አሳወቀ።

ኮሚሽኑ የሰላሙ ሁኔታ አሁንም ያልተረጋገጠ መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ባወጣው ባለ 21 ገጽ ሪፖርቱ ከህዳር 3 ቀን 2020 ጀምሮ በግጭቱ ውስጥ በተሳተፉ #ሁሉም_አካላት የተፈፀሙ መጠነ ሰፊ አሰቃቂ ድርጊቶችን አስፍሯል።

ከእነዚህም ውስጥ ፦
- የጅምላ ግድያ፣
- አስገድዶ መድፈር፣
- ረሃብ፣
- የትምህርት ቤቶች እና የህክምና ተቋማት ውድመት፣
- የግዳጅ / በኃይል ማፈናቀል እና የዘፈቀደ እስራት ይገኙበታል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሀመድ ቻንዴ ኦትማን ፤ " የሰላም ስምምነቱ መፈረሙ በአብዛኛው የመሳሪያ ድምፅ ጸጥ ያሰኘው ቢሆንም ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በትግራይ ያለውን ግጭት አልፈታም ወይም ምንም አይነት አጠቃላይ የተሟላ ሰላም አላመጣም " ብለዋል።

" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርስ የመብት ጥሰት እና በትግራይ እየተፈጸመ ያለ ግፍን የሚገልጹ ሪፖርቶች እንዳሉት ኮሚሽኑ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ያፋ ባደረገው ሪፖርት፤ የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ጥሰቶችን መፈፀም መቀጠላቸውን አመልክቷል። ይህም ስልታዊ የሆኑ አስገድዶ መድፈር፣ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃቶችን እንደሚያካትት አመልክቷል።

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት ሃይሎች ይፈፀማል ስላለው የሰላማዊ ዜጎች እስራት እና የማሰቃየት ድርጊትን በተመለከተ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።

በተጨማሪም ፤ በቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ተወላጅ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያሳዩ በርካታ ሪፖርቶችን እንዳገኘ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ እና ለጭካኔ ወንጀሎች የሚያጋልጡ ሁኔታዎች መኖራቸው በእጅጉ እንደሚያሳስበው አመልክቷል።

ይህ ሁኔት በኢትዮጵያ እንዲሁም በሰፊው ቀጣና መረጋጋት ላይ እንዲሁም በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ህፃናት ላይ እንድምታ እንዳለው ገልጿል።

https://www.ohchr.org/en/press-releases/2023/09/ethiopia-nearly-one-year-after-ceasefire-un-experts-warn-ongoing-atrocities

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
Report_of_the_Ethiopian_Human_Rights_Commission_EHRC_and_the_Office.PDF
1.6 MB
#EHRC #UN #ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ከሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም - መጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ከተጎጂዎችና ጉዳት ከደረሰባቸው ማኅበረሰቦች ጋር ባደረጉት ምክክር የተገኙ ግኝቶችን በተመለከተ ይፋ ያደረጉት ባለ 90 ገጽ ሪፖርት ከላይ ባለፈው ፋይል ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#FoodandAgricultureOrganization #UN

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ  የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸለሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ሽልማት የተሰጣቸው ዛሬ በጣልያን፤ ሮም ከተማ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO) ፤ ሮም ውስጥ ባሰናዳው ዝግጅት ዶ/ር ዐቢይ ፤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያደረጉ ላለው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ እንዳበረከተላቸው ተነግሯል።

የፋኦ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኩ ዶግዩ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፋኦ ከፍተኛ ሽልማት ለሆነው አግሪኮላ ሜዳልያ ሽልማት በመብቃታቸውን " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

ይህ ሽልማት መሪዎች እና ሌሎችም የዓለማችን እውቅ ሰዎች የምግብ ዋስትናናን ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ድህነትን ለመቀነስ ለሚያደርጉት የተሳካ ጥረት የሚሰጥ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህም የአግሪኮላ ሜዳሊያ ለጠ/ ሚኒስትሩ እየተበረከተው ፦
* በኢትዮጵያ ገጠርና ኢኮኖሚ ልማት ላይ ላበረከቱት አስተዋፅኦ
* በተለይም " በስንዴ፤ ምግብ እራስን መቻል ፕሮግራም " ባደረጉት የግል ድጋፍ
* በኢትዮጵያ አረንጓዴ ሌጋሲ (Green Legacy) ስራ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈ ዋና ዳይሬክተሩ " ባለፉት 5 አመታት ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችውን አስደናቂ እድገት ተመልክቻለሁ " ማለታቸው ተነግሯል።

ይህ ሊሆን የቻለው " በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰጡ ውጤታማ፣ ተጠያቂነት ያለውና የተረጋጋ አመራር ነው " ያሉት የፋኦ ዋና ዳይሬክተር ፤ ተመልክቼዋለሁ ያሉት እድገት የተመዘገበው " ባለፉት ዓመታት በነበሩ አስቸጋሪ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ነው ፤... ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን እንደ አህጉር ለአፍሪካም ይልቅ መልዕክት ነው " ማለታቸው ተሰምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው የተሰጣቸውን ሽልማትና እና እውቅናን ተከትሎ ባሰራጩት መልዕክት ምስጋና አቅርበው ፤ " ከፍ ያለ ጠቀሜታ ባላቸውና የኢንደስትሪ ግብዓት በሆኑ የግብርና ምርቶች ላይ ማተኮራችን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያስገኘልን ይገኛል። የምግብ ሉዓላዊነት ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን " ብለዋል።

የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያን በተሸለሙበት ወቅት የፋኦ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ እና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ነበር ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፋኦ ድረገፅ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia