#EHRDC
የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ቡድን በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በሚገኙበት ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ መመልከቱን አሳውቋል።
ቡድኑ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በመገኘት በእስር ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ መአዛ መሐመድ ፣ ጋዜጠኛ መስከረም አበራን መጠየቁን አመልክቷል።
ጉዳያቸውንም በንቃት እየተከታተለው መሆኑንም ማዕከሉ አሳውቋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC #EHRDC
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል በኢፌድሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ታግደዋል።
ስለ እግዱ ኢሰመጉ ምን አለ ?
ላለፉት 33 አመታት በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ፥ ዲሞክራሲ እንዲስፍን እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ከፍተኛ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ አንጋፋ ድርጅት እንደሆነ ገልጿል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሠልጣን ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ በቀን ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ድርጅቱ በደረሰው መሰረት እገዳ እንደተጣለበት አመልክቷል።
ምክንያት የተባለው ምንድነው ?
ለኢሰመጉ መታገድ ምክንያት የተባለው ፤
° ከተቋቋመለት አላማ ውጪ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ፤
° ገለልተኛ እንዳልሆነ፤
° በ2023 የበጀት አመት የአስተዳደር ወጭ ገደብ ጠብቆ ባለመስራቱና ኃላፊነት በጎደለው መልኩ እየተንቀሳቀሰ ነው በሚል ነው ድርጅቱን ከማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ የታገደው።
ሆኖም ዕግዱን ተከትሎ ኢሰመጉ በጉዳዩ ላይ ለማንኛውም መገናኛ ብዙሃን የሰጠው መግለጫ የለም።
ኢሰመጉ ፤ ሁሌም ቢሆን ሕግና ስርዓትን ጠብቆ የሚንቀሳቀስ ነፃና ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ድርጅት መሆኑን ገልጾ በአሁኑ ሰዓት ዕግዱ በሚነሳበት ሁኔታ ላይ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
በዚህም ምንም አይነት መግለጫ የማውጣት ሃሳብ አልነበረውም።
ሆኖም ግን በማህበራዊ ድረገጽ ኢሰመጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረጉ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች እንደታገደ የሚገልጹ ጽሁፎች እየተንሽራሽሩ በመሆናቸው መግለጫ ለማውጣት መገደዱን አመልክቷል።
ድርጅቱ በማሀበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተንሽራሸሩ የሚገኙት ሃሳቦች በባለስልጣኑ ስለዕግዱ ከተሰጡት ምክንያቶች ጋር ፈጽሞ የማይገናኙ የኢሰመጉን ዓላማና ተግበር የማይወክሉ እና መልካም ስራውን ለማጥፋት የሚደረጉ ሙከራዎች ናቸው ብሏቸዋል።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ምን አለ ?
ባለፉት አራት አመታት ድርጅቱ በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየ መሆኑን በዋነኝነት ለበርካታ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት እና የውትወታ (advocacy) ስራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ ገልጿል።
ድርጅቱ የተቋቋመለትን አላማ ሊያሳካ በሚያስችል መልኩ የአገሪቱን ህጎች ባከበረና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ እንደ አንድ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑን ጠቁሟል።
ይሁንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት በፃፈው ደብዳቤ ድርጅቱ ከማንኛውም እንቅስቃሴዎች እገዳ የተጣለበት መሆኑን ገልጿል።
ምክንያት ?
" ባለስልጣኑ በድርጅቱ ላይ ባደረገው የክትትልና ግምገማ ስራዎች ድርጅቱ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ መንቀሳቀሱ፣ ገለልተኛ አለመሆኑ፣ ግልፅ የሆነ የአደረጃጀት መዋቅር የሌለው መሆኑ እና ሃላፊነት በጎደለው መልኩ የተንቀሳቀሰ መሆኑ በተደረገ ክትትልና ግምገማ ለማረጋገጥ መቻሉ ነው " ተብሏል።
ድርጅቱ ግን ከተመስረተበት ጊዜ አንስቶ ከተቋቋመበት አላማ ውጪ በየትኛውም ያልተገባ ወይም ከህግ የሚጻረር እንቅስቃሴ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የማያውቅ መሆኑን ገልጿል።
ድርጅቱ በማያውቀው መልኩና ሃሳቡም በህግ አግባብ ባልተጠየቀበት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ክትትልና ግምገማ ያካሄደ መሆኑን ገልጾ የተጣለው እገዳ አግባብነት እንደሌለው እና ህግን የተከተለ እንዳልሆነ በመግለፅ በእግዱ ላይ በቂ ማብራሪያ እንዲሰጠው የሚጠይቅ ደብዳቤ ዛሬ ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ያስገባ መሆኑን አሳውቋል።
ዝርዝር ማብራሪያ የመጠየቂያ ደብዳቤ አይቶ ውሳኔ እስኪሰጠን ድረስ ድርጅታችን ከየትኛውም ሥራዎቹ ታግዶና ጽ/ቤቱም ተዘግቶ የሚቆይ መሆኑን የአገልግሎቶቻችን ተጠቃሚ ለሆኑ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች፣ ለአጋር ድርጅቶች እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ እናሳውቃለን፡፡
እገዳ የተጣለበት ድርጅቱ ፅ/ቤቱ ተዘግቶ እንደሚቆይ አመልክቷል።