TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመንገደኞች እንግልት እና የመንግስት አካላት ምላሽ !

ከአማራ ክልል በተለይም #ከሰሜን እና #ደቡብ_ወሎ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ብዙዎች እየተንገላቱ ነው።

ይህ ጉዳይ አንድ ወቅት ጠንከር አንዴ ላላ ፤ ያዝ ለቀቅ እያደረገ አሁንም ድረስ ቀጥሏል።

አንዳንዶች በብዙ ልመና ነው የሚያልፉት።

ወደ መጣችሁበት ተመለሱ የሚባሉ ወገኖች ምክንያት ቢጠይቁም በግልፅ አስረድቶ የሚነግራቸው አላገኙም።

ለመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ምን አሉ ?

👉 " ... መላ ሊባልለት የሚገባ ነገር ነው። ከደሴ ተነስተን ወደ አ/አ እየሔድን ነበር ግን " ሸኖ " ላይ የአማራ ክልል መታወቂያ ይዛችሒ አትገቡም ተብለን ስንጉላላ ቆይተን ሹፌሩ ይዘሐቸው ተመለስ ተብሏል። ሌሎቹ ተመልሰዋል። እኔ ግን ግድ መሔድ ስላለብኝ ለፈተና ባጃጅም በግሬም ኡ/ ገብቻለሁ ፡፡ እባካችሁ ዛሬ ብቻ አደለም ያዝ ለቀቅ እያደረጉ ነው እንጅ ከብዶናል "

👉 " እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አሁንም ድረስ ከወሎ መዳረሻቸውን አ.አ አርገው የሚመጡ ተሳፋሪዎች ከበኬ ኬላ አየተመለሱ አሌልቱ ላይ ብዙ እንግልት እየገጠማቸው ይገኛል "

👉 " ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለው ብዙዎች ሲንገላቱ ቆይተው ወደ ኃላ እንዲመለሱ ተደርገዋል። እኛ በብዙ ልመና ለህክምና ነው ብለን አልፈናል። "

#ሪፖርተር_ጋዜጣ ያነጋገራቸው ፦

👉 " ሐምሌ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. መነሻችንን ከወልዲያ ከተማ አድርገን ወደ አዲስ አበባ ስንጓዝ የአማራ ክልልን አልፈን ኦሮሚያ ክልል ስንገባ ተደጋጋሚ ፍተሻ ተደርጎልናል። ለገዳዲ ከደረስን በኃላ ግን የአዲስ አበባ መታወቂያ የላችሁም በሚል ምክንያት ወደ ደብረ ብርሃን መልሰውናል። ሁኔታው በጣም አሳዛኝ ነው ።

ከሸኖ ከተማ ጀምሮ እስከ ሰንዳፋ ድረስ የተደረገብን ፍተሻ በጣም አድካሚ ከመሆኑም በላይ፣ የአዲስ አበባ መታወቂያ የላችሁም በሚል ሲሳለቁብን ማየት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አሳፋሪ ተግባር ነው።

ፖሊሶች ፍተሻ ካደረጉ በኋላ የአዲስ አበባ መታወቂያ የሌላቸውን እዚያው ክልላቸው ወስደህ አውርዳቸው በማለት ለሾፌሩ ተናግሯል።

በዚህም የተነሳ በግዴታ ለገዳዲ ከደረስን በኋላ እንደገና ተመልሰን ደብረ ብርሃን ከተማ አድረናል። በስተመጨረሻም በነጋታው የቤት መኪና ተከራይተን ለቅሶ እንደምንሄድ በመናገር አዲስ አበባ ገብተናል።

የተፈጠረውን ክስተት አስከፊ ነው። በጊዜው ገንዘብ ስለነበረን ከፍለን ተመለስን ነገር ግን ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ከመኪና እንዲወርዱ ሲደረጉ ሕፃን ልጅ የያዙ እናቶች ጭምር ለመመለሻ የሚሆን ገንዘብ አጥተው ሜዳ ላይ ወድቀው ነበር።

ይህን ያህል አማራ ምን አድርጎ ነው ? ወስደህ አውርዳቸው እንዴት ይባላል ? ኢትዮጵያዊ አይደለንም ወይ ? ብዙ ግፍ ያለበት ክልል እኮ ነበር፣ በአማራ ላይ ይህ ሁሉ ሲደረግ ሕግ አለ ወይ ያስብላል ? "

👉 " አደራው ኃይሌ እባላለሁ ከደሴ ከተማ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ እየተጓዝኩ ነበር 100 ኪሎ ሜትር በማይሞላ ርቀት ውስጥ ከጫጫ ከተማ እስከ ለገዳዲ ከተማ ቢያንስ 7 ጊዜ ተፈትሸናል።

የመጨረሻው የአዲስ አበባ መግቢያ ፍተሻ በነበረው ለገዳዲ ስንደርስ ከጥቂት የአዲስ አበባ ከተማ መታወቂያ ከያዙ ሰዎች ውጪ ቀሪዎቹ ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል።

ድርጊቱ በጣም የሚያሳዝን ነው።

ከመኪና እንድንወርድ ከተደረገ በኋላ ስልካችንን ከፍተን በውስጥ ያሉ ምሥሎችና ድምፆችን ከፍተን እንድናሳይ ተደርጓል።

👉 " ሁኔታው የሕግ ድጋፍ ያለው እንደማይመስልና አልፎ አልፎ ፖሊሶቹ በመሰላቸው አሠራር እንጂ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የሚፈቅድ ምንም ዓይነት የሕግ መሠረት ማቅረብ አይቻልም።

ድርጊቱ አሳፈሪ በመሆኑ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ለጉዳዩ አፋጣኝ መልስ መስጠት ካልቻለ፣ እንደ አገር አብሮ በኖረ ሕዝብ ላይ አሁን ያለው የፖለቲካ ግለት ተጨምሮበት የባሰ ቁርሾ፣ እርስ በርስ የመለያየትና ከፋፋይ የሆነ አጀንዳ ይሆናል "

የመንግስት አካላት ምን አሉ (ለሪፖርተር ጋዜጣ) ?

▪️የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ፦

" ጉዳዩ ስለመከሰቱ መረጃ አለኝ። ነገር ግን የሕወሓት ሠርጎ ገቦችን ለመያዝ በሚል ግልጽ ባልሆነ መንገድ ዜጎች እየተንገላቱ በመሆኑ ጉዳዩን ለኦሮሚያ ክልል መፍትሔ እንዲሰጥበት አሳውቀናል። "

▪️የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አራርሳ መርዳሳ ፦

ጥያቄ ከሰሙ በኋላ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

▪️የሰሜን ሸዋ ዞን የፀጥታና አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ ፦

" ጉዳዩ መከሰቱን መረጃ አለኝ።

ተሳፋሪዎች ደብረ ብርሃን ከተማ ካለፉ በኋላ እንዲህ ዓይነት ችግር ተፈጥሯል።

ከኦሮሚያ ክልልና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ደውላችሁ አጣሩ "

▪️የአዲስ አበባ የፀጥታ ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ፦

" ስለሚባለው ጉዳይ ምንም ዓይነት መረጃ የለንም "

▪️የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፦

" የተጠቀሰው ጉዳይ አይመለከተንም "

▪️ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሪት ሰላማዊት ካሳ ፦

" ጉዳዩ የሕወሓት የሽብር ቡድን በወረራ ይዟቸው ከነበሩት የአማራ ክልል አካባቢዎች የተለያዩ የመታወቂያ ማኅተሞችና የአስተዳደር ሰነዶችን በመዝረፉና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህን ሐሰተኛ መታወቂያዎች ሰነዶችን የያዙ ሠርጎ ገቦች ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ ሲሉ በመያዛቸው ምክንያት የሚደረግ የክትትል ሥራ ነው።

የጥፋት ተልዕኮ የያዙና ከአማራ ክልል ተዘርፈው በተወሰዱ ሰነዶች ተመሳስለው የተሰሩ መታወቂያዎችን የያዙ ግለሰቦች አሁንም ወደ አዲስ አበባ ለመግባት የሚያደርጉት ጥረት እንዳለ ለፀጥታ ኃይሎች መረጃው በመድረሱ ይህንን ለመከላከል ጥብቅ ፍተሻዎችና ማጣራቶች እየተደረጉ ነው።

ይሁን እንጂ አዲስ አበባን የጥፋት ተልኳቸው መዳረሻ ለማድረግ እየሞከሩ ያሉትን አካላት ለመከላከል በሚወሰደው ዕርምጃ፣ በመንገደኞች ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩንና ዜጎችም ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን የተመለከቱ ቅሬታዎች ደርሰውናል።

ይህም በደኅንነት ፍተሻና ማጣራት አፈጻጸም ላይ መሻሻል ያለበትን ሁኔታ ለይቶ የፀጥታ ኃይሉ የማስተካከያ ዕርምጃ እንዲወስድ ይደረጋል ። "

▪️የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የአብን ከፍተኛ አመራር አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ፦

" ... ከአማራ ክልል የወሎ አካባቢዎች ተነስተው መዳረሻቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዜጎች ኦሮሚያ ክልል ሸኖ ሲደርሱ መታወቂያቸው እየታየ ከተሳፈሩበት መኪና እንዲወርዱና ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጉን ተጨባጭ መረጃዎች አሉ።

የሚመለከታቸው የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል የሥራ ኃላፊዎች በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን መጉላላትና አግላይ የነውር ተግባር ታስቆሙ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደሴ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቅ የከተማዋን ሰላም ሊያስጠብቁ እንደሚገባ የደሴ ከተማ አስተዳደር ገልጿል። ነዋሪዎች በሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎች፣ መረጃዎችና አሉባልታ አትደናገሩ ብሏል። ማንኛውም የተለየና አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ነዋሪዎች ለጸጥታ ኃይል በማሳወቅ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ተጠይቋል። ከተለያዩ አከባቢዎች ለመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ነገር…
#Update

#ደቡብ_ወሎ

በደቡብ ወሎ ከታች ቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ህዝቡን እንዲረጋጋ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዞኑ ባሉ ወረዳዎች ውስጥ የሀገር መከላከያን ልብስ በመልበስ መከላከያ በመምሰል በአቋራጭ መንገዶች ሲጓዙ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

በአሉባልታ ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ በርካታ ሰዎች ወደ ዞኑ እየገቡ መሆኑን የገለፀው የደቡብ ወሎ ዞን ከሰሜን ወሎ ዞን ጋር በመሆን መመለስ ያለባቸውን ተፈናቃዮች እና ሰሌዳ አልባ ተሽከርካሪዎችን የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

#አምባሰል_ወረዳ

በአምባሳል ወረዳ ሀሰተኛ አሉባልታ ሲነዙ እና ህብረተሰቡን በማወክ ዘረፋ ሊፈፅሙ ተዘጋጅተው የነበሩ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል።

መላው ነዋሪ በሀሰተኛ ወሬና አሉባልታ ሳይደናገጥ በፍፁም መረጋጋት አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቦለታል።

#ሐይቅ

በሐይቅ ከተማ " ከዚህ ቀደም ህወሓት ቀብሮት የነበረ ከባድ እና ቀላል መሳሪያ ተገኘ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አሳውቋል።

የህብረተሰቡን ሰላም ለማወክና አካባቢው እንዳይረጋጋ እንዲሁም ተከታይ ለማብዛት ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

" ምንም ባላያችሁበትና ባላረጋገጣችሁበት አዲስ አበባ ቁጭ ብላችሁ በሀሰተኛ መረጃ ህዝብ የምትረብሹ ኃላፊነት የጎደላችሁ የማህበራዊ አንቂ ነን የምትሉ ግለሰቦች፣ ዩትዩበሮች ከድርጊታችሁ ታቀቡ " ያለው የሐይቅ ፖሊስ ይህን የፈፀሙት ላይ በህግ እንዲጠየቁ እየሰራው ነው ብሏል።

ነዋሪዎች በሀሰተኛ መረጃ ይስደናገጡ በተረጋጋ ሁኔታ የአካባቢውን ሰላም በንቃት እንዲጠብቁ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia