TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጅማ አባጅፋር ደጋፊዎች ለኢትዮጵያ ሚዲያዎች ያስተላለፉት መልዕክት...⬇️

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሚዲያዎች።

#ውድ የኢትዮጵያ ሚድያዎች በያላቹበት የጅማ አባጅፋርን ውድቀት የምትመኙ እንደምን አላቹ እኛ ጅማዎች በመጣን በአመታችን እንደዚህ ታላላቅ ቡድኖች የሚያስጨንቅና ሌሎችን የሚያሳስቅ ቡድን ገንብተን ይኸው ድፍን ዓመት ሊሞላን ነው

#እናንተ ሚድያዎች ግን ምን ያክል አድሎ በቡድኖች ላይ እንደምታደርጉ ያየንበትን ዓመት አሳልፈናል የኛ ጅማ አባጅፋር ዓመቱን በሙሉ እንደዚህ የሚገርም እንቅስቃሴ እያደረገ አንድም ግዜ ስለክለባችን ድንቅ ብቃትና ጥንካሬ ዘገባ ሳትሰሩ ውጤቱንና ደረጃውን ከመግለፅ ባልዘለለ ዓመቱን ዘለቃቹት

#እኛ ጅማዎች ስለ ክለባችን እንድታወሩ ለማድረግ ቢራ ፋብሪካ🍺 የለንም ነገር ግን ድንቅ የሆነ የፍቅር መገለጫ ቡና☕️ አለን ፍቅር ማሳየት እና ቡና በነፃ ማጠጣት እንጂ እንድታወሩልን መቼም ገንዘብ አንሰጣቹም ነገር ግን ለሙያቹ ታማኝ ሆናቹ ሁሉንም አገልግሉ

#ይህን ስንል ግን በየቦታው እየተጓዙ ጫወታውን በቀጥታ በRadio ለጅማና ወዳጆቿ የሚያስተላልፉትን እና OBN, Fano እና ጅማ ማህበረሰብ ሳናመሰግናቹና ሳናደንቃቹ አናልፍም

#በስተመጨረሻም ገና ቻምፒዎን እኖናለን ገና አንድ ነጥብ ስንጥል ምን እንዳላቹ እናውቃለን እኛ በልጆቻችን ትልቅ እምነት አለን በወሬያቹ ቢሆንማ እነ....... ቻምፒዮንስሊግ ሁላ ባነሱ ነበር

#እኛ ግን ፍቅር ነን እንወዳቹዋለን ማብራርያም ከፈለጋቹ ኑ ቡና እየጠጣን እንጨዋወት

#የኛ ጅማ አባጅፋር ታሪክ መስራቱን ይቀጥላል
#ይህን መረጃ በየSocial ሚድያው Share በማድረግ እየተሰራብን ያለውን ለሰው እናሳውቅ።

@tsegabwolde @tikahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

ውድ ኢትዮጵያዊያን ሃገራችንን ምንወደው የራሳችን የሆኑ ነገሮችን ስንወድ፤ እርስ በእርሳችን ስንከባበርና ስንፋቀር ነው። እኛ ብዙ ቋንቋ፣ ባህልና እምነት ያለን ኩሩ ህዝቦች ነን። ኢትዮጵያዊነት #ሱስ የሚሆንብን ስለራሳችን ህዝብ፤ ስለምንወዳት ሀገራች ጠንቅቀን ስናውቅ ነው። ሁሉም ቋንቋ እና ባህል #የኛ የኢትዮጵያዊያን ነው፤ ልንኮራባቸው ለንከበከባቸው ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethedu
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ትላንት በተጠናቀቀው የካቲት ወር በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል። ጉዳትም ደርሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወሩ ስለነበሩት ሁኔታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት እጅግ በርካታ ቀናትን የወሰደ ሙከራ ቢያደርግም ምንም ምላሽ የሚሰጠ አካል አላገኘም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ግን ስለነበሩት ሁኔታዎች…
#AmharaRegion

° " ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረገው በገዛ ከተማው ነው መአት ያወረደበት ... ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከአጎራባች ' ሸኔ ' ናቸው " - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

° " #ሀሰት_ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም " " - አባገዳ አህመድ ማህመድ

በአማራ ክልል ፤ የሰሜን ሸዋን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች ላይ ግጭት ከጀመረ ከሳምንት በላይ ሆኖታል።

በተደጋጋሚ ፦
- የሰዎች ደም በሚፈስበት፣
- ንብረት በሚወድምበት ፣
- ሰዎች ቄያቸውን ለቀው በሚፈናቀሉበት በዚህ ቀጠና ባለፈው የካቲት ወር ውስጥም በርካቶች መገደላቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ #ከ8_ቀናት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ መባባሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በመነሻው ላይ በሁለቱም በኩል እርስ በእርስ መወነጃጀል ያለ ሲሆን በኤፍራታ ግድምና ቀወት ውስጥ ግጭቱ ከፍቶ መዋሉ ነው የተሰማው።

በሁለቱም በኩል ያሉት ነዋሪዎች ፣ የአጣዬ ከንቲባ ፣ የአካባቢው አባገዳ ምን አሉ ?

በኤፍራታ ግድም ወረዳ የአላላ ከተማ ነዋሪ ፤ ጦርነት ከተጀመረ 8 ቀን መያዙን ፣  ብዙ ቤቶች መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪው " የአርሶ አደሮች ዱቄት ሳይቀር ፣ በግ ፣ ፍየል ፣ ግመል ፣ አህያ፣ ከብት በሙሉ ሙልጭ አድርገው ወስደውብናል። ኃላሸት የሚባል ሰውም ገድለውብናል እኛው ክልል ላይ ገብተው " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ካደረጉ በኃላ ህዝቡ ተሬ እና ዘንቦ ወደሚባለው አካባቢ በለበሰው ልብስ ሸሽቶ ተጠልሎ እንደሚገኝ ገልጸዋል። " በተከታታይ 18 ሰዎችን ገድለውብናል "ም ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰንበቴ ነዋሪ ፤ " እስከ ጅሌ ጥሙጋ ባርሲሳ ፣ ካራ ሌንጫ ፣ መከና ወይም አጣዬ ከተማ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ከትላንትና ጀምሮ ተኩስ ነበር። ትላንት አንዲት ሴት እንዲሁም ግመልና ከብቶችም ተመተው ነበር ግጭቱ የቀጠለው በዚህ ነው፤ አንድ ሰው ሲሞት ሁለት ሰው ቆስለዋል፤ አንዱ ወደ አዳማ ተልኳል። ዛሬ ደግሞ 4 ሰው ሲሞት 3 ሰው ቆስሏል " ብለዋል።

ዋነኛው እቅዳቸው የጅሌ ጥሙጋ ከተማ #ሰንበቴን " እንይዛለን ፣ እናጠፋለን " የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ የአጣዬ ነዋሪ ደግሞ ፤ ሰሞኑን ግጭት ተባብሶ ዛሬ አጣዬን በተኩስ ልውውጥ ሲያናውጥ መዋሉን ፣ 5 ሰው መገደሉም. ጥቃት ፈፃሚዎቹ የታጠቁ አካላት " ሸኔ " ናቸው ብለዋል።

ሌላው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፣ የሰንበቴ ነዋሪ " ግጭቱ የጀመረው #መጋቢት_አንድ ላይ ነው። ይህም በጅሌጥሙጋ ኮላሽ የሚባል ስፍራ 1 ሰው ገድለው 2 ሰው አቁስለው ከብቶችንም ነድተው ከሄዱ በኃላ ነው ግጭቱን የተስፋፋው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከባልች ቀበሌ እስከ ሰንበቴ እና መከና አጣዬ ድረስ ጦርነት ነው። የዛሬውን ለየት ያደረገው ታጣቂዎቹ #ከሰሜን_ሸዋ ተሰባስበው ፤ እራሳቸውን አደራጀትው ሌሊቱን በተሽከርካሪዎች ተጉዘው መጥተው ውጊያ መክፈታቸው ነው " ሲሉ አክለዋል።

ባለፉት 10 ቀናት 29 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረው የተወሰዱት ከብቶችና የወደመው ንብረትም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ አስተያየት #አልቀበልም ያሉት የአላላ ነዋሪው ፤ " አማራው ሲያጠፋ በአማራው አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ፤ ከኦሮሞውም ሲያጠፋ አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ ሰላም የሚያሰፍነው ይሄ ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህግ እና በሽምግልና  ነገሩ መክሰም አለበት እነሱ የሚሉት ከጨፋ ጀምሮ እስከ ሸዋሮቢት ድረስ የኦሮሞ ቦታ ነው። አጣዬም #የኛ_ነች ፤ አላላም ፣ ሞላሌም ፣ ማጀቴም ... ሁሉም የኛ ነው የሚሉት። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ችግሩን ሊፈታው ይገባል " ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #አባገዳ አህመድ ማህመድ " መንገድ የለም። ከጅሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፋርሲ ወረዳዎች እንዲሁም ከዞን መገናኘት አልቻልንም " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሃይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች ተሰባስበው መፍትሄው ምንድነው ? ለማለት መንገዱ ተከፍቶ ለህዝቡ ምግብ ለማድረስ ፣ የቆሰሉትንም ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ ጥረት ላይ ነን። መንገድ ከተዘጋ 1 ወር ሊሆነው ነው። እኛም ሆነ መንግሥታዊ አመራሩ ሄደን ማየት አልቻልንም። የአማራ ክልልም #ታጣቂዎቹን_ስለሚፈሯቸው ቀርበው ለማነጋገር አልተቻለም። እኛ ጋር ያሉትን #ወሰናችሁን አልፋችሁ አትሂዱ እያልን እየመከርናቸው ነው ። " ገልጸዋል።

ነዋሪዎችና የአካባቢው አስተዳደሮች ጥቃቱን የከፈቱት " ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ናቸው ቢሉም አባገዳ አህመድ " ሀሰት ነው " ብለዋል።

" ሀሰት ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እዚህ አልገባም። እየተዋጋ ያለው እራሱ ነዋሪው ነው " ብለዋል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባው ተመስገን ተስፋ ፤ ከተማዋና ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረጉት ብለዋል።

አጣዬ ላይ ' #ወረራ ' መፈፀሙን ገልጸው " ሰውም አልቋል፤ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለዋል።

ይህን የሚፈፅሙት ከአጎራባች  " #ሸኔ በሏቸው " ሲሉ የጠሯቸውን የታጠቁ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

" ዋናው መፍትሄ መንግሥት ጠንከር ብሎ #እርምጃ መውሰድ ያለበት ላይ እርምጃ መውሰድ ፤ ይሄ ነበረ መፍትሄው  አሁን ባለው መንገድ ፣ #በእሹሩሩ ሰውም አለቀ " ብለዋል።

#የአጣዬ_ህዝብ የገዛ ከተማው ላይ እንዳለ መአት እንደወረደበት የገለጹት ከንቲባው " እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መንግስት ቢደርስልን ጥሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በኩል ለጥፋቱ ለችገሩ " የፋኖ ታጣቂዎችን " ተጠያቂ ሲያደርጉ ከሰሜን ሸዋ ዞን በኩል ደግሞ " ሸኔን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ተጠያቂ ያደርጋሉ።

NB. ባለፉት አምስት ዓመታት አጣዬ ከ10 ጊዜ በላይ የመቃጠል አደጋ አስተናግዳለች።

እስካሁን የአማራ ክልል መንግሥት ስለ ጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የቪ.ኦ.ኤ. ራድዮ (ጋዜጠኛ መስፍን አራጌ) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia