TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀሰተኛ ወሬዎችን ተጠንቀቁ‼️

በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ #ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለመረበሽ የሚደረጉ ማናቸውንም ዓይነት እንቅስቃሴዎችን በመለየት በጋራ እንደሚከላከሉ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አካላት ገለፁ፡፡

ተማሪዎቹም ተጨባጭ ባልሆኑና መሠረተቢስ #ሀሰተኛ ወሬዎች ተታለው ሳይደናገጡ ዋና ትኩረታቸው በትምህርታቸው ላይ ሊሆን እንደሚገባም የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ አሳስበዋል፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ መማር ማስተማር ሂደትን #ለማደናቀፍና ለመረበሽ የሚፈልጉ አንዳንድ ሀይሎች ተማሪዎች ርስበርስ እንዲጋጩ ሆን ተብለው መሠረት የሌላቸው ሀሰተኛ ወሬዎችን በግቢው ውስጥ በመንዛት #ብጥብጥና ግጭት ለመፍጠር የተሞከረው ሙከራ አለመሳካቱን ገልፀው፣ ዩኒቨርሲቲው ያለውን መልካም ስምና ገፅታን በማበላሻትና ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተረጋግቶ እንዳይከታተሉ ለማድርግ በውጭም ሆነ በውስጥ በሚሰሩ የጥፋት ሀይሎች ላይ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው የተደረሰበትንም ውሳኔና እርምጃ በቀጣዩ ዩኒቨርሲቲው እንደሚያሳውቅ ተነግረዋል፡፡

ተማሪዎችም ከእውነት በራቁና በሚናፈሱ ወሬዎች ሳይደናገሩ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ እንዲሁም ወላጆችም ባልተጨበጠና ሀላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች በማህበራዊ ድህረ-ገጽ በሚሰራጩ መሰረት በሌላቸው ወሬዎች ሊረበሹ እንደማይገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ #ሲሳይ_ዮሐንስ እንደተናገረው ተማሪዎች እንዳይረጋጉ ሆን ተብሎ በሀሰት የሚነዙ ወሬዎች መኖራቸውን ጠቅሶ በአሁኑ ግዜ የመማር ማስተማሩ ተግባር ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ነው ሲል ተነግረዋል፡፡

ምንጭ፦ Hadiya zone Communication main process
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ሊወጣ ነው‼️

ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር ላይ አዲስ ህግ ልታወጣ መሆኗን አስታወቀች።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ #የጥላቻ_ንግግርን የተመለከተና ተጠያቂነትን የሚያመጣ አዲስ ረቂቅ ህግ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ እንደገለጹት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተስፋፉ የመጡት ሃላፊነት የጎደላቸው መልዕክቶችና የሀሰት ወሬዎች በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት በመሆናቸው መንግስት ይህን አደጋ ለማስወገድ ህጋዊ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል አሰራር በማርቀቅ ላይ ነው።

ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ምሁራን አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው።

የጥላቻ ንንግሮች የዓለማችን የወቅቱ ፈተና እንደሆኑ ይገለጻል።

በሃገረ አሜሪካ የጥላቻ ንግግር ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር ተያይዞ ሰፊ የውይይት አጀንዳ የከፈተ ጉዳይ ነው።

አሜሪካ በህገመንግስቷ የመጀመሪያ ክፍል ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሳይሸራረፍ እንዲከበር ማድርጓ ለጥላቻ ንግግር መበራከት አስተዋጽኦ አድርጓል የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም ህዝብን ከህብ የሚያጋጩ፣ ሁከትን የሚፈጥሩና ሰላምን የሚያውኩ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ግን አሜሪካ ጠበቅ ያለ ርምጃ ትወስዳለች።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መምጣትና መስፋፋት ለጥላቻ ንግግሮች መበራከት አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚገልጹ የዘርፉ ባለሙያዎች ዓለማችን ከገጠሟት የጊዜው ብርቱ አደጋዎች አንዱ እንደሆነም ያስምራሉ።

ኢትዮጵያም የጥላቻ ንግግሮች ሰላባ ለመሆኗ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚከሰቱ #ግጭቶች አይነተኛ ማሳያ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የጥላቻ ንግግሮችና #ሀሰተኛ_ወሬዎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ሰበብ ምክንያት መሆናቸውን እንዳመነበት ገልጿል።

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ክፍል ሃላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ ይህን አደጋ ለመቀነስ የጥላቻ ንግግሮች ላይ ገደብና ተጠያቂነት የሚያሰፍን ህግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።

አቶ ዝናቡ እንዳሉት ኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ላይ መገኘቷን ተከትሎ ለጀመረችው የለውጥ ጎዳና እንቅፋት የሚሆኑትን ጉዳዮች በመለየት በህግ ልትፈታቸው ተዘጋጅታለች።

በተለይም ለህዝብ የሚቀርቡ ንግግሮችና የሚተላለፉ መልዕክቶችን በተመለከተ ሃላፊነትና ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ነው አቶ ዝናቡ የገለጹት።

የማህበራዊ ሚዲያዎች መበራከት ከጥቅማቸው እኩል ጉዳቶችንም ማስከተላቸውን የጠቀሱት አቶ ዝናቡ በጥላቻ ንግግሮችና ሃላፊነት በጎደላቸው እንቅስቃሴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል።

በመሆኑም መንግስት እነዚህን ግጭት ቀስቃሽና ሰላም አዋኪ የሆኑ የጥላቻ ንግግሮችን ለማስቆም ረቂቅ ህግ በማዘጋጀት ላይ ሲሆን በቅርቡ ተጠናቆ ለሚመለከተው አካል ለውይይት እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

አንዳንድ ምሁራን ጉዳዩ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጋፋው ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሳንሱር ማድረግ አስቸጋሪ እንደሆነ በመግለጽ ህጉ በምን ዓይነት መልኩ ችግሩን ለማስቀረት እንዳሰበ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነም ይገልጻሉ።

የጥላቻ ንግግሮችን በህግ ለማስቀረት የሚቻል ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ነው ምሁራን የሚገልጹት።

ምንጭ፦የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia