TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NationalBankofEthiopia

ብሔራዊ ባንክ ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉን የገንዘብ መጠን በድጋሜ ዝቅ ማድረጉ ተገለፀ።

ባንኩ ትናንት ካቲት 29 ጀምሮ ይህንንና መሰል ጉዳዮችን የያዙ መመሪዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

በማሻሻያዉ መሰረት ከባንክ ዉጭ ይዞ መንቀሳቀስ የሚቻለዉ የገንዘብ መጠን ለድርጅቶች ወደ 200,000 ብር እንዲሁም ለግለሰቦች ወደ 100,000 ብር ዝቅ እንዲል አድርጓል።

ባንኩ ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን ገደብ የሚጥል መመሪያ ሲያወጣ በ6 ወራት ዉስጥ ለ2ተኛ ጊዜ ሲሆን ከ6 ወራት በፊት የወጣዉና እስካሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆዬዉ መመሪያ ከባንክ ዉጭ ሊኖር የሚችለዉ የገንዘብ መጠን 1.5 ሚሊዮን ብር የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይም የዳያስፖራ አካዉንት ባለቤቶች የገቢ ንግድ ላይ የሚሳተፉበት አካሄድ እንዲሁ ማሻሻያ ተደርጎበታል።

በዚህ መሰረት እነዚሁ ደንበኞች በአስመጭነት መሳተፍ የሚችሉት ባንኩ ቅዲሚያ ትኩረት እንዲያገኙ መርጫቸዋለሁ ባላቸዉ ዘርፎች ላይ የተወሰነ የዉጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንደሚኖር ተገልጿል፡፡

እነዚህ ለተለያዩ የፋብሪካ ምርቶች በግብዓትነት የሚያገለግሉ ጥሬ እቃዎች ፣ መድሃኒቶች ፣ እንዲሁም በተለዬ አስፈላጊ የተባሉ የምግብ እና ምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ብቻ እንዲሆን ታስቦ መመሪዉን ማሻሻል እንዳስፈለገ የባንኩ ምክትል ገዥ አስረድተዋል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NationalBankofEthiopia

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት የባንክ ስራን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ 5 መመሪያዎችን እንዳሻሻለ አሳውቋል።

እነዚህ መመሪያዎች በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች የተመደቡ ናቸው።

በመጀመሪያው ምድብ የሚካተቱት ፦

- “ የብድር ተጋላጭነት ጣሪያ ስለመወሰን”፤
- “ከባንኩ ጋር ዝምድና/ግንኙነት ባላቸው ወገኖች አማካኝነት ስለሚኖር የብድር ተጋላጭነት”
- “ስለንብረት ምደባ እና ለተዛማጅ ስጋቶች ስለሚያዝ የመጠባበቂያ ፕሮቪዥን ” የተመለከቱ መመሪያዎች ናቸው።

በ2ኛው ምድብ የሚካተቱት መመሪያዎች በባንክ ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አካላት ሊያሟሏቸው ስለሚገቡ መስፈርቶች እና የኩባንያ አስተዳደርን የሚመለከቱ ናቸው።

ከተደረጉ ማሻሻያዎች አንዱ ...

በከፍተኛ የብድር ተጋላጭነት ገደብ መመሪያ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

የመመሪያው ዓላማ አንድ ተበዳሪ (ተያያዥነት ያላቸው ወገኖችን ጨምሮ ) ከባንኩ ጋር በገባው ውል መሠረት ግዴታውን መወጣት ባለመቻሉ ምክንያት በባንኩ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ኪሳራ ለመቀነስ እና የባንኮች የተጋላጭነት መጠንን በወቅቱ ለመቆጣጠር የሚያስችል በቂ ፖሊሲ እና አሠራር እንዲኖራቸው ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

መመሪያው በባዝል መርህ መሠረት ማንኛውም ባንክ ለአንድ ወይም ተያያዥነት ላላቸው ደንበኞች የሚኖረው አጠቃላይ የብድር ተጋላጭነት ከባንኩ ጠቅላላ ካፒታል ከሀያ አምስት በመቶ (25%) እንዳይበልጥ ገድቧል፡፡

ይህ መመሪያ ተያያዥነት ያላቸው አካላት እንደ አንድ የባንክ ተበዳሪ ሆነው እንዲቆጠሩ ይደነግጋል።

(ተጨማሪ ማሻሻያዎችን ከላይ በተያያዘው ምስል ያንብቡ)

#NBE #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 10.7 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ተገኝቷል " - ብሔራዊ ባንክ ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል። ባንኩ " የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል " ብሏል። የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም…
#Ethiopia : ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ ምን ለውጦችን አካቷል ?

1ኛ. የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ሥርዓት ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሚና፣ ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኩራል።

2ኛ. የውጭ ምንዛሪን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማስተላለፍ ግዴታ ቀሪ ሆኗል፡፡ ላኪዎች እና ንግድ ባንኮች ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ ለራሳቸው ማስቀረት ይችላሉ። ይህ ለግሉ ዘርፍ የሚሰጠውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በእጅጉ እንደሚያሻሽል ይጠበቃል።

3ኛ. ቀደም ሲል በ38 የገቢ ንግድ ሸቀጦች ላይ ተጥሎ የነበረው እግድ ተነሥቷል፡፡ ወደ ውጭ የሚደረግ የካፒታል ሂሳብ ፍስት እንደ በፊቱ የተገደበ ቢሆንም፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያው ለገቢ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ነጻ ሆኗል፡፡

4ኛ. ምርቶችን ወደ ውጭ የሚልኩ ነጋዴዎች ካፈሩት የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለራሳቸው ያስቀሩት የነበረው 40 በመቶ ወደ 50 በመቶ ብሏል፡፡ በሂደት የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው የሚያስቀሩበት አሰራር ይዘረጋል።

5ኛ. ቀደም ሲል ባንኮች ለተለያዩ ገቢ ሸቀጦች የሚጠቀሙበት የውጭ ምንዛሪ አሠራርና አደላደል ደንቦች ቀሪ ሆነዋል፡፡

6ኛ. አሁን በሥራ ካሉና በባንኮች ከተቋቋሙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureaus) በተጨማሪ ባንክ ያልሆኑ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ይቋቋማሉ፡፡ ለእነዚህ ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችም በገበያ ዋጋ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ እንዲገዙና እንዲሸጡ የሥራ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

7ኛ. ሸቀጦችን በፍራንኮ ቫሉታ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ረገድ የተጣሉ ክልከላዎች ተነስተዋል።

8ኛ. በውጭ ተቋማት፣ በውጭ ኢንቨስተሮች እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን (በዳያስፖራዎች) የተከፈቱ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦችን አስተዳደር የሚመለከቱ በርካታ ሕጎች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

9ኛ. በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ስዎች ከውጭ የሚላክላቸውን ሐዋላ፣ በውጭ ምንዛሪ የሚከፈል ደሞዝን/የኪራይ ገቢን እና ሌሎች ገቢዎችን የሚያስቀምጡባቸውን የውጭ ምንዛሪ ሃሳቦች እንዲከፍቱ፣ እንዲሁም እነዚህን የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች ተጠቅመው የውጭ አገልግሎት ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ተፈቅዷል፡፡

10ኛ. ቀደም ሲል የግል ኩባንያዎች ወይም ባንኮች በሚወስዷቸው የውጭ ብድሮች ላይ ይከፍሉት የነበረው የወለድ ተመን ጣሪያ ተነሥቷል።

11ኛ. መመዘኛውን የሚያሟሉ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

12ኛ. በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሠሩ ኩባንያዎች የውጭ ምንዛሪ ገቢያቸውን ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው መያዝን ጨምሮ ልዩ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መብት ተሰጥቷቸዋል፡፡

13ኛ. ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ ሀገራት የሚጓዙ ወይም ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ሊይዙ በሚገባ የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ላይ ተጥለው የነበሩ የተለያዩ ጥብቅ ደንቦች እንዲላሉ ተደርጓል፡፡

#NationalBankofEthiopia

@tikvahethiopia
" የገበያ ስርዓቱ ችግር ካጋጠው ብሔራዊ ባንክ ጣልቃ ይገባል " - የብሔራዊ ባንክ ገዥ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥው ማሞ ምሕረቱ ዛሬ ለኢዜአ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ማብራሪያ ስለ ውጭ ምንዛሬ ስርዓቱ መቀየር አንስተዋል።

" ይፋ የተደረገው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ሕግ ማዕቀፍ በርካታ ለውጦች ይዞ ያመጣል " ሲሉ ገልጸውታል።

በብሔራዊ ባንክ ብቻ ይተመን የነበረው ስርዓት በመደበኛውና በትይዩ ገበያ (ጥቁር ገበያ) የተራራቀ ልዩነትን ማስፋትን ጨምሮ በርካታ ችግሮች እንደነበሩበት ጠቅሰዋል።

ከዚህ አኳያ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያው እንዲወሰን መደረጉን ገልጸዋል።

አቶ ማሞ ፥ " የምንዛሬ ተመኑ በገበያ መወሰኑ ሕገ ወጥነትና ብልሹ አሰራርን በመቅረፍ ኤክስፖርትና ኢንቨስትመንት ለማበረታታት ከፍተኛ የሆነ ሚና ይጫወታል ፣ የምንዛሬ ስርዓቱ የተረጋጋና ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል " ብለዋል።

" በዚህ ሂደት ላይ የገበያ ስርዓቱ ችግር ካጋጠው ብሔራዊ ባንክ ጣልቃ ገብቶ ያስተካክላል " ሲሉ ተናግረዋል።

#NationalBankofEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የገበያ ስርዓቱ ችግር ካጋጠው ብሔራዊ ባንክ ጣልቃ ይገባል " - የብሔራዊ ባንክ ገዥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥው ማሞ ምሕረቱ ዛሬ ለኢዜአ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህም ማብራሪያ ስለ ውጭ ምንዛሬ ስርዓቱ መቀየር አንስተዋል። " ይፋ የተደረገው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ሕግ ማዕቀፍ በርካታ ለውጦች ይዞ ያመጣል " ሲሉ ገልጸውታል። በብሔራዊ ባንክ ብቻ ይተመን የነበረው ስርዓት በመደበኛውና…
" 2.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ሆኗል " - የብሔራዊ ባንክ ገዥ

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምሕረቱ ፥ እስካሁን ባለው ከዓለም አቀፉ የገንዘብ  ተቋም (IMF) እና ዓለም ባንክ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ ከውጭ ከሚገቡ የፍጆታ ዕቃዎች 18 በመቶ ብቻ በውጭ ምንዛሬ እንደሚመጡ ገልፀዋል።

ሌሎቹ በአብዛኛው በኢ-መደበኛ ወይም በትይዩ ገበያ ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ እንደነበር ጠቁመዋል።

በዚህም " የምንዛሬ ተመኑ ወደ ገበያ መር መለወጡ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ ሊፈጥር አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።

ባንኩ ህገ-ወጥነትና አሉታዊ ጫና የሚፈጥሩ ጉዳዮች ከተከሰቱ ህጋዊ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚከሰትን ህገወጥ አሰራር ለመቆጣጠር ጥብቅ የፊሲካል እና የገንዘብ ፖሊሲ ገቢራዊ ይደረጋል ሲሉ አውጀዋል።

በዚህም " ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ በቂ ዝግጅት አድርገናል " ብለዋል።

#NationalBankofEthiopia #ENA

@tikvahethiopia