TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Embargoed_Copy_CARD_Voice_of_Guji_Eng_Oro_Amh_HR_Situation_Report.pdf
ካርድ "የጉጂ ሰቆቃ / Voice For Guji" በሚል ያጠናቀረውን ሪፖርት ይፋ አደረገ።

የመብቶች እና ዲሞክራሲ እድገት ማዕከል / ካርድ በኦሮሚያ ክልል፣ በጉጂ ዞኖች ውስጥ የሚፈጸሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን አስመልክቶ " የጉጂ ሰቆቃ / Voice For Guji " በሚል ያጠናቀረውን ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

➡️ በእነዚህ አከባቢዎች እየደረሰ ያለው የህዝብ ሰቆቃ በመገናኛ ብዙኃን ችላ ተብሏል።

➡️ ጉዳት የደረሰበት ሕዝብ ድምጹ እንዳይሰማ ሆኗል።

➡️ በተለይ በ2015 መጀመሪያ ላይ የምስራቅ ቦረና ዞን መመስረትን ተከትሎ የተፈጠሩ የፖለቲካ ችግሮች ውጥረቱን አባብሰወል።

ሪፖርቱ 36 ማሳያ ታሪኮችን አካቷል።

ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ሁለቱም ወገኖች (የመንግሥት እና የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች) ተሳታፊ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

ሪፖርቱ በማሳያ ታሪኮቹ ፦

° ከሕግ ውጪ ንፁኃን ላይ የተፈፀሙ ግድያዎች፣
° የዘፈቀደና የጅምላ እስሮች፣
° ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣
° የንብረት ውድመት፣
° አስገድዶ የመሰወር እና የገንዘብ ማግኛ እገታ ድርጊቶች፣
° የማሰቃየት እና ኢሰብዓዊ አያያዝ የመፈፀም፣
° የማፈናቀል ድርጊት የተፈፀመባቸው ንፁኃን ዜጎችን ታሪኮች ይዟል።

በሪፖርቱ ከተካተቱ ማሳያ ታሪኮች መካከል ...

አንድ ባለታሪክ " መንግሥት የአሮሞ ነጻነት ግንባርን ወደ ኢትዮጵያ ሲጠራ  የኛ ልጆች ብለን ተቀብለናቸዋል። ይሁን እንጂ መንግሥት 'ሸኔ' እያለ መጥራት ከጀመረ በኋላ ሁኔታው ተባባሰ። በሌሊት የሸኔ ተዋጊዎች ያስተዳድሩናል፣ ቀን ላይ ደግሞ የመንግሥት ኃይሎች ያስተዳድራሉ " ብለዋል።

ሌላዋ ባለታሪክ ፥ " በጉጂ የሚገኙ ማዕድናትም የግጭቱ መንስኤ ናቸው። ከጉጂ ጎሮ ዶላ ወረዳ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በመንግሥት ታጣቂዎች ሽኔ የሚል ስያሜ ስለተሰጣቸው ዕርዳታ ለማግኘት ተቸግረዋል " ስትል ገልጻለች።

ሌላኛው ባላታሪክ " ሁለቱም ወገኖች በጠላትነት የሚፈረጁትን ግለሰቦች ስም ዝርዝር ይይዛሉ፣ ይህም የአመፅና የመፈናቀል አዙሪቱን እንዲቀጥል አድርጓል" ቃሉን ሰጥቷል።

በሪፖርቱ በጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት በስፋት የተዳሰሰ ሲሆን ከ #8_ዓመት ሕጻን አንስቶ ባለትዳር እና የልጆች እናት የሆኑ ሴቶች ከአንድ በላይ በሆኑ ታጣቂዎች ተገደው መደፈራቸውን ማሳያ ታሪኮቹ ያሳያሉ።

ሪፖርቱ ወንድ ወታደሮች በጾታ ላይ የተመሰረተ ወንጀሎች ላይ የሚሳተፉት አከባቢን የመቅጣት ፤ የማዋረድ እና የመቆጣጠር ፍላጎቶች ምክንያትነት መሆናቸውን በምክንያትነት ያስቀመጠ ሲሆን በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ሁለቱም አካላት በኩል የሚፈጸም መሆኑን አንስቷል።

በተጨማሪም፥ በሁለቱም አካላት ሰዎችን በመያዝ ለመልቀቅ ገንዘብ የመጠየቅ ተግባራት ፤ ኢሰብአዊ ድብደባና ዝርፊያ መስተዋላቸውን ተገልጿል።

በግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በአግባቡ አለመታወቁ እና ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በመኖራቸው ነዋሪው መቸገሩ በሪፖርቱ ተነስቷል።

የቀረበው ምክረ-ሐሳብ ምንድነው ?

ገለልተኛ፣ ነጻ እና ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግ፤ ሁለቱም ወገኖች ግጭት እንዲያቆሙ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የጀመሩትን ድርድር እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

ሙሉ ሪፖርት ፦ t.iss.one/tikvahethiopia/88262

@tikvahethiopia