TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የብሄር ብሄረሰቦች ቀን⬇️

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል #የተራራቁና #የተኳረፉ ሕዝቦችን በማስታረቅና በማቀራረብ #ይከበራል ተባለ፡፡

የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዓሉ እስካሁን ሲከበርበት የቆየው መንገድ የተለያዩ #ክፍተቶች እንዳሉበት በጥናት #ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

በሕዝቦች መካከል የቆየውን አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች ከማስጠበቅ አንፃር ክፍተቶች ነበሩ ብለዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ላይ እየታየ ያለው ሁኔታም ለዚህ ማሳያ ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ የብሔር ማንነትንና ኢትዮጵያዊነትን በማጣመር የዘንድሮውን በዓል ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ሰው በብሔሩ ብቻ የሚፈናቀልበት፣ የሚጠቃበትና የሚገደልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ያሉት አፈ ጉባኤዋ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል መጠራጠርና አለመተማመን ተፈጥሯል፣ በህብረተሰቡ ውስጥም በርካታ ቁስል አለ ብለዋል፡፡

የዘንድሮ በዓል የተራራቁ የሚቀራረቡበትና ለመፃኢ የጋራ ተስፋቸው የሚተባበሩበት መንገድ የሚታሰብበት ሆኖ እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡

በተለይም የጎላ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ የሰላምና የማረጋጋት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ሳይንሳዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ዘላቂነት ያለው ሰላም ለመፍጠር ከወዲሁ ስራዎችን ጀምረናል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

በበዓሉ ዝግጅት ወጣቶችና የኪነ ጥበብ ሰዎች እንደሚሳተፉ የተናገሩት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ እለቱን የኢትዮጵያውያን ቀን አድርጎ ያከብራል ብለዋል፡፡

ለበዓሉ አከባበር የሚወጣው ወጪም ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የሚውል ሲሆን ድግስ የማይበዛበት ዝግጅት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊነት በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia