TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ ባለፈው የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት በትግራይ መቐለ ከተማ ዓይደር ከፍለ ከተማ በተለምዶ " ሓሚዳይ የኢንዱስትሪ መንደር " ተብሎ በሚጠራ ቦታ በቡድን የተደራጁ ዘራፊዎች የተጠና ስርቆት ሊፈፅሙ ሲሉ ተደርሶባቸው አምልጠዋል። በወቅቱ ይህ መረጃ የደረሰው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ቦታው ድረስ በመሄድ ጉዳዩን ተከታትሏል። ድርጊቱ እንዴት ተፈፀመ ? የካቲት 14/2016…
" ... ተራ የዝርፍያ ሙከራ ሳይሆን #በባለሙያ የተደገፈና የተጠና ነው " - አቶ አዳነ ሓጎስ
የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ/ም ሌሊት 8:00 ሰዓት በተደራጁ የዘራፊ ቡድኖች በመቐለ " ሓሚዳይ የኢንዱስትሪ መንደር " የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ስርቆት ሙከራ ተደርጓል።
የመቐለው የቲክቫህ አባል ፤ ለጎርፍ መከላከያና የተለያዩ አጥሮች የሚውሉ የብረት ምርቶች የሚያመርተውን " ምድሓን ጋብዮን ፋብሪካ " የተባለ ደርጅት ባለቤት የሆኑት ባለሃብት አቶ አዳነ ሓጎስ ስለጉዳዩ እንዲያብራሩለት በስልክ ጠይቆዋቸዋል።
ትራንስፎርመሩ ለፋብሪካቸው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እንዲውል የገዙትና ዋጋው 3 ሚሊዮን ብር መሆኑን ፤ የትራንስፎርመር ስርቆቱ በአከባቢው ተደጋግሞ የተፈፀመና ተራ ዝርፍያ ሳይሆን #በባለሙያ የተደገፈና የተጠና መሆኑን ገልጻዋል።
ይህ እየታወቀ ግን መንግስትና ፓሊስ ልዩ ትኩረትና ክትትል በማድረግ ባለማስቆማቸው ማዘናቸውን አስረድተዋል።
" የስርቆት ሙከራው እጅግ የተጠና ባለሃብቱን ተስፋ ከማስቆረጥ አልፎ አገር አስጥሎ የሚያሰድድ ነው " ብለዋል።
#TikvahFamilyMekelle
@tikvahethiopia