" የህዝብን ደህንነት መጠበቅ የመንግስት ዋነኛ ተግባር መሆኑ መዘንጋት የለበትም " - የትግራይ ዩኒቨርስቲዎች ምሁራን ማህበር
የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ሙሁራን ማህበር ከቅርብ ግዚያት ወዲህ በክልሉ እየታዩ ያሉ የፀጥታ ስጋቶችና ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።
ማህበሩ በመግለጫው እንዳለው ባለፉት ወራት በክልሉ የከተማና የገጠር አከባቢዎች ወንጀሎች እየተበራከቱ ሰዎች እየተገደሉ ፣ አካላቸው እየጎደለ ፣ እየታፈኑ ፣ ንብረታቸው እየተዘረፉ ነው ፤ ለምሳሌ በኣሸንዳ ሳምንት ያጋጠሙ ሁለት ከፍተኛ ወንጀሎች ለበርካቶች የሞትን የመቁሰል አደጋ ምክንያት ሆነዋል ሲል ገልጿል።
በተለይም በእህታችን ዘውዱ ሃፍቱ ላይ ያጋጠመ ወንጀል የተለየ እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ የግድያ ተግባር ነው ያለው የማህበሩ መግለጫ " በዚህም በዓሉን ለማክበር ከሌላ አከባቢ ለመጣና ለነዋሪው ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል " ብለዋል።
የምሁራን ማህበሩ መግለጫ ወንጀሎች ፣ የሰላምና የድህንነት ስጋቶች እየቀነሱ ሳይሆን እየጨመሩ መሆናቸው ገልፆ ፤ የግዚያዊ መንግስቱ አስተዳደርና በየደረጃው ያሉት የመንግስት አካላት የህዝብ ደህንነት መጠበቅ ዋነኛና የቀን ተቀን ተግባራቸው መሆን መዘንጋት የለባቸውም ሲል አስገንዝቧል።
#ስለ_ዘውዱ_ሃፍቱ ፦ ነሃሴ 13/ 2015 መኪና በሚነዱ ማንነታቸው እስከ አሁን ባልታወቁ ሰዎች በመቐለ ፤ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ደስታ ሆቴል አከባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ለህልፈት የተዳረገች እንስት ስትሆን ፤ በወቅቱ አብራት የነበረች ሰምሃል የተባለች ጓደኛዋ በሁኔታው ደንግጣ ዓይደር ሆስፒታል ገብታለች።
የዘውዱ ገዳዮች እስከ አሁን በቁጥጥር ስር ባለመዋላቸው ህዝቡ በተለይ በውስጥና በውጭ የሚገኙ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ቁጣቸው በመግለፅ ላይ ናቸው። የከተማው ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ የምርመራው ስራ ስላልተጠናቀቀ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገር አመልክቷል።
በሌላ መረጃ ፤ ነሃሴ 26 / 2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:20 በመቐለ በተለምዶ " ዳያስፓራ " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከባድ ወንጀል ተፈፅሟል።
በአከባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንዳሉት የሰሌዳ ቁጥር " 02779 ኮድ 3 " ከሆነች መኪና በመውረድ በጉዞ ላይ የነበረ አንድ ወጣትን ለማጥቃት ሲጀምሩ ሰው ስለደረሰባቸው በያዙዋት መኪና ገጭተው አምልጠዋል።
ይህንን መሰል የወንጀል ተግባሮች በመቐለ እና በሌሎች የክልሉ ከተሞች እየተባባሰ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ማሳያ ናቸው መባሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
#TikvahFamilyMekelle
@tikvahethiopia