TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አመሰግናለሁ! የእኔ በዚህችን ምድር መኖር ለምን ያህል ሰው አስፈላጊ እንደሆነ ባላውቅም ፈጣሪ ያለምክንያት እንዳልፈጠረኝ አምናለሁ። በተሰጠችኝ ትንሽ እድሜ ከራሴ አልፌ ለሰዎች መኖር እፈልጋለሁ። ለሰው ልጆች ብርሀን መሆን እፈልጋለሁ። ለሀገሬ ጉልበቴን ሳልሰስት መስራት እፈልጋለሁ። ሳታውቁትም ሆነ እወቃችሁ ለአንድ አመት ያህል የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች እኔን ገንብታችኋል፣ አርማችኋል፣ ሰው እንድሆን ሰብአዊነት እንዲሰማኝ አድርጋችኋል ለዚህ ደግሞ በቃላት ልገልፀው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ!

. ባለጠበኩት ሁኔታ ከለሊት ጀምሮ በ #መልካም_ልደት መልዕክቶች እና መልካም ምኞቶች ስልኬን ያጥለቀለቃችሁ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ወዳጆቼ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ! ፈጣሪ በእናተ ስለከበበኝ ዘውትር አመሰግነዋለሁ! እኔ የእናተም ድርምር ውጤት ነኝ! የወደዳችሁኝ ያህል እጥፉን ወዳችኋለሁ! ያከበራችሁኝን ያህል እጥፉን አከብራችኋለሁ!

ለሁላችሁም ፈጣሪ ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልኝ!

ሚያዚያ 17 - ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህፃን ሚሊዮን🔝

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ህጻን ሚሊዮንን #በጉዲፈቻ ለማሳደግ ያቀረቡት ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አገኘ።

ቀዳማዊ ቤተሰቡ ህጻን #ሚሊዮንን ከክበበ ህጻናት ማሳደጊያ ተቀብሎ #ለማሳደግ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም ለፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 7ኛ የወንጀል ችሎት የህጻናትና ሴቶች ጉዳይ በፅሁፍ ማመልከቻ አቅርቦ ነበር። በማመልከቻቸው አመልካቾች የተፈራረሙበት የጉዲፈቻ ውል #እንዲጸድቅላቸው ጠይቀዋል።

ቀዳማዊ ቤተሰቡ ለህጻኑ #መልካም አስተዳደግ እንደሚሰጥና ህጻኑን ለማሳደግ በቂ ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዳለው ጠቅሷል። ፍርድ ቤቱም ህጻን ሚሊዮን ከሁለት አመት እድሜ በታች በመሆኑ ችሎት ፊት ቀርቦ አስተያየት መስጠት ስለማይችል ችሎቱ የተለያዩ ማስረጃዎችን መርምሮ፥ አመልካቾች ህጻኑን በጉዲፈቻ ቢያሳድጉት ችግር የለውም ወይም መልካም ነው ብሎ በመወሰን ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም የተፈራረሙትን ውል ተሻሽሎ በወጣው የቤተሰብ ህግ 213/92 አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት አጽድቆላቸዋል።

የውሳኔውን ግልባጭም ጉዳዩን ችሎት ፊት ቀርበው ለተከታተሉት ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው እንዲደርሳቸው ተደርጓል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ለቀዳማዊ ቤተሰቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አያይዘውም በጉዲፈቻ ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው ለሌሎች አርዓያ እንደሚሆንና ልጅ ማሳደግ ትልቅ ሃላፊነት መሆኑን እንዲሁም ህጻናትን በጉዲፈቻ ለማሳደግ ሁሉም እንዲያስብ ያደርጋል ብለዋል።

በእድሜያቸው ሶስት መንግስታት ማየታቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንቷ ከፍተኛ የሃገር መሪዎችና ሃላፊዎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸውን ሲያስፈጽሙ አይተው እንደማያውቁም ተናግረዋል። ቀዳማዊት እመቤቷ #ችሎት ፊት ቀርበው ጉዳያቸውን ማስፈጸማቸው ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል መሆኑን ያመላክታልም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ስራ

የAAU ዩኒቨርሲቲ 4ኪሎ ካምፓስ የዘንድሮ ተመራቂ የሆኑ የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራቂዎች ከምርቃታቸው ከሳምንት በፊት "Tesfa Parents Childhood Cancer Organization" በመገኘት ከህፃናት ከንሰር ታማሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፈዋል።

መልካም ስራችሁ ለሌሎች ወጣቶች መማሪያ ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ዜና

አዲስ አበባ በሚገኙ 12 የመንግስት ሆስፒታሎች በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከነገ ጀምሮ #ነፃ አገልግሎት መስጠት ሊጀምሩ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለፁት “በጎነት በሆስፒታል” በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች ከነገ ጀምሮ በተለያዩ ሆስፒታሎች አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ።

ወጣቶቹ በየሆስፒታሎቹ በተለይም አስታማሚ ለሌላቸው ወገኖች እገዛና ድጋፍ የማድረግም ሚና ይኖራቸዋል ተብሏል።

ወጣቶቹ የሚሰጧቸው አገልግሎቶች፦

•በፅኑ የታመሙ ታካሚዎችን ወደ ህክምና ክፍል በመውሰድ፤
•የህክምና ካርድ ማውጣት፤
•የአካባቢ ጽዳትና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ይሆናል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ዜና

በእሳት ቃጠሎ ጉዳት የደረሰበት የስሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የሳር ምድር ሙሉ ለሙሉ አገግሟል ተባለ፡፡ የፓርኩን የደን ሽፋን ለማሳደግ 50 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉም ተነግሯል፡፡

Via #ShegerFM
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ስራ! በህይወት ሳለን የመረዳጃ እድር ከሌሎች ማህበራት ጋር በመተባበር 90ሺህ ብርና የትምህርት ቁሳቁስን አሰባስቦ ረዳት ለሌላቸዉ አረጋዊያንና ተማሪዎች ደጋፍ አበረከተ። 90ሺህ ብር፤ ብርድ ልብስና ሳሙና ለአረጋዊያን ድጋፍ የተደረገ ሲሆን እንዲሁም ቦርሳ፣ ደብተር፣ እስክርቢቶና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶች ለተማሪዎች መበርከቱ ተገልጿል። ይህ ድጋፍም ለ20 #አረጋዊያንና 300 ለሚሆኑ ህፃናት ተማሪዎች መሆኑም ታውቋል። በዚህ በጎ አድራጎት ስራም ተስፋ ልማት አቀፍ ማህበር፣ ቦኤዝ ምግብ ኮምፕሌክስ፣ ይቻላል ፋውንዴሽን፣ አስቴር ቤተ ፍቅርና ያጅቡሻል የመድሃኒት መደብር የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸዉ ተገልጿል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመላው ለ2011 የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች #መልካም_እድል እንዲገጥማችሁ TIKVAH-ETHIOPIA መልካም ምኞቱን ይገልጻል!

TIKVAH-MAGAZINE በመቀላቀል ስለውጤታችሁ አዳዲስ መረጃዎችን መከታተል ትችላላችሁ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#መልካም_ዜና

በትግራይ ክልል #ህዝቡ ባደረገው ከፍተኛ ተሳትፎና የመከላከል ስራ ራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና እንደርታ ወረዳዎች ከአንበጣ መንጋ ነፃ መሆናቸው ተገለፀ። ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባለፉት ሳምንታት በተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ መከሰቱ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም በትግራይ ክልል መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኞች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በክልሉ ያሉ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች፣ የክልሉ ልዩ ሀይል፣ ተማሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባደረጉት የመከላከል ስራ በራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና እንደርታ ተከስቶ የነበረው አንበጣ መንጋ መወገዱን የክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረፋ

መልካም በዓል !

" ይህን የተባረከ #የአረፋ_ቀን እምነታችንን በልባችንና በተግባራችን የምናድስበት ፤ ስላጠፋነው ጥፋት / ስህተት ከልብ አዝነን ዳግመኛ ወደዛ ላለመመለስ ቃል የምንገባበት እና ወደ ሁሉን ቻይ አምላካችን #አሏህ 🤲 የምንቀርብበት ቀን ነው። " - ሙፍቲ ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር)

#መልካም_በዓል !!
#TikvahFamily ❤️

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM