#AddisAbaba
° “ መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን ” - ማኀበራት
° “ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” - የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር
በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ለመገንባት በማኀበር ተደራጅተው ከቱሉዲምቱ እስከ ዓለም ባንክ ድረስ ቤት እየገነቡ የየበሩ ማኀበራት፣ “መሬቱ በኦዲት ሰበብ ታግዶ የበደል በደል ነው የደረሰብን” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በሰጡት ቃል፣ “እንደ ማኀበር በጋራ ሆነን ጥያቄ አቅርበን እየተከታተልን ነው ከ3 ዓመታት በላይ የቆየነው። ‘ያኔ ለጊዜው ይቁም፣ በፍጥነት ምላሽ ይሰጣል’ ተብሎ ቆሞ ነበር አሁን ስንሄድ ነው የሚያናግረን ሰው ያጣነው” ብለዋል።
ቦታዎቹ #ከቱሉዲምቱ እስከ #ዓለምባንክ እንደሚገኙ አመልክተው፣ “ አጠቃላይ 960 ማኀበራት ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 217ቱን ‘ መስተንግዶ ያግኙ ’ ብለው ለቀውላቸዋል። የቀረነው ግን ‘ ይለቀቃል ’ ተብሎ ለረጅም ጊዜ እየታሸን ነው ” ሲሉ አማረዋል።
➡️ ቤት ለመገንባት ከባንክ ገንዘብ የተበደሩ እንዳሉ፣
➡️ የባንክ እዳቸውን ከፍለው ባለመጨረሳቸው መሬታቸው ለጨረታ የቀረበ እንዳሉ፣
➡️ ቤታቸውን ለመሸጥ የፈለጉ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።
ይህ የሆነው ፣ “ ሕገ ወጥ #የመሬት_ወረራ በመኖሩ ኦዲት ይደረግ ” በሚል ሰበብ እንደሆነ፣ እነርሱ ግን መሬታቸው ሕገ ወጥ እንዳልሆነ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸው፣ ከተማ አስተዳደሩ ኦዲቱን በፍጥነት አጣርቶና አጠናቆ እግዱን እንዲያነሳ ጠይቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የቅሬታ አቅራቢዎቹ ሰነድ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቱ ውል ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ የተገባ መሆኑን ፣ ከባንክ #በ100_ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደተበደሩ ያስረዳል።
ማኀበራቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ኃላፊዎች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
በከተማ አስተዳደሩ የቅሬታና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባይነህ አመርቆ ቅሬታውን በተመለከተ ለመናኸሪያ ሬዲዮ በሰጡት ቃል ግን፣ “ግለሰቦች በሌላ ማኀበር የከተማዋን ሀብት ለግል ጥቅም ለማዋል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይደረጉ እንደነበር ይታወቃል” ብለዋል።
“ ይህንምን መነሻ አድርጎም የተወሰኑ የታገዱ አሉ ፣ Specific የሚታወቁ ማለት ነው ” ብለው ፣ የእኚሁ አካላት ጉዳይ “ትክክለኛ ነው? ትክክል አይደለም ? የሚለው ነገር ተጣርቶ ውሳኔ የሚሰጣቸው ” እንደሆኑ አስረድተዋል።
“ ከዛ ውጪ ግን ቅሬታ ያላቸው ካሉ በማንኛውም ጊዜ መጥተው ማቅረብ ይችላሉ” ነው ያሉት።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia