#TikTok #USAHouse
የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ተሰብስቦ ለዩክሬን ፣ ለእስራኤል እና ለሌሎች የባህር ማዶ የአሜሪካ አጋሮች የ95 ቢሊዮን ዶላር (5,419,427,000,000 ብር) የእርዳታ ጥቅል/ፓኬጅ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።
" ቲክቶክ " በአሜሪካ እንዲታገድም ድምጽ ሰጥቷል።
የተወካዮች ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ድምፅ የሰጠው በ " #ቲክቶክ " ጉዳይ ሲሆን ባለቤትነቱ የባይትዳንስ የሆነው መተግበሪያ ለአሜሪካ ኩባንያ ካልተሸጠና ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት ካላቋረጠ በመላው አሜሪካ ውጤታማ በሆነ መንገድ #ለማገድ 360 ለ 58 በሆነ ድምጽ ረቂቅ ሕግ #አጽድቋል።
" ቲክቶክ " በአሜሪካ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።
በመቀጠል ምክር ቤቱ ፦
➡️ ለዩክሬን 60.8 ቢሊዮን ዶላር (3,422,796,000,000 ብር)፤
➡️ ለእስራኤል 26.4 ቢሊዮን ዶላር (1,483,211,600,000 ብር)፤
➡️ ለታይዋን እና ለኢንዶ ፓስፊክ ሀገራት ' ቻይናን ለሚጋፈጡ ' የ8 ቢሊዮን ዶላር (456,372,800,000 ብር) የእርዳታ ድጋፍ በድምሩ የ95 ቢሊዮን ዶላር ጥቅል እርዳታ ረቂቅ ሕግ አጽድቋል።
የምክር ቤቱ አባላት የዩክሬን ድጋፍ ሲጸድቅ ፤ " ዩክሬን !! " እያሉ በመጮህ የሀገሪቱን ባንዲራ ሲያውለበልቡ ታይተዋል።
@thiqahEth @tikvahethiopia